Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, September 14, 2014

የአምባገነንነት ዘመን ውጣ የነፃነት ዘመን ግባ

አዲስ ዓመት ካለው የተሻለ ነገር የምንፈጥርበት  እንዲሆንልን በመመኘት ካለፉት ብዙ አዲስ አመቶች የሚለይበትን እና በሕይወታችን ትርጉም ያለው ለውጥ የምናመጣበት  እንዲሆን የህሊና ጥንካሬያችንን ማጎልበት ይጠበቅብናል::
ለእኛ ላመንንበት ኢትዮጵያውያን መጪው አዲስ  ዓመት ከኢህአዴግ ጋር ሙስና ዘረኝነት እኔብቻ አውቂ ነኝ ባይነት
ስድብ ጥላቻ የተሞላ ነው የሚሆነው ብሔራዊ  አለመግባባትን በየዓመቱ እያሳደገ የመጣውን የኢህአዴግ ፖሊሲ 2007 መጨረሻው እንዲሆን እራሳችንን ለመጪው ምርጫ  እናዘጋጅ። ባለፉት አመታት በኢህአዴግ ፍፁም ስህተት በኢህአዴግ ሰራሽ የኑሮ ውድነት ኢትዮጵያውያን ጀርባችን  ደምቶዋል።
ከአመት ዓመት የውጭ እርዳታ የሚቀበለው ኢህአዴግ ሕዝቡም ነፍሱን ሸጦ ከሀገር የውጣ ቤተሰቡ ከውጭ  በሚልክለት እርዳታ የኑሮን ሁለት ጫፎች ለማገናኘት ሲዳክር ይሄው ሃያሶስት ዓመት ከኢህአዴግ ጋር አሳልፈናል።የተሻለ ቀን ይመጣል እያልን ስንጠብቅ በኢህአዴግ ቀስ በቀስ የባሰ ቀን እያመጣብን ክፉኛ በኑሮ ውድነት እየተደቆስን ነው ያለነው።

በዚህ አዲስ ዓመት ከውጭ ያሉ ወዳጅ ዘመዶች  የላኩት ገንዘብ ባይላክ ምን እንሆናለን ብለን ማሰብ ይገባናል? የተሻለ ቀን እራሱ አይመጣም የተሻለ ቀን እራሳችን  ነን የምናመጣው ለዚህም ምርጫ 2007 የመጀመሪያ በዚህ አዲስ ዓመት ያለን አማራጭ ነው።
ኢትዮጵያ ሀገራችን  ቤታችን ናት ይህቺን የምንወዳትን ሀገራችንን ለራሳችን እንድትመቸን ማድረግ የራሳችን ግዴታ ነው ይህም የቤት ሥራ በ2007 ልንሰራው ይገባል። ማንንም ሳንጠላ ሀገራችንን መውደድ እና በሀገራችን ጉዳይ ነቅተን መሳተፍ አማራጭ  የሌለው የትግል ጎዳናችን ነው። ከኢህአዴግ ውጭ ለሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች ዕድል በመስጠት እራሳቸውን እንዲያጠነክሩ እናድርግ።
በሰለጠኑት ዴሞክራሲያዊ ሃገራት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ከተመረጡ በሁዋላ በጋራ መንግስት  ሲመሰርቱ ማየት የተለመደ ነው እኛም ላሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ድምፅ ከሰጠን ብዙ ምሁራን ፖለቲካውን ይቀላቀላሉ  በጋራ ለመስራት አቅም ያገኛሉ።
በቸልተኝነት የሀገራችንን ጉዳይ በመተው ለትውልድ ያልጠራ ስርአት እና ህገ  መንግስት የምጣስበትን ሀገር እንዳናወርስ። ፈጣሪያችን 2007 መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነትን የሚያገኝበት ፍትህ የምሰፍነበት እንዲሁም ሁሉም ዜጋ ሰው እንዲሁም ኢትዮጵያዊ በመሆኑ እኩል የሚሆንበት እንዲያደርግልን እንለምናለን።
ኢትዮጵያ በ 2007 የነፃነት እና የፍትህ ምድር ትሆናለች።
ኢትዮጵያ በነፃነት ለዘላለም ትኑር።

                                        

No comments:

Post a Comment

wanted officials