Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, September 23, 2014

ወያኔ ከነዋይ ደበበ ጋር በስዊድን ያዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት በኪሳራ ተመታ፤ በጀርመንም ይቀጥላል

  • 6
    Share
በሃገረ ስዊድን በትናንትናው ዕለት ወያኔ ነዋይ ደበበን ተጋባዥ ድምፃዊ አድርጎ ያዘጋጀው የሙዚቃ ምሽት በታዳሚ እጦት ተመታ። ነዋይ ደበበ ከፍተኛ የሞራል ድቀት እንደደረሰበትም ጉዳዩን በቅርብ ይከታትሉ የነበሩ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘግበዋል። ነዋይ በጀርመንም እንዲሁ ኦክቶበር 4 ከፍተኛ ቦይኮት እንደሚገጥመው በዛው ያሉ ኢትዮጵያውያን አስታውቀዋል።
ወያኔ ከነዋይ ደበበ ጋር በስዊድን ያዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት በኪሳራ ተመታ፤ በጀርመንም ይቀጥላል
በውጭ ሃገር የሕወሓት መንግስትን እየደገፉ በሙዚቃ ኮንሰርትና በሌሎች የትያትር ዝግጅቶች ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚመጡ አርቲስቶችን ሕዝቡ ቦይኮት እየጠራባቸው ሲህን ከዚህ ቀደም በጀርመን ማዲንጎ አፈወርቅ በተመልካች ድርቅ ተመቶ ወደ ሃገር ቤት ተመልሷል። ሃመልማል አባተም በዋሽንግተን ዲሲ ለሲዲ ምርቃት ያዘጋጀችው ኮንሰርትም እንዲሁ በተመልካች ድርቅ የተመታ ሲሆን፤ ሸዋፈራው ደሳለኝ በበኩሉ በደረሰበት ከፍተኛ ተቃውሞ የኮሚዲ ዝግጅቱን ሳያቀርብ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።
“ነዋይን ነዋይ አሳሳተው” በሚል በተደጋጋሚ የሚተቸው ድምጻዊው በስዊድን የሕወሓት አስተዳደር በጠራው ኮንሰርት ላይ እንደሚገኝ ፍላየር ከተበተነ ጊዜ ጀምሮ በዚያው ሃገር የሚገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በመሰባሰብ የቦይኮት ፍላየሮችን በማዘጋጀት ሲቀስቀሱ ሰንብተዋል። በዚህም መሠረት ነዋይ ትናንት ምሽት የሕዝቡን ተቃውሞ በመፍራት ተደብቆ በመግባት ዝግጅቱን ያቀረበ ሲሆን መድረክ ላይ ሲወጣ የጠበቀው የሕዝብ ቁጥር ከ50 የማይበልጥ በመሆኑ እጅጉን ማፈሩን አብረውት የነበሩ የቅርብ ምንጮች ገልጸውልናል። በዚህ ኮንሰርት ላይ የተገኙት 50 የማይሞሉት ሰዎችም የኢምባሲ ሰራተኞች እና አንዳንድ ከኢትዮጵያ መንግስጥ ጥቅማትቅም የሚያገኙ ሶማሌዎች እንደሆኑ ምንጮቻችን ገልጸዋል። እንደነዚሁ የቅርብ ምንጮች ገለጻ ነዋይ በኮንሰርቱ ውስጥ የተጠበቀውን ያህል ሰው ባለመገኘቱ “ሕዝቡን ምን አድርገነው ነው፤ ስንጠራው የማይመጣው?” እስከማለት ደርሷል። ነዋይ በተደጋጋሚ በሆዱ ሳይሆን በሕሊናው እንዲያስብ ተመክሯል የሚሉት በስዊዲን የሚገኙት ኢትዮጵያውያን “ሕዝቡን ምን አድርገነው ነው ስንጠራው የማይመጣው?” ማለቱ በራሱ የአመለካከት ደረጃው የት ላይ እንዳለ ያሳያል ብለዋል።
በተመሳሳይ ዜና ነዋይ ደበበ በጀርመን ሃገር ኦክቶበር 4 የሙዚቃ ዝግጅት እንደሚያቀርብ የሰሙት ኢትዮጵያውያን ቦይኮት ለማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኙ ጨምሮ የደረሰን ዜና ያስረዳል።
ነዋይ ደበበ በቅርብ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የመጣ ጊዜ ለመለስ ዜናዊ የዘፈነውን “የሙሴ በትር” ዘፈን ‘ዝፈን ብለው ሰጥተውኝ እንጂ ትርጉሙ አልገባኝም ነበር፤ ከዘፈንኩት በኋላ ነው መሳሳቴን ያወቅኩት” ብሎ ለጓደኞቹ የነገራቸው ሲሆን ወዲያው ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ ደግሞ ተገልብጦ በተቃራኒው መገኘቱን የቅርብ ሙያ አጋሮቹ ይተቹታል።
ነዋይ የስዊድን ኮንሰርቱ ከመደረጉ በፊት በኢሳት ራድዮ ተቦርነ ያቀረበውን ዜና ለግንዛቤ እዚህ አምጥተነዋል፦
https://www.youtube.com/watch?v=TUvGs-3sJfg


No comments:

Post a Comment

wanted officials