የሌላ ሰው የመመርቂያ ጥናት ዘርፎ በኖርዌይ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀው ኢትዮጵያዊ ዲግሪው ተሰረዘ
በዘነበ ወላ
ሐሳዊ ምሁራንን በሀገራችን እያየን ነው፡፡ ለጥቂት ጊዜያት በምዕራቡ ዓለም መሰነባበታቸውን አስታክከው በሌላቸው እውቀትና ክህሎት አንቱታን የመሻት አባዜ የተጠናወታቸውን ሰዎች ማየት የተለመደ ክስተት ከሆነም ሰነባብቷል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎቻችን ፤ በየመሥሪያ ቤቶቻችን አድፍጠው የተቀመጡት አደባባይ ወጥተው ‹ዶክተር ኢንጅነር› ነን ብለው በድፍረት ከነገሩን በቁጥር ይልቃሉ፡፡ ያልመረመሩትንና ያላጠኑትን የሌላን ሰው ጥናት ና የምርምር ውጤት የራስ አድርጐ በማቅረብ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ከሚገኘው የትምህርት ተቋማት መመረቅ እያቆጠቆጠ ያለ ሌላው ችግር ነው፡፡በቅርቡ በኖርዌይ ትሮምሶ (Tromso) ዩኒቨርሲቲ የተከሰተው የምርምር ጽሁፍ ዘረፋ ለዚህ አባባል አንዱ ማሳያ መሆኑን የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ያምናል፡፡ የዚህ ችግር ሰለባ ከሆኑት አያሌ ሰዎች አንዱ አበራ ኃይለማርያም ወልደየስ ነው፡፡
አበራ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነው፤ በ1979ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል፡፡ ከዚሁ ተቋምበሕግ ትምህርት LLB ዲግሪውን አግኝ~ል፤ ቀጥሎም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና የደህንነት ተቋም እና ኮስታሪካ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ፎር ፒስ በጣምራ በሚያካሂዱት ፕሮግራም ተመዝግቦ በ2001 ዓ.ም በሰላምና ደህንነት ጥናት የ Joint Master of Art ዲግሪውን አግኝቷል፡፡ አበራ የአየርላንድ መንግስት በሰጠው ስኮላርሽፕ ከ Kimmage Development Study Center, Holy Ghost College በልማት ጥናት የ MA ዲግሪውን ሲያገኝ The Effect of Government Relocation Policies on the Livelihoods Strategies of Poor Households: The Case of Basha Wolde Chilot የሚል የምርምር ፁሁፍም አበርክቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አበራ ከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና የደህንነት ተቋም ሲመረቅ ያቀረበው Ethnic Identity and the Relations of Amhara, Oromo and Tigray Students at Addis Ababa University Main Campuse የሚለው የምርምር ጽሁፉ (በአቶ አንተነህ ታደሰ አስማማው የተዘረፈው) An Anthology of Peace and Security Research በሚል ርእስ ከሌሎች ጥናቶች ጋር በጋራ ታትሞለታል፡፡ ይህ ጥናት በጀርመን ሀገር Ethnic Identity ከዚህ በተጨማሪ and Ethnic relations፡ Case study on an Ethiopia Higher Learning Institution በሚል ርዕስ ለህትመት በቅቷል፡፡ አበራ Freedom of Association: Trials and Tribulations of Advocacy in Ethiopia በሚል ርዕስ ሌላ የምርምር መጽሃፍ እዚያው ጀርመን ሀገር ከማሳተሙ በተጨማሪ ‘ስምንተኛው ሺህ እና ሌሎቹም’ የሚል የአጫጭር የአማርኛ ልብ ወለዶች ስብስብ በ 1999 ዓ.ም አሳትሟል ፡፡
የአበራን የምርምር ፅሁፍ መዘረፍ መረጃው ከጋራ ወዳጆችን እንደደረሰኝ የተባለው ነገር እውነት ስለ መሆኑ ጥያቄ አቀረብሁለት፡፡ ድርጊቱ መፈፀሙን ገልጾ ችግሩን ከመሠረቱ መርምሬ ጭብጥ አንድይዝ ከ ደበሊን- አዲስ አበባ (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ)-ኖርዌይ (ቶሮሞሶ ዩኒቨርሲቲ) -ባህርዳር (ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ) ጉዳዮን አስመልክቶ የተፃፃፈበትን መረጃ ከኢንተርኔት አትሞ በቀጠሮ ሰጠኝ፡፡ እኔም ከተለያዩ አካላት ጋር የተለዋወጣቸውን የ e-mail መልዕክቶች ለሳምንት ካስተዋልኩት በኋላ በሌላ ቀጠሮ ተገናኝተን ከ አቶ

ቁም ነገር፡- ጥናትህን እንዴት አካሄድከው?
አበራ፡- እንደሚታወቀው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደህንነት ተቋም ስማር የመመረቂያ ፅሁፍ ማዘጋጀት ነበረብኝ ፤ በአዲስ ሀሳብ ላይ መፃፍ ፍላጎቴ ነበር፤ ስለሆነም Ethnic Identity and the relations of Amhara, oromo and Tigray students at Addis Ababa university main compass ርዕስ ዋናውን ካንፓስ ማዕከል አድርጌ አጠናሁ፡፡ ጥናቱ በዓይነቱ የመጀመሪያው ነው፡፡ ጉዳዩም ስሱ(sensitive) ስለነበር በጥልቀት ለማየት ብዙ ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ በመጨረሻም እጅግ በጣም ጥሩ ውጤት አገኘሁበት፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት ተቋምም ከሌሎች አምስትና ስድስት ተመራማሪዎች ጥናት አንዱ አድርጎ ለህትመት አበቃው፡፡ ስብሰቡን An Anthology of Peace and Security Research በሚል ርእስ በኢንተርኔት መረቡም በጉዳዩ ለሚያጠኑ ለቆታል፡፡ ለሰላም ና የደህንነት ጥናት ተቋም ያቀረብሁትን

ጥናት እኔ በመጽሐፍ መልክ አሻሽዬው ጽፌዋለሁ፡፡ ከጀርመኖች ጋር ባደረኩት ስምምነት በእንግሊዘኛ Ethnic Identity and Ethnic relations፡ A Case study on an Ethiopia higher landing institution በሚል ርዕስ ለህትመት በቅቷል፡፡ ይህ መጽሐፍ አሁን በአማዞን ዌብ ሳይት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ጥናቴ ነው በአንተነህ የተዘረፈው፡፡
ቁም ነገር፡- እንዴት ደረስክበት?
አበራ ፡- በወቅቱ እኔ ለሌላ ትምህርት አየር ላንድ ደብሊን ሄጄ ነበር፡፡ ሆሊ ጎሰት ኮሌጅ የልማት ጥናት(Development Studies) እየተከታተልኩ ነበር፡፡ በቀጥታ በኤንተርኔት የሚለቀቁ የምርምር ጽሁፎችን፣ የተለያዩ ምርምሮችን እና መጻሕፍትን ለመመልከት online ቤተመጻሕፍት ገባሁ ፡፡ የተለያዩ ለጥናቴ የሚያግዙኝን ምርምሮችን እየዳስስኩ ሳለሁ፤ ይሄን THE IMPACT OF ETHNICITY ON STUDENT RELATIONS IN BAHIRDAR UNIVERSITY, ETHIOPIA የሚለውን ርእስ ሳይ ኦ! ብዬ ያለፈ ጥናቴን እያስታወስኩ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ በውስጤም “እኔም ለካ በሌሎች ተመራማሪዎች ላይ ተፅዕኖ የማሳድር ሆንኩ እንዴ? ይኸው ሌሎችን ማነሳሳት ጀመርኩ ማለት ነው!” ብዬ ደስ አለኝ፡፡ ተመራማሪው አንተነህ ታደሰ አስማማው ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እንደሆነ ያትታል፡፡ የእኔ ጥናት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ካፓስ ላይ ያተኮረ ምርምር ነው፡፡ የኔ ጥናት የዩኒቨርሲቲውን የተለያዩ ካምፓሶችን አይወክልም፡፡ ሌሎቹ ካምፓሶችም በዚህ ዓይነት ብዙ ሊሠራባቸው ይችላል፡፡ ገረፍ ገረፍ ማድረጉን ተውኩና ከፍቼው ዳውን ሎድ አድርጌ ሙሉውን ማንበብ ጀመርኩኝ ፡፡ በጥልቀት ስገባበት የሆነ ያለመመቸት ስሜት ተሰማኝ፡፡ ሀሳቡ ለእኔ አዲስ ነገር አልሆነብኝም፡፡ የራሴኑ ጥናት የማነብ መሰለኝ፡፡ ወደ መጀመሪያው ገጽ ተመለስኩ፡፡ እኔ ይህንን ጥናት ለምን ማጥናት እንዳሰብኩ ያስቀመጥኳቸውን አራት ነጥቦች ቃል በቃል ይዘርዝራል፡፡ ሙሉውን ፅሁፍ ዘለልኩት እንዳለ ቃል በቃል በሙሉ የእኔን ምርምር ነው የገለበጠው፡፡ አንዲት ቃል እንኳን አልተለወጠም? እኔ ያነጋገርኳቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራን ፤ተማሪዎች ቃለ ምልልስ እንዳሰፈርኩት ይዘቱ ምንም ሳይቀየር ተገልብጦ አየሁትና በጣም አዘንኩኝ ፡፡ አንድም ቦታ የእኔን ወይም የዩኒቨርስቲውን ስም አይጠቅስም መቶ በመቶ የራሱ ምርምር አድርጐ ነው ያቀረበው፡፡
አንድ ሰው አይኑ እያየ የገዛ ንብረቱ በፈጠራው ፀሐይ ተነጥቆ የሌላ ሰው ንብረት ሲሆን ሲያየው የሚሰማው አይነት ስሜት ተሰማኝ፡፡ ይህ የሆነው ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ ነበር፡፡ ስራዬን መቀጠል አልቻልኩም፡፡ ወደ መኝታዬ ብሄድም እንቅልፍ ከየት ይምጣ ሌሊቱን በሙሉ በብስጭት በሀዘን፣ በቁጭት እህህ ስል ሌሊቱ ነጋ፡፡ቀደም ብዬ እንዳልኩት በወቅቱ እኔ ያለሁት አየርላንድ ሲሆን ችግሩ የተፈጠረው ኖርዌይ ነው ፡፡እንዴት ይህ ነውር የተሞላበት ነገር ተፈፀመ በማለት እያሰላሰልኩ ነበር በተሰበረ ልብ ማለዳውን የተያያዝኩት፡፡
ቁም ነገር፡- ማለዳ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ከወንክ?
አበራ፡- ወደ ቤተ መጻሕፍት ሄድኩ፡፡ በአጋጣሚ አንዱን አስተማሪዬን ቤተ-መጻሕፍት ውስጥ አገኘሁት፡፡ ፓትሪክ ማረን ይባላል፡፡ ለመምህሬ ሰላምታ ከሰጠሁ በኋላ የቸገረኝ ነገር እንዳለ አወጋው ጀመር “አንድ ሰው ያንተን ጥናት ሳያስፈቅድህ ወይም አንድም ስፍራ ላይ ሳይጠቅስ ለማስተር ዲግሪ መመረቂያው ቢያደርገው ምን ታደርጋለህ?” አልኩት፡፡ “ለዩኒቨርስቲው አቤቱታዬን አቅርባለሁ” አለኝ፡፡ እኔም የደረሰብኝን ነገርኩት፡፡ ‹‹አቤቱታህን ለትሮምሶ ዩኒቨርሲቲ አሁን ቁጭ በልና ጻፈው፡፡ ጽፈህ እንዳጠናቀክ ከመላክህ በፊት አሣየኝ አለኝ ፡፡እንዳለኝም እኔም አቤቱታዬን ለ ቶሮሞሶ ዩኒቨርሲቲ(ኖርዌይ) ፃፍኩና ለመምህሬ ሳላሳየው ላኩት፡፡ እንግዲህ ሲሞላላቸው አይተውት ዳኝነትም ተቀምጠው አንድ ቀን ምላሽ ይሰጡኛል ብዬ ባላስብም ወደሚቀጥለው ሥራዬ ለመሄድ እንቅስቃሴ ለማድረግ ሞከርኩ፡፡ ምን አልባትም አራት ወይም አምስት ሰዓታት ቆይቼ የኢ-ሜይል ሳጥኔን ስከፍት መልዕክቴን ሳየው ምላሽ ዩኒቨርሲቲው ሰጥቶኛል፡፡ ምክሩን የጠየኩት ሚስተር ፓትሪኩ ራሱ ከቤተ-መጽሐፍቱ አልወጣም፤ እያነበበ ነበር፡፡ ምላሹን ወስጄ አሳየሁት “ላክላቸው እንዴ?” አለኝ ‹‹ኧረ መላክ ብቻ አይደለም ምላሻቸውንም ጭምር ነው የማሳይህ›› አልኩት በጣም ተገረመ፡፡እኔም በonline ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሰላምና ደህንነት ተቋም ያሳተመውንና በኢንተርኔት የለቀቀውን የአንተነህ ታደሰ አስማማውን ፅሁፍ በተጨማሪ አማዞን ላይ የእኔን የታተመውን መጽሐፍ link አያይዤ አንተነህ በጠራራ ፀሐይ ዘረፋ መፈጸሙን ነው ለዩኒቨርሲቲው የፃፍኩት፡፡ አንድ አንቀጽ ወይም አንድ ሃሳብ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ዘረፋ ነው የከናወነው ይህንን ወንጀል ኮሚቴ አቋቁመው ምርመራ እንዲጀምሩ ነበር ያመለከትኩት፡፡ አንተነህ የተማረበት ቶሮሞስ ዩኒቨርሲቲ ዳይሬክተር ዶ/ር ሩትዝ ትባላለች እሷ የአንተነህ አማካሪው ነበረች፡፡ እሷም ምላሽ ስትሰጠኝ ‹‹እንዲህ አይነቱን ነገር ለእኛ በማድረስህ እናመሠግንሃለን፡፡ አሁኑኑ ምርመራ እንጀምራለን›› ብላ ፃፈችልኝ፡፡ በዚህ ጊዜ ትንሽ ሠላም አገኘሁ፡፡ ቀጥሎም ምን ማድረግ እንዳለብኝ ማብሰልሰል ጀምርኩኝ፡፡
ቁም ነገር፡- ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲስ ማሳወቅ አልነበረብህም?
አበራ፡- ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሰላምና ደህንነት ተቋም ጽፌአለሁ ፡፡ በወቅቱ ዳሬክተሩ አቶ ሙሉጌታ ገ/ሕይወት ነበሩ ፡፡ይህ ጉዳይ ተቋሙን በቀጥታ ይመለከተዋል፤ ምክንያቱም ለህትመት ያበቃው ጥናት ነው የተዘረፈው፡፡ ስለዚህ አብረን ሙግታችንን መቀጠል ይኖርብናል አልኩ፡፡ እኔ በወቅቱ መልዕክቴን ስልክ አቶ ሙሉጌታ በአገር ውስጥ አልነበሩም፤ ውጪ ሀገር ነበሩ፡፡ መልእክቱ እንደደረሳቸው ለምክትላቸው ለአቶ ዮናስ አስታወቁት፡፡ ሌላው ፕሮፌሰር ከጂታል (Kejetil) ኦስሎ ውሰጥ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምር መምህር ሲሆን እሱም ይህንኑ ጉዳይ እንዲከታተል አቶ ሙሉጌታ ፅፉለት፡፡ ፕሮፌሰሩ ከጂታልም ጉዳዩን አብሮኝ ለመከታተል ፍቃደኛ መሆን አለመሆኔን በ ኢሜል ጠየቀኝ ፡፡ የእሱን ተሳትፎ እጅግ በጣም እንደምፈልግ ምላሽ ሰጠሁት፡፡ ከጂታል “በእርግጥ እኔ ያለሁት በአሁኑ ጊዜ ኦስሎ ውስጥ ነው ቢሆንም መከታተል የምችልበት መንገድ አለኝና እንዲህ ዓይነቱን ነገር አጣርተን በሂደት ምላሽ ያገኛል አለኝ” በፕሮፌሰሩ ምላሽ ትንሽ መረጋጋት ጀመርኩኝ፡፡
ቁም ነገር፡- የክትትሉ ጭብጥ ከምን ደረሰ?
አበራ፡- ምንድነው ያደረኩት በአንተነህ åሁፍ ላይ ያቀረበሁት አቤቱታ ውጤቱ ሳታወቅ ፁሁፍ ዌብ ሳይት ላይ መነበብ የለበትም፡፡ አንተነህ ታደሰ አስማማውም ራሱን የመከላክል መብት አለው፡፡ የራሱን መከላከያ ሊያቀርብ ይችላል፤ አልዘረፍኩም ሊልም ይችላል፤ እኔ ተዘርፌያለው ብያለው፡፡ ስለለዚህ ይህ ክርክር ያለበት የምርምር ውጤት በዌብ ሳይት ላይ እየተነበበ መቆየት የለበትም ብዬ ስላመንኩ እንዲነሳ ለዩኒቨርሲቲው አቤቱታዬን ፃፍኩኝ፡፡ ወዲያውኑ አቤቱታዬ እንደደረሳቸው ተግባራዊ አደረጉት፡፡ ከድረ-ገፁ ላይ ፅሁፉን አነሱት ፡፡ይህ ለእኔ አንድ የተሳካ ስራ ነበር፡፡
ቁም ነገር፡- አቶ አንተነህ ምላሹ ምን ነበር?
አበራ፡- ዶ/ር ሩትዝ እንደነገረችኝ እሱም(አንተነህ) በጉዳዩ ላይ ያለውን ምላሽ እንዲሰጥ ያንተን አቤቱታ አያይዤ ልኬለታለሁ፡፡ ምላሽ እስኪሰጠን ትንሽ ትግስት ያሻናል፤ ታግሰን መጠበቅ አለብን አለችኝ፡፡ ምላሹን ስንጠብቅ ወራት ፈጀን ግለሰቡ ከቶሮሞስ ዩኒቨርሲቲ ተመርቆ የነበረው እ.ኤ.አ. 2012 ነው፡፡ እኔ ጉዳዩ ላይ የደረስኩበት በዓመቱ 2013 ነው፡፡ ስለዚህ አጣርተው እስኪደርሱበት በትዕግስት ጠበቅሁ፡፡
ቁም ነገር፡- በአድራሻው አቶ አንተነህን ለማግኘት አልሞከርክም?
አበራ፡- ሞክሬያለሁ 2012 ከተመረቀ ይሄን ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል ብዬ አስብኩ፡፡ አጠናሁት ባለው ምርምር መግቢያ ላይ ያኖረው አድራሻ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እንደሆነ ይገልፃል፡፡

ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከመጣ ተመልሶም የሚሄደው ወደ እዚያው እንደሆነ ገመትኩ፡፡ ስለዚህ በቀጥታ ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ለዶ/ር ባዬ ፃፍኩላቸው፡ ፡ እንዲህ ዓይነት ችግር ተፈፅሟል፡፡ ማስረጃዎቹ እነዚህ ናቸው፡፡ የማጣራትና የምርመራው ሥራም በኖርዌይ ቶሮሞስ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ተግባር የፈፀመ አካዳሚ ዲስሆነሰት- ያሳየ ሰው ስለሆን ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመልሶ ተማሪዎች ለማስተማር የሞራል ብቃቱ የለውም ብዬ አምናለሁ፡ ፡ የእኔን ማስረጃ ተመልክታችሁ በማጣራት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ እንዳለባችሁ ማሳሰብን እወዳለሁ ብዬ ላኩላቸው፡፡ ፕሬዘዳንቱም ይህንን ነገር ይጣራ ብለው ለምክትላቸው መሩለት፡፡ ‹‹ይህ አቤቱታ የቀረበው በሀሰት ከሆነ ግን የራሳችንን እርምጃ እንወስዳለን›› ብለው ኢ-ሜይል አደረጉልኝ፡፡ በሚቀጥለው ቀን በሰጡኝ ምላሽ “ሰውየው እዚህ ዩኒቨርሲቲያችን ውስጥ የለም አንዳንድ ችግሮች ፈጥሮ ተሰውሯል የት እንዳለም ስለማናውቅ እርምጃ መውሰድ አልቻልንም፡፡ እኛም ሳናውቅ ነው ለትምህርት ወደ ኖርዌይ የሄደው›› የሚል ምላሽ ላኩልኝ፡፡
ቁም ነገር፡- ራሱን ማግኘቱስ?
አበራ፡- እሱን ለማግኘት ብዙ ሙከራ አላደረኩም፡፡ መፈለግ አለብኝ ብዬም አላምንም በእኔ እምነት ይህ ሰው ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ተማሪዎችን አስተምሮ ማብቃት ይችላል፤ አቅጣጫን የማሳየት፣ የመምራት፣ የመምከር እና ስለሐቅ የመናገር የሞራል ብቃት አለው ብዬ አላምንም፡፡ በማስተማሩም ሥራ መቀጠል የለበትም፡፡ ስለሆነም ለሚመለከታቸው ካመለከትኩ በኋላ እሱን በግል ማግኘቱ አስፈለጊነቱ ጎልቶ አልታየኝም፡፡
ቁም ነገር፡- የኖርዌይ ቶሮሞሶ (Tromso) ዩኒቨርሲቲ ውሳኔ ምን ሆነ?
አበራ፡- ዩኒቨርሲቲው አጣርቶ ግለሰቡ በቀጥታ ዘረፋ ላይ መገኘቱን አረጋግጦ ጥናቱን ሰረዘው፡፡ የሰጡትንም ዲግሪ እንዲነጠቅ ወሰነ፡፡ የምጠብቀው ውሳኔ ይህ ነበር ለእኔ ይህ ትልቅ ድል ነው፡፡ ሌሎችም የማይደረስባቸው መስሎአቸው የሌሎችን ልፋት ና ድካም የራሳቸው አድርገው ያልተገባ ክብርና ጥቅም ለማግኘት የሚሞክሩ ጥሩ ትምህርት ይሰጣቸዋል ብዬ አምናለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- የእኛስ ዩኒቨርሲቲዎች ይህንን ዓይነቱን ችግር ለመከላከል አንድ ዓይነት አገናኝ መስመር አያሻቸውም ትላለህ?
አበራ ፡- ጥናቶችን ‹‹በዌብ ሳይት›› ላይ ሲለቀቅ የቅርብ ጊዜ ባህል ነው፤ ብዙዎቹ እኮ ተጠንተው አሁንም መደርደሪያ ላይ ነው የሚገኙት፡ ፡ ከእነዚህ ላይ ገልበጥ ገልበጥ አድርገው የሚመረቁ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ይህ አንዱ የችግሩ አቅጣጫ ነው፡ ፡ ጥናትና ምርምር የማድረግ ትልቁ ግብ የእውቀት ክፍተትን መሙላት ነው፡፡ አየርላንድ እኔ በተማርኩበት የትምህርት ተቋም የምንፅፈውን Essay የምንልከው፡ ፡ በማንኛውም ኢ-ሜይል አድራሻ አይደለም፡፡ ለፕሮፌሰሮቻችን ነው የምንልከው ሙድል የሚባል መስመር አለ፡፡ ይህ መስመር የተመራማሪውን አዲስ ሃሳብና ከሌላ የወሰደውን፣ የጠቀሰውን አጣርቶ ይለያል፡፡ የዚህ ቴክኖሎጂ ዝርዝር መረጃ የለኝም ይሁን እንጂ የተማሪዎቻቸውን ጥናት የሚቀባበሉበት እና የሚያጣሩበት መንገድ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ “በኦን ላይን” የሚለቀቁ ጥናቶች ዘረፋውን ያስቀረዋል ባይባልም በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሰዋል ተብሎ ይታመናል፡፡ ትልቁ ነገር ግን አንድ ተመራማሪ በውስጡ ለራሱ እሴት ሊኖረው ይገባል፡፡ ለምን በዚህ ጉዳይ ላይ እመራመራለሁ? የምጨምረው ቁም ነገር አለን? በእውነቱና በሀቅ መመርመር አለብኝ ብሎ ሊገባበት ይገባል፡፡ ውጤቱም መጀመሪያ ያድክም እንጂ መጨረሻው ደስ ያሰኛል፡፡ እኔ ትልቅ ቦታ የምሰጠው ለዚህ ነው፡፡ በውስጤ “ቫሊዩ” ሳይኖር ወረቀቱን ብሰበስብ ምን ይጠቅመኛል፡፡ ትልቁ ነገር የትምህርት ጥራትን ለማምጣት በተማሪዎቻችን መንፈስ ውስጥ የእውቀትን እሴት በ ው ስ ጣ ቸ ው ማስረፅ ነው፡፡ ይህንን ለማድረግ ተ ቋ ማ ቱ ፣ ባ ለ ሙ ያ ዎ ቹ ፣ ዜጋው ፣ ወላጆችና ተማሪዎች እና መ ን ግ ሥ ት ትልቁ የቤት ሥራችንን መስራት ይኖርብናል፡፡
ቁም ነገር፡- አመሰግናለሁ አቶ አበራ ኃይለማርያም
አበራ ፡ – እኔም እግዜር ይስጥልኝ፡፡
No comments:
Post a Comment