በወያኔ ስር የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት፣ የወያኔ አገልጋይ ኢሕአዴግ፣የአፋኞችና የነፍሰ ገዳዮች ምሽግ- የወያኔ ደህንነት
ነዓምን ዘለቀ
ዋና ጸሃፊያችንና የትግል ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ
የንቅናቄአችን ዋና ጸሃፊና የትግል ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ትብብር በፋሽስታዊ ወያኔ አፋኞች እጅ መውደቅ ያስቆጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባሳየው ወገናዊነት ልባችን ተነክቷል። የአንዳርጋቸው መታሰር ይቆጨናል፤ እየደረሰበት ያለው ስቃይ ያንገበግበናል፤ የሱን አይነት ብርቱ፣ ቆራጥ፣ አስተዋይና ብቃት ያለው ታጋይ ትግሉ ማጣቱ ይጎዳናል:: አንዳርጋቸው በሳል የፖለቲካ ሰውና ቆራጥ የተግባር ታጋይ ብቻ አይደለም። በግል ለማታውቁት በበርካታ የእውቀት ዘርፎች በጥልቀት ያነበበ፤ ፍልስፍና፣ ሊትሬቸር፣ ሲኒማ የሚወድና ህሊናው በዕውቀት በከፍተኛ ደረጃ የበለፀገ ነው። የሰው ልጅ መከራ፣ በደልና ስቃይ እስከ አጥንቱ ይሰማዋል። ዱባይ ላይ ከአመት በፊት ስላገኛት ኢትዮያዊት የነገረኝ ሲቃ እየተናነቀው ነበር።ልጅቷ ሲያገኛት ያለማቋረጥ ታለቅሳለች፤ ምን እንደሆነች ቢጠይቃት ለመናገር ባትፈቅድም አጥበቆ ሲይዛት እንደተናገረችው፤ ተቀጥራ በምትሰራበት የቤቱ ባለቤት ሽማግሌ አረብና አራት ወንድ ልጆቹ በየገዜው ተራ በተራ ደፍረዋታል። የሚያስነባት ይህ ነበር። አንዳርጋቸው “የኢትዮጵያውያን መከራና ውርደት መቼ ነው የሚያበቃው” በሚል ነበር ሲቃ እየተናነቀው ያጫወተኝ።
አንዳርጋቸው የንዋይና የስልጣን ፍቅር የለበትም። ፍላጎቱ ያ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ወያኔ ከሰበሰባቸውና ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኙ የወያኔ ሎሌዎች የተሻለ ደረጃ ላይ ባገኘነው ነበር። በምንም መለኪያ በሱ ደረጃ ብቃት፣ ምሁራዊ ብስለትና ስብዕና የተላበሡ እንደሌሉባቸው ግልጽ ነው። አንዳርጋቸው የመረጠው የፍትሕ፣ የነጻነትና የእውነትን መንገድ ሲሆን እሱ የመረጠው ከህሊናው ጋር መኖርን ነው። ለዚህም ነው ስልጣን እና ገንዘብን ገፍቶ፣ የአውሮፓን ምቾት ትቶ፣ በርሃ ወርዶ አፈር ላይ እየተኛ በርካታ ታጋዮችን አስተምሮ ትግሉን ጠንካራ መሰረት ላይ የተከለው – ትግሉን መስመር አስይዞ ዛሬ በፋሺስቶች እጅ ቢወድቅም።
ፋሽስቶቹ ወያኔዎች በተለመደው ድንቁርናቸው ያቀዱትና የአለም አቀፍ ህግን ጥሰው የሄዱበት የብልግናና የውንብድና መንገድ እሱን በማፈን ነጻነትና ፍትህ የጠማውን የኢትዮጵያ ህዝብ አንገት እናስደፋለን፣ ቅስም እንሰብራለን፣ ታጋዮችና ትግሉን እናዳክማለን፣እናመክነዋለን ከሚል ስሌት ነበር። በተቃራኒው ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥም በውጭው አለም ከዳር ዳር በከፍተኛ ቁጣና ቁጭት እንዲንቀሳቀሱ እያደረገ፤ ለመራራ ትግል እንዲዘጋጁና ለመስዕዋትነት እንዲቆርጡ እያነሳሳ ይገኛል። <<እኔም አንዳርጋርጋቸው ጽጌ ነኝ>> በሚል በሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ትግሉንም ንቅናቄአችንንም እንዲቀላቀሉ እያደረገ ነው። ዛሬ ብዙ ሺዎች የአንዳርጋቸው ጽጌን ፈለግ ተከትለዋል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሚሊዮኖች የነጻነት፣ የእኩልነት፣ የፍትህ ጠበቆችና ታጋዮች ሆነው የፋሽስታዊውን የወያኔን ስርዓት በሁሉም መንገዶች እንደሚፋለሙ አፍታም ጥርጥር የለንም። በግንቦት 7 በኩል እልሃችን፣ ቁጭታችን፣ ጽናታችን፣ ቁርጠኝነታችን እጥፍ ድርብ እንዲሆን አድርጎናል። እኛም ግንባራችችንን ሳናጥፍ የተጀመረውን ትግል ከግብ ለማድረስ በቁርጠኝነት ተነስተናል። በዛሬው እለትና በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ንቅናቄያችን በመላው ዓለም በ27 ከተሞች ከሚያደርገው ህዝባዊ ስብስባዎች አንዱ በሆነው በአትላንታ ከተማ በመካከላችሁ የተገኘሁት ኢትዮጵያ ሀገራችንንና ህዝባችን የሚገኙበትን የምታውቁትን እጅግ አስከፊ ሁኔታ ለመደጋገም አይደለም።
የዛሬው ስብሰባ ዋና አላማና ትኩረት ትግሉ ወደ አንድ ሌላ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን በተመለከተ የጋራ ግንዛቤና የትግል አቅጣጫ እንዲኖረን ለመመካከር ነው ሲሆን፤ ሁሉም የዚህ ትግል ንቁ ተሳታፊና አባል እንዲሁም ደጋፊ በመሆን ምን አይነት ተግባራዊ የትግል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንደሚገባን ሁላችሁም ወስናችሁ እንድትንቀሳቀሱ ለማስገንዘብና ለልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችም የንቅናቄአችንን ጥሪ ለማቅረብ ነው።
ዘረኛውና ዘራፊው የወያኔ አርነት ትግራይ ስርዓት
የኢሕአዴግ/ኦህዴድ ከፍተኛ ካድሬና የካድሬዎች አሰልጣኝ የነበረውና በልዩ ልዩ ከፍተኛ መንግስታዊ ሃላፊነቶች ስርአቱን ያገለገለው አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር በኢሳት ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ያደርገውን ሰፊ ቃለ-ምልልስ የተከታተላችሁ ይመስለኛል። አቶ ኤርሚያስ ለገሰ በርካታ ሃቆች፣ መረጃዎችና ቁም ነገሮችን በአካተተበት “የመለስ ትሩፋቶች” በሚል ርእስ ያሳተመው የመጀመሪያ መጽሐፉ በቨርጂንያ በተመረቀበት ወቅት በስፍራው ተገኝቼ ኤርሚያስ ሲናገር የሰማሁዋቸውና ለዚህ ስብሰባ ፋይዳ አላቸው ብዬ የወስድኳቸውን እዚህ ለመጥቀስ እወዳለሁ፡፡
“ስርዓቱ የኔ ነው እንድትል፤ የኔነት ስሜት (Sense of Belongingness) እንዲሰማህ አያደርግም። የወያኔ/ህወሃት ዋና ተግባሩ ዘረፋ ነው”። “ኢህአዴግ በጥራትም፣ በጽናትም፣ በብቃትም እዚህ ግባ የሚባል ድርጅት አይደለም” የሚሉ አስተያየቶችን ሰንዝሮ ነበር።
የወያኔን አገዛዝ ምንነት አሁንም ድረስ በአግባቡ ላልተረዱ ብዙ መረጃዎችና ሃቆች ያካተተ መጽሀፍ ነው። ባለራዕይ ከሚሉት ከቀድሞ የወያኔ ቁንጮ ጀምሮ በቀለኞች፣ ቂመኞችና ዘረኞች መሆናቸውን ይበልጥ ተረድተንብታል። የአብዛኞቹን የወያኔ መሪዎችና አባላት እኩይነት፣ ዘራፊነት፣ አጭበርባሪነት፣ የስርዓቱን እጅግ የወረደና የዘቀጠ ምንነት፣የመሪዎቹን ርካሽነት፣ ጭካኔአቸውን፣ ለከት የሌለው ስግብግብነታቸውን፣ በስርዓቱ ውስጥ የነገሰውን አድርባይነት ገላልጦ አሳይቶናል። እጅግ የወረደ ስብዕና ባላቸው ጨካኝና ርካሽ ሰዎች እጅ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደወደቀችም ተገንዝበናል። ስርዓቱን ጥለው ከወጡት የቀድሞ ባለስልጣናት ያልሰማነውን በርካታ ውስጠ ድርጅታዊ ምስጢሮችን ያካተተ ትልቅ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ታሪካዊ ሰነድ ጭምር በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ነው የሚል እምነት አለኝ።
እነዚህን ላለፉት በርካታ የትግል አመታት ካጠራቀምናቸው መረጃዎችና ሃቆች ጋር ስንደምራቸው የዚህ ዘረኛና ለከት የለሽ ስግብግብ የወያኔ አገዛዝ ማንነት መፈተሽ የሚገባው በይፋ (officialy) ባስቀመጠውና በብልጣ ብልጥነት በሚነግድባቸው – አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ ልማታዊ መንግስት፣ የትራንስፎርሜሽን እድገት ወዘተ – ርዕዮቱ ሳይሆን በተግባር በሚሰራበት (Operating) ርዕዮት ሊሆን ይገባዋል፤ ይህም ተግባራዊ ርዕዮት ዘረኝነትን መሰረት ያደረገ ወያኔዎች የተያያዙት መንግስታዊ ዘረፋ ነው። ወደ ስልጣን እስኪመጡ ከደርግ/ኢሰፓ ጋር በሚታገሉበት ወቅት በጠባብ ብሄረተኝነትና በዘረኝነት የታጀለ ቢሆንም፣ ቢያንስ በወቅቱ አንግበውት የነበረው ፍትህ፣ እኩልነት፣ የብሄር ብሄረሰቦች መብት ወዘተ የሚሉ ነበሩት። ዛሬ ግን ትርጉም አልባ መፈክሮች መሆናቸውን የወያኔዎች 23 ዓመታት ተግባሮቻቸውና አድራጎቶቻቸው በይፋ ይመሰክሩባቸዋል።
የፋሽስቱ ወያኔ ዘረኝነት ከህመም ወደ ነቀርሳ (Cancer) የተለወጠ መሆኑ ግልጽ ነው። ከ23 ዓመታት በኋላም የመከላከያ ሰራዊቱን ዕዝ ወሳኝና ቁልፍ ቦታዎች ከላይ እስከታች 95 በመቶ፤ የደህንነቱ መዋቅሩም 90 በመቶ እንዲሁም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ 50 በመቶ ኤፌርት የሚባለው የህወሃት ግዙፍ ኩባንያዎች ስብስብ (Conglomerate) ተቆጣጥሯል። የህወሃት አባላትም በቤተሰብ፣ በዘመድ-አዝማድ የተያያዙ በሰፊው የትግራይ ህዝብ ስም የሚነግዱ የትግርኛ ቋንቋተናጋሪዎች ሁሉንም በበላይነት ይዘዋል። ይህ አዲስ ዘረናና ዘርራፊ ገዥ ቡድን (oligarchy) የዳበረበት፣ ፍጹም የሆንር ኢፍትሃዊ የስልጣን፣ የጥቅም፣ የስራ፣ የትምህርት፤ የኢኮኖሚ ወዘተ የነገሱበት፤ አድሎ የተንሰራፋበት መሆኑን የምታውቁትና የኢትዮጵያ ህዝብም የሚኖርበት ሃቅ ነው ።
አሸባሪው የወያኔ አገዛዝ በመጠነ ሰፊ ቅራኔዎች ተቀስፎ የተያዘ፣ ደካማና ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ የገባ ስርዓት ነው። መሪዎች እርስ በርስ የማይተማመኑ፣ የጎሪጥ የሚተያዩ፣ የሚናናቁ ስለመሆናቸው ንቅናቄያችን በርካታ መረጃዎች አሉት። ለስልጣን ያላቸው ስግብግብነትና ዘራፊነታቸው ስላስተሳሰራቸውና ስላያያዛቸው ብቻ በጉልበት፣ በአፈና በሽብር የሚገዙ ናቸው። ራሱ ባወጣው ህገ መንግስት ውስጥ የደነገጋቸውን ዩንቨርሳል ዲክላሬችን ኦፍ ሁማን ራይትስና ሌሎች ህጎችን ሁሉ በየእለቱ እየረገጠ የቀጠለ ስርዓት ነው። በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት (Legitimacy) የሌለው መሆኑን የስርዓቱ መሪዎች ያውቁታል። የዚህን ስርዓት ደካማነትና የፈጠራቸውን ዘርፈ ብዙ ቅራኔዎች የሚመሰክሩት ስርዓቱን ጥለው የሚወጡት ብቻ አይደሉም፤ በቅርብ ጊዜ አዲሱ ለገሰ የሚባለው መሪ ካድሬ የፃፈውንና በኢሳት የቀረበውን ብዙዎቻችሁ የሰማችሁ ይመስለኛል። ስርዓቱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደወደቀ ከፍተኛ የሆነ የአመራር እጦትና በርካታ ሌሎች ችግሮች እንዳሉበት፤ ከግንቦት 7ና ከኦነግ ጋር የሚሰሩ የብአዴንና የኦህዴድ አመራሮች እንዳሉ ወዘተ አዲሱ ለገሰ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪዎች ባቀረበው ሪፖርት ዘርዝሯል። ይህን ተከትሎም በመላው አገሪቱ የሚገኙ 350ሺህ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ኢህአዴግ የሚባለው የወያኔ መገልገያ ድርጅት አባል ለማድረግ አስገዳጅ ስልጠና መጀመሩን ታውቃላችሁ፡፡
የወያኔ/ህወአት አገልጋይና መሳሪያ የሆነው ኢሕአዴግ
ወያኔዎች ኢህአዴግ በሚባለው ጭንብላቸውና መሳሪያቸው ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት አሁንም ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አስገድዶ የፓርቲ አባል የማድረጉ ሂደት እድሜያቸውን የሚያራዝም የሚያድን እንደማይሆን እነሱን ከተኩት ከደርግ/ኢሰፓ ስርዓት ትምህርት ለመወስድ ያልቻሉ የአዕምሮ ስንኩላን ስብስብ መሆኑን ዳግም እያረጋገጡ ነው። እነሱ የተኩት ኢሰፓ ሁሉም የህብረተስብ ክፍል ሁሉም ዜጋ በግድ አባል ለማድረግ የሞከረ፣ በግለስብና በህዝብ ላይ ፍጹማዊ አገዛዝ (Totalitarian) ለመዘርጋት ሞክሮ ያልተሳካለት፡ ለውድቀቱም አንዱ መንስኤ አሁን ወያኔ በማድረግ ላይ ያለውን በዜጎችና በህዝብ ላይ ፍላጎቱን በማስገደድ፤ በጉልበት መጫኑ ነበር። በኢሰፓ ርዕዮት አምነው ከልብም ተቀብለው ለፓርቲው ህልውና የታገሉና መስዋዕት የሆኑት ስንቶቹ እንደሆኑ በዚያች ቀውጢ ሰዓት የኢትዮጵያ ህዝብም ራሳቸው ወያኔዎችም የሚያውቁት ነው፡፡
ዜጎችን በማስገደድ የስልጣናቸውን እድሜ ለማራዘም የስርዓቱ አገልጋይና የአፈና መሳሪያ ለማድረግ የሚደረገው ይህ ሂደት የፋሽስቱን የወያኔን ስርዓት እድሜ የሚያራዝም አይሆንም። ታሪክ አንዳንዴ ራሱን ስለሚደግም የዚህንም ሂደት ውጤት የምናየው ይሆናል፡፡ ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥ ለመላላጥ ከመሆን እንደማያልፍ ጥርጥር የለንም፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፓርቲ አባላት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰላዮችና አፋኞች አምባገነናዊ ስርዓቶችን – ከሆስኒሙባርክ እስከ ሙአመር ጋዳፊ – ሊያድኗቸው እንዳልቻሉ የቅርብ ጊዜ ምሳሌዎች ናቸው።
በስርዓቱ ውስጥ የሚገኙ ኢህአዴግ የሚባለው የህወሃት መሳሪያ የሆነው ድርጅት አባላት አብዛኞቹ ለኑሮ ዋስትና፣ለእለት ጉርስ፣ የስራና የትምህርት እድል ለማግኘት ወዘተ ሲሉ አባል እንደሆኑ እናውቃለን። በኢትዮጵያዊነታቸው በዜግነታቸው ማግኘትና መጎናጸፍ የሚገባቸውን መብቶቻቸውን ለማግኘት ባለመቻላቸውና በመገደዳቸው እንደሆነ ግልጽ ነው። ለሆዳቸው ሳይሆን ለህሊናቸው ጭምር ተጨንቆ ማሰቢያው ግዜው አሁን ነው፤ ጊዜው ሳይመሽ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መወገን እንላለን ።
ይህን ስርአት ከውስጡ እንዲታገሉት፤ የስርአቱ መናጆና ባይተዋር ለሆኑት ብዙሃኑ የኢሃአዴግ አባላት ጥሪያችንን እናቀርብላቸዋለን። የወያኔ ስርአት ዘረኛና ዘራፊ፤ የህዝብን መብቶች አፋኝ ስርዓት መሆኑን ከእነሱ በላይ እማኝ እንደሌለ ያውቁታል። ጥቂት ሺዎች የሚመዘብሯትና የሚንደላቀቁባት በአፈና በሽብር የሚገዟት ኢትዮጵያ እንደሆነች እነዚሁ ብዙሃን የኢህአዴግ አባላት ያዉቁታል። የፋሽስቱ ወያኔ ግብዓተ መሬት ሁሉንም ጠራርጎ ወደ ክፉኛ ወድቀትና አይቀሬው ግብዓተ መሬቱ ከመሄዱ በፊት ከህሊና ጋር ተነጋግሮ ከአፋኞች፣ ገዳዮችና ዘራፊዎች ጋር አብሮ መቆም ሳይሆን በልዩ ልዩ መንገዶች የዚህን አሸባሪና የዘርኝነት ነቀርሳ የተጠናወተው ስርአት ወድቀት እንድታፋጥኑ፤ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንድትቆሙ ጥሪ እናቀርባለን። በታሪክ ሆነ በህግም ፊት ከተጠያቂነት ለመዳን የሚቻለው ለዚህ ስርዓት እድሜ የማራዘም ተግባራትን በመፈጸም ሳይሆን የስርዓቱን እድሜ የሚያሳጥር ተግባራትን በማድረግ ብቻ ነው እንላለን።
የኢህአዴግ የሚባለው የህወሃት መጠቀሚያ ድርጅትም ሆነ የራሱ የፋሽስቱ የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣኖችና ከፍተኛ ጄነራሎች ዛሬ የዘረፉትን የህዝብ ገንዘብ በምዕራብ ሀገሮች ንብረት እየገዙበትና ወደ ውጭ ባንኮች ገንዘብ እያሸሹ እንደሆነ በየጊዜው የሚደርሱን በርካታ መረጃዎች አሉ። ቤተስቦቻቸውንም ወደ ውጭ የሚልኩ ጥቂቶች አይደሉም። እንድ እግራቸው አገር ውስጥ ሌላው ወደ ውጭ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ብዙሃኑ የስርአቱ ተከታዮችና ደጋፊዎች ሊያውቁት ይገባል።
የአፋኞችና የገዳዮች ምሽግ -የወያኔ ደህንነት
የፋሽስቱ አገዝዝ ያለፈውን የደርግ/ኢሰፓ መንግስትና በታሪክም ያለፉትን የኢትዮጵያ አገዛዞችን ኢ-ፍትሃዊ፣ጨቋኝ፣ ሰው በላ፣ ወዘተ እያለ ሲከስ፣ ሲያወግዝ፣ ሲያሳጣ የነበረው ሰቆቃ ፈጻሚ ኢ-ሰብአዊ እያለ እንደነበር ሲታወስ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ታሪክ አቻ የማይገኝለት በሰብዓዊ ፍጡር ላይ ግፍ የሚሰራ፣ በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ ሰቆቃ ፈጻሚ፣ አፋኝና ገዳይ ራሱ ወያኔ ህወሃት ነው::
ዛሬ ማዕከላዊ ምርመራ ሌሎችም የወያኔ የደህንነትና የፓሊስ ምርመራ ቦታዎች የምድር ሲኦል ሆነዋል። ሰው ከሰው መፈጠሩን የሚያማርርባቸው ስፍራዎች ናቸው። “ሞት ምርጫ ሆና ለሚሰቃዩት የማይቀርብበት” ከስቃይ ብዛት አዕምሮአቸውን የሚስቱበት ሲሆን፣ እጅግ ዘግናኝና አረመኔያዊ ሰቆቃዎች ሳቢያ በርካታ ኢትዮጵያውያን እዚያው በሰቆቃው ወቅት ህይወታቸው ያልፋል፤ ወንድ፣ ሴት፣ ሽማግሌ፣ ለጋ ወጣት ላይ ልዩነት አይደረግም፤ሁሉም ስቃይ ይቀበላል፤ በፍርድ ስም ይሸፈጣል። ዳኛው ከሰቆቃ ፈጻሚው ጋር አብሮ ንጹሁን ዜጋ ያጠቃል:: በወያኔ፤ ኢትዮጵያ ሰብዕናተዋርዷል፣ ሰብዓዊ ፍጡር ረክሷል:: የግፍ ጽዋ ሞልቶ ፈሷል!!
ዛሬ በየለቱ በማዕከላዊና በደህንነቱ መስራያ ቤት የአፈና ቪላ ቤቶች፣ በየክፍለ ሀገር እስር ቤቶች ለመስማት እንኳን የሚዘገንኑ ሰቆቃዎች በኢትዮጵያውያን ላይ ይፈጸማሉ። አካላቶቻቸው ይተለተላሉ፣ ይጎድላ፣ ይደማሉ፣ ይጮሃሉ። የትውልድ ብሄራቸው እየተጠቀሰ ይሰደባሉ፣ ሰብእናቸው በህወሃት መርማሪዎች ደጋግሞ ይዋረዳል፣ ፍርድቤት ሳይደርሱ ዓመታት ይማቅቃሉ፣ ለፍርድ ቤት ተብየው የወያኔ ቧልት ቢቀርቡም ባላመኑበት ባልሰጡት ቃል ይቀጣሉ።
ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ “ሞቶ መነሳት” በሚል ርዕስ የጻፈውን ብዙ ኢትዮጵያዊያን እንዳነበቡ እገምታለሁ። ይህንኑ አስመልክቶ በአየር ሃይል በተመደቡ የወያኔ ደህንነቶች ተወስዶ በጨለማ ቤት ተወርውሮ ለሁለት ዓመት ያህል የደረሰበትን ስቃይና ግፍ አስመልክቶ ለኢሳትና ለሌሎች ሚዲያዎች የሰጠውን ቃለ ምልልስ ብዙ ኢትዮጵያውያን ተከታትለውታል የሚል እምነት አለኝ።
የወያኔ ታጣቂዎች በህዝባችን ላይ የሚፈጽሙትን ግድያ፣ ሰቆቃ፣ ግፍና፣ ዜጎችን የማዋረድ ተግባራት ከዜጎች አንደበት እጅግ ጥቂቱን ለማቅረብ እወዳለሁ። ጥቂቶቹን እንስማ፡-
- አቶ ጋስ – የአፋር ሰባዓዊ መብት በአፋር ውስጥ የስምንት ልጆች አባት የሆኑ ግለሰብ፣< -SOBE&feature=youtu.be”>https://www.youtube.com/watch?v=0IYVtJ-SOBE&feature=youtu.be
- ድምጻችን ይሰማ የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በመብት እንቅስቃሴ ወቅት በቅርብ ሳምንት የወያኔ ፖሊሶችና ደህንነቶች ድብደባ፤ ስቃይና ውርደት ከደረሰባቸው ሴቶች አንዱዋ የምትለውን እንስማ፣
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34355
- በራሱ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ወያኔዎች በተለመደ ጭካኔያቸው በምርጫ 97 ያደረሱበትን የጻፈውንና ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በኢሳት ያቀረበውን በአጭሩ እናድምጥ፣
- በቅርብ ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚባለው የፋሽስቱ የወያኔ አገልጋይ ለአንድ ሚዲያ ነኝ ለሚል ግለሰብ በሰጠው ቃለ ምልልስ እናድምጥ
- ይህን አሳዛኝ ሰቆቃ በመአከላዊና በሌሎች ሰቆቃ መፈጸሚያ ቤቶች ወያኒዎች ዘግናኝና አሰቃቂ ሰቆቃ ከፈጸሙባቸው መካከል ለምሳሌነት ስለበደሎቻቸው ያልዋቸውን ደግሞ ቀጥሎ እንመልከት፡-“ዓይን ተሸፍኖ፣ እጅ በካቴና ታስሮ መደብደብ፣ ውስጥ እግርን መግረፍ፣ የአውራጣት ጥፍር ማውለቅ፣ ቁስሉን መርገጥ፣ ጆሮንበጥፊ መምታት፤ አንዱ ከፊት ሌላው ከኋላ ሆኖ ጀርባን፣ ታፋን፣ መቀመጫን፣ ወገብ፣ ትከሻን መደብደብ። ስደክም ግድግዳአስደግፈው መደብደብ፣ ስደክም በላዬ ውሃ እያፈሰሱ መደብደብ፤ ሰውነት እስኪቆስል ድረስ መቀመጥ መነሳት ፤እስኪዝለፈለፍስፖርት መስራት፣ ሲያቅተው፣ ሲወድቅ መርገጥ፤መጫሚያ፣ ታፋን፣ የእጅ ጣቶችን፣ እራስን መቀጥቀጥ፤ የውስጥ ሱሬ ሳይቀርአስወልቀው ብልት መቀጥቀጥ፤ መሬት ሲዘረር አንገት ላይ በጫማ ቆሞ ማሰቃየት፤ ጡት ሳይቀር በኤለትሪክ ገመድ መግረፍ፤ውስጥ እግር፣ መቀመጫ፣ ጀርባ መግረፍ፤ እጅ በካቴና አስረው በዚያ ግድግዳ ላይ መስቀል፤ በአካል ላይ ከፍተኛ ድብደባ፣ለረጅም ሰዓት ዘቅዝቆ መሰቀል፣ ሲጮህ አፍ በጨርቅ መጠቅጠቅ፤ ክብር የሚነካ ስድብ፣ ለ45 ቀናት ማታ ማታ ድብደባ ለረጅምሰዓት፤ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ሲታሰር ፍርድ ቤት አልቀረበም፤ ለስድስት ወር እጅና እግሩ በእግር ብረት ማሰር፤ በድብደባየግራ የዘር ፍሬው (ብልቱ) ሟሙቶ ጠፍቷል፤ በኤሌትሪክ ሰውነቱ ተጠብሷል፤ ለ48 ሰዓታት ምግብና ውሃ መከልከል፤ ለቀናት እንቅልፍ መከልከል፤ በአንድ እግር ለረጅም ሰዓታት ማስቆም” ። በቅርብ ሳምንታት የሙስሊም ሴቶች ይህ ነው በማይባል ጭካኔና አረመኔያዊ መንገድ መገረፋቸው፣ልብሳቸው ወልቆ እርቃናቸውን እንዲሆኑ መደረጉ፣ የቁርዓን እና የመሳሰሉት እምነት ተኮር መገለጫዎች በታሰሩባቸው የፖሊስ ጣቢያዎች በሙሉ እንዲቃጠሉ ተደርገዋል።ሲለቀቁም እራቁታቸውን ሌሊት ሰው በማያያቸው ሰዓት ተፈትተው ወደሚሄዱበት እንዲሄዱ መደረጉ እውነታ ነው።ከላይ የተዘረዘሩን አሰቃቂ ጭካኔዊ ተግባራትን፣ ሰቆቃን፣ አፈናን ግድያን እንመራዋለን በሚሉት ህዝብ ላይ የሚፈጽሙ “ሰውን አንደበድብም፣ አናሰቃይም፣ አንገርፍም” በማለት እንደለመዱት ይክዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚባለው የፋሽስቱ የወያኔ አገልጋይ ግለሰብ በሰጠው ቃለ ምልልስ፣ የወያኔው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም በሌላ ቃለ ምልልስ የደገመው ይህንኑ አይናችንን ግንባር ያድርገው የሚል ክህደትና የተለምዶ ሽፍጦችን ነው።ከሶስት ሳምንታት በፊት በዋሽንግተን ዲሲ በአንዳንዶቹ የፋሽስቱ ወያኔ ሎሌዎችና ተላላኪዎች ላይ በተቆጡ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የደረሰባቸውን ማሸማቀቅ፣ ውግዘትና፣ ማስነወር “ብልግና” ተደረገ “ነውር” ተፈጸመ በማለት በዚያ ሰሞን እነሱና የስርዓቱ ተጠቃሚዎች በሆኑ ሚዲያዎች ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ተደምጠዋል። ሰዎች የሚከበሩት ሌላውን ሰው ሲያከብሩ፣ በጎ ሲሰሩ፣ መልካም ሲሰሩ፣ አርአያዊ ስነ ምግባር ሲኖራቸው ነው። ጨዋነት ያልተጻፈ ማህበራዊ ፕሮቶኮል ነው። የሚሰራው ጨዋዎች ባሉበት ማህበረስብ ሁሉ አብዛኛው ማህበረሰብ በጋራ የሚገዛበት የሚመራበት ማህበራዊ (Social Norm and etiquette ) ሲሆን ነው። ያለ መቀባበል (Reciprocity) ጨዋነት የሚሰራ ሊሆን አይችልም።የወያኔ ጉዶች በአንጻሩ ምንም ሃፍረት ያልተፈጠረባቸው ይሉኝታና ሞራል የማያውቁ ኢትዮጵያና ህዝቡዋን ያዋረዱ፣ ቤተ ክርስትያንና መስጊዶችን ሳይቀር የሚያረክሱ ተግባራትን የሚፈጽሙ፣ ቅዱሳን መጽሃፍትን የሚያዋርዱ የሚያረክሱ፣የውንብድና የሽብር ተግባራት የሚፈጽሙ፣ በንጹሃን ዜጎች ላይ ሰቆቃ እየፈጸሙ የዜጎችን ቅስም መስበር ምንም የማይመስላቸው (Saddists) እጃቸው በደም ተጨማልቆ በጉልበት እየገዙ ያለምንም ይሉኛታ፤ በለየለት አይናአውጣነት ስለ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ሊሰብኩ ይዳዳቸዋል። የወያኔ ፋሽስቶችና ሎሌዎቻቸው በዘረኝነት፣ በዘረፋ፣ በአፈና ቅስም እየስበሩና እያዋረዱ፤ ፍርሃትን በህብረተስቡ ውስጥ ስላነገሱ፣ በህዝብ እንዲከበሩ እንዲታፈሩ የሚከጅሉ የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ አድርቅ የሚለው ብሂል ፈጽሞ የማይገልጻቸው እንደሆኑ በድጋሚ አረጋግጠውልናል።በዋሽንግተን ዲሲ ወጣት ታጋዮች እንደተደረገው በመላው አለም የወያኔ አገዛዝ መሪዎች የነሱ ሎሌ ባለስልጣኖቻቸው በተገኙበት ሀገር ከተማና ቦታ ሁሉ ማስነወር ማሸማቀቅ፤ ስላምና እረፍት መንሳት፣ የእግር ረመጥ መሆን በመላው ዓለም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት የትግላችን አካል ነው። ይህ ስልት የህዝባዊ እምቢተኝነት አካል ነው። የአልገዛም፣ አናከብርህም፣ አንቀበልህም፣ ወግድ የማለት የሰላማዊ አመጽ አካል ነው። በዴሞክራሲያዊ ሃገሮች በህግ የበላይነት ማቀፍ ውስጥ ለምንገኝ ሁሉ የመታገያ መሳሪያ በመሆኑ ይህን የትግል ስልት ተግባራዊ እንድናደርግ በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጥሪያችንን እናድሳለን ።እነዚህ ወደ ምእራብ ሀገሮች የሚመጡ ባልስልጣኖቹም ሆኑ በእነሱ መሪነትና ውሳኔ ሰጪነት ባለፉት 23 ዓመታት በህዝብ ላይ ወንጀል የፈጸሙ፤ ስቆቃ፤ ግድያ፤ አፈና ጭካኔያዊ ተግባራትን በንጹሃን ዜጎች ላይ ያስፈጸሙና የፈጸሙ የደህንነት፣የፌደራል ፖሊስ፣ የልዩ ህይል፣ የክልል ፖሊስና በተዋረድ ያሉ የዚህ ስርአት የአፈና መዋቅሮች የወያኔ የስልጣን ምሰሶዎች በመሆናቸው በሁሉም መንገድ መታገልና ለፈጸሙት መጠነ ሰፊ ወንጀሎች በህግ ፊት እንዲቀርቡ ዝግጅቶችን ማድረግ ሌላው አንገብጋቢ የትግል ዘርፍ ነው።የወያኔ የብሄራዊ ደህንነት የሚባለው የአፋኞች፣ የሰቆቃ ፈጻሚዎችና፣ የገዳዮች ምሽግ በሚመለከት በደርግ ዘመን በደህንነትና በፓሊስ ውስጥ ያገለግሉ የትግርኛ ተናጋሪዎች ተመርጠው እስካሁን በቁልፍ ቦታዎች ላይ እንደሚገኙበትማ እነማን እንደሆኑ እናውቃለን፤ ባዶ ስድስት በሚባለው የወያኔ እስር ቤት ጀምሮ ግፍ፣ ግድያና ሰቆቃ የፈጸሙ የወያኔ ህወሃት አባላት ፈላጭ ቆራጭ እንደሆኑበት በማእከላዊ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ በሚገኙ ሰቆቃ መፈጸሚያ ቪላ ቤቶች (Safe Houses) የት የት እንደሚገኙ፤ ምን ዓይነት ወንጀልች ሲፈጸሙ እንደነበር፤ በልዩ ልዩ የሀገራችን አካባቢዎች ትግራይን ጨምሮ ተመሳሳይ ድብቅ የአፈና ቦታዎች በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን የገደሉ፣ ያስገደሉ፣ ያሳፈኑ፣ ያፈኑ፤ ሰቆቃ የፈጸሙ እነማን እንደሆኑ ንቅናቄያችን መረጃዎች አሉት። በጎረቤት ሀገሮች በኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ እንዲሁም በቅርቡ የመን ድረስ ድንበር ዘለውና ባህር አቋርጠው ግድያ አፈና ያቀነባበሩ የፈጸሙት እነማን እንደሆኑ ከተለያዩ አቅጣጫዎች በርካታ መረጃዎች ለንቅናቄያችን እየደረሱ ናቸው።እነዚህን አፋኞችና ገዳዮች እንዲሁም ውሳኔ ሰጪ አለቆቻቸውን ለፍርድ ለማቅረብ የሚቻልበትን መንገዶች በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና የህግ ባለሙያዎች ነዋሪ የሆኑባቸውን ሀገሮች ህጎች በመፈተሽ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጸሙ የጦር ወንጀሎች፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል፣ የጅምላ ግድያ፣ ከፍርድ ቤት ውጭ የተደረጉ ግዳያዎች፣ አፈናዎች፣ ሰቆቃዎች ተጠያቂ የሚሆኑ የወያኔ ውሳኔ ሰጪዎች፣ ውሳኔ አስፈጻሚና ፈጻሚዎችን ፍርድ ፊት እንዲቀርቡ በተደራጀ መንገድ መንቀሳቀስ አንዱ የወቅቱ ዓብይ የትግል ተግባር ነው። በስዊድን የተጀመራውን የወያኔን ወንጀለኞች ወደ ፍርድ የማቅረብ ሂደት በሌሎችም የአውሮፓ ሀገሮች እንዲሁም በአሜሪካና በካናዳ መጀመር የትግሉ አንዱ ዘርፍ ነው።በኢትዮጵያ ውስጥ ቤተሰብ ዘመድ በወያኔ የታፈኑባችሁ፣ የደረሱበትን የማታውቁ፣ በወያኔ አፋኞች መገደላቸው ማስረጃ ያላችሁ፣ የደህንነትና የፖሊስ አፋኞች፣ ሰቆቃ ፈጻሚዎች፣ ገዳዮችን ማንነት መረጃዎችን የምታውቁ፣ ለዚሁ ተግባር ለሚቋቋሙ ግበረ ሀይሎች ስለወንጀለኞቹ ዝርዝር መረጃ በመሰብሰብ እንድትልኩ ጥሪ እናቀርባለን። ወንጀለኞች በተለይም በዴሞክራሲያዊ ምዕራብ ሀገሮች መሽሸጊያ እንዳያገኙ በውጭ ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ስለእነዚህ ወንጀለኞች የምታገኙትን መረጃዎች ሁሉ እንድታቀብሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።ቀደም ሲል ፋሽስታዊው የወያኔ ዘረኛ ስርአት ደካማና በቅራኔዎች ተቀስፎ የተያዘ ፤ ውስጡ የበሰበሰ፤ የነተበ ነው ብለናል። ካልገፋነው ግን ሊወድቅ አይችልም። እየተንፏቀቀና እየተንገዳገደ እንዳይቀጥል ገፍቶ መጣል ያስፈልጋል። ወያኔን በሥልጣን ላይ ያቆየውን የመከላከያና የስለላ ተቋማቱን ማዳከም አለብን። መስዋትነት ለመክፈል የተዘጋጁ ሃይሎችን መቀላቀል የሚችል ዜጋ ሁሉ እንዲቀላቀል ንቅናቄያችን ጥሪ ያቀርባል። በደጀን የተሰለፈው ኃይል ደግሞ የዘማቹን ስንቅ በማዘጋጀት በገንዘቡ፣ በጉልበቱ፣ በመረጃ ይተባበር። የተቆጣ፣ ጥቃት፣ ውርደት፣ ግፍ የመረረው ሁሉ ለነፃነቱ ግድ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የስነ ልቦና ዝግጅት ያድርግ። ከወያኔ ሰላዮች ራሱን ተከላክሎ በያለበት በጥብቅ ከሚያምናቸው ጋር በመሆን በየአካባቢው በቡድን በቡድን ይደራጅ፤ የወያኔ ቀንደኛ ሹሞችና ወንጀለኞችን ይሰልል፤ መረጃዎችን ለንቅናቄችን በዘዴ እንዲልክ ጥሪ እናደርጋለን።በወያኔ ስር የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊትዘረኛውና እና ፋሽስቱ ወያኔ አርነት ትግራይ በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚያደርሰው በደል፣ ግፍና ዘረኝነት ሌላው ገፈት ቀማሽ በፋሽስቱ ወያኔአባል በሆኑ የጦር መኮንኖች እዝና ቁጥጥር (Command and Control) ተወጥሮ የተያዘው ከኢትዮጵያ ህዝብ አብራክ የወጣው ከአማራ፣ ከኦሮሞ፣ ከደቡብ ህዝቦች፣ ከአፋር፣ ከጋምቤላ፣ ከሌሎች ብሄር ቤሄረሰቦች የተመለመለው በታችኛው እርከን ላይ የሚገኘው ሰራዊት ነው።ይህ 5ኛና 6ኛ ክፍል ባልጨረሱ የወያኔ መኮንኖች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተሰንጎ የተያዘ ሰራዊት ዘርፈ ብዙ በሆኑ ችግሮችና ቅራኔዎች እንደተወጠረ ከበቂ በላይ መረጃዎች አሉ። ኢትዮጵያ ስትዘረፍ፣ ወገኖቹ ሲፈናቀሉ፣ ወንድምና እህቶችህ ሲሰደዱ ይህ ስራዊት የሚመለከት ነው። ከላይ ከዋናው ኤታማጆር ጀምሮ ዕዞች፣ ክፍለ ጦሮች፣ ብርጌዶች፣ ሬጅመንቶች፣ ሻለቃ፣ ሻምበል እስከ ጋንታና እስከ ታች ጓድ ድረስ የፋሽስቱ ህወሃት አባላት በበላይነት የያዙት ይህን ያገጠጠ ዘረኝነት በየእለቱ የሚኖርበት በመሆኑ ሰራዊቱ ያውቀዋል። በችሎታ በአገልግሎትና በብቃት ሳይሆን በዘረኝነት የተጫኑበት እንደሆነ ይህ ሰራዊት በሚገባ ያውቃል። ይህ ሰራዊት ከስንቁ፣ ከአልባሳቱ፣ ከትጥቁ ጭምር እየዘረፉና እያጭበረበሩ በመነገድ እነዚህ የወያኔ አርነት ትግራይ አባላት በሆኑ አዛዦችና ጥቂት ተባባሪ ሎሌዎቻቸው እንዲከብሩም ያውቀዋል፡፡ 90 ከመቶ የሚደርሱት ከፍተኛዎቹ የህወሃት ጀነራሎች የዋና መምሪያ፣ የዕዝ፣ የልዩ ልዩ መምሪያዎች፣ የክፍለ ጦርና ከዚያም ዝቅ ብለው በተዋረድ የሚገኙ ቈልፍና ወሳኝ ቦታዎች ላይ በኃላፊነት የተቀመጡት የወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት፣ እውቀት፣ የአመራር ብቃት፣ ልምድ ለ21ኛ ክፍለ ዘመን ዘመናዊ መደበኛ (የሽምቅ ተዋጊ ሃይል ያልሆነ ማለት ነው) ሰራዊት እዝና ቁጥጥር (Command and Control) በምንም መለኪያ የማይመጥኑ ምናልባትም ለዚህ እጅግ አሳፋሪ ሁኔታ ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ሀገር እንድሆነች ከታች ያለው ከታች የሚገኘው ብዙሃኑ የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ሊገነዘቡ ይገባል።የፋሽስቱ ወያኔ ታማኝ ጀነራል መኮንኖች አብዛኞቹ ነጋዴዎች፤ ሙሰኞች፤ ዘራፊዎች እንደሆኑ፤ ባለብዙ ፎቅ ህንጻዎች ባለንብረቶች እንደሆኑ፤ ልዩ ልዩ ሃብቶችን እንዳጋበሱ፤ ወደ ወጭ ሀገሮችም ገንዘብ እንደሚያሸሹ፤ ቤተስቦቻቸውንም እንደሚያሸሹ ይህ ሰራዊት በሚገባ ያውቀዋል። በአንጻሩ የተበላሸ ስንቅ እየመገቡት፤ በሰበብ አስባቡደሞዙን እየቆረጡ በችግር ይቀጡታል። የደሞዝ፣ የአልባሳት፣ የምግብ አስከፊ ሁኔታዎችን አስመልክቶ ጥያቄ ያነሱ የጦሩ አባላት ከልዩ ልዩ ግንባሮች ታፍነው የጠፉ፤ እስከአሁንም ድረስ የደረሱበት እንደማይታወቅ ሰራዊቱ ስለሚኖርበት የሚታዘበው፤ በልዩ ልዩ ወቅቶች ሰራዊቱን እየጣሉ የኮበለሉ የስራዊቱ መኮንኖች፣ የበታች ሹሞችና ወታደሮች በይፋ እንዳጋለጡ ይሰማል፤ እርሱም በየግንባሩ ይሰማል። በግምገማና በልዩ ልዩ ስልቶች እርስ በእርሱ እምነት እንዳይኖር፣በጥርጣሬ እንዲተያይ፣ ለአንድ ሰራዊት የውጊያ ብቃት ወሳኝ ከሆኑት መስፈርቶች አንዱ የጋራ የውጊያ መንፈስ (Esprit de corps) የሌለው መሆኑን እናውቃለን፡፡ እርስ በእርስ መተማንን (Cohesion) እንዳይኖረው፤ በፖለቲካና በብሄር ተከፋፍሎ ተንፈራቆ እንዲቆም፣ የጎሪጥ እንዲተያይ፣ በራሱም እንዳይተማመን የተደረገ በዚህም ምክንያት ሞራሉ እንዲላሽቅ መደረጉ የሚኖርበት ሃቅ መሆኑን የታችኛው የመከላከያ ስራዊት አባላት ያውቁታል እየኖሩበትም ነው።ወያኔ ጦርነት ባወጀ ቁጥር፤ ጠብ በጫረባቸው ወቅቶች ሁሉ መቶ በመቶ ከፊት እንዲጋፈጥ፤ የጥይት እራት እንዲሆን፤ፈንጂ ረጋጭ የሚያደርጉዋቸው የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የደቡብ የጋምቤላ እንዲሁም የሌሎች ብሄር ብሄረስብ አባላትን እንጂ በዘረኝት በላዩ ላይ በአዛዥነት የተጫኑበት የወያኔ አርነት ትግራይ ወታደራዊ ሹሞች እንዳልሁኑ ያውቃል፤ ኖሮበታልም። በ 1990 –1992 (እ.ኤ.አ. 1998-2000) ከኤርትራ ጋር ወያኔ ባደረገው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ለጋ ወጣት ወንድሞቹን ፈንጂ ረጋጭ አድርገው ለእልቂት እንደዳርጉዋቸው ያውቀዋል። በመጨረሻው በ2000 ዓ.ም. በተደረገው ውጊያ የጦርነቱን ሁኔታ ለመለወጥ የተቻለው በወታደራዊ ሳይንስ በልምድ በብቃት ምርጥና ከፍተኛ ዝና የነበራቸውን ብ/ጄነራል ተስፋይ ሀብተማርያም አየር ወለድ (ከብ/ጄነራል ለገሰ ተፈራ ጋር የህብረተሰባዊት ኢትዮጵያ የላቀ ጀግና ሜዳልያ ተሸላሚ) ብ/ጄነራል በሀይሉ ክንዴ ታንከኛ፣ ብ/ጄነራል ንጉሴ አዱኛ መድፈኛ፣ ብ/ጄነራል ተጫኔ መስፍን ከአየር ሃይል፣ እንዲሁም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ በደርግ ኢሰፓ ስር በነበረው የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት ውስጥ ያገለገሉ ወያኔ ከደርግ ውድቀት በኋላ እነሱና ቤተሰቦቻቸውን ለውርደትና ለችግር የዳረጋቸው የቀድሞ ሰራዊት የመስመር መኮንኖች፤ ባለሌላ ማዕረግተኞችና ወታደሮችን መልሶ በማስገባት ነበር። ከተጠቀሙባቸው በኋላም መልሰው ነው ያባረሯቸው። ይህን የዘረኝነት በቀጽሞ ሰራዊት አባላት ላይ የተፈጸመ ዳግመኛ የግፍ ታሪክ ብዙው የኢትዮጵያ ህዝብ አያውቀውም። ወያኔዎች በእነዚህ ሙያዊ ብቃትና ክፍተኛ አስተዋጽዖ የጦርነቱን ሁኔታ ለመለወጥ መቻላቸውን ህዝብ እንዲያውቅ ማድረግ ዘረኝነታቸውና የበታችነት ስሜታችው አልፈቀደምና። እ.ኤ.አ. በ2006 ወያኔ ሶማሊያን ሲወርር ማን ከፊት ሆነው እንደተማገዱ ፈንጂ ረጋጮች እነማን እንደነበሩ ይህ ሰራዊት አይቶአል፤ ያውቀዋል። ኖሮበታል።በወታደራዊ ሳይንስ ትምህርታቸው በአለም ታዋቂ ከሆኑ የጦር ኮሌጆች፣ ወታደራዊ አካዳሚዎች፣ ስታፍና ኮማንድ ተቋማት የተመረቁ የምድር ፣ የአየርና የባህር ምርጥ የበላይ አዛዦችና የመስመር መኮንንኖች በብዛት ነበሩበት። የሶማሊያ ወራሪን ጦር ሃይል መክቶ ከማባረር እስከ ሰሜን የጦር ግንባሮችን ይህ ነው በማይባል ጀግንነት የተዋጋ ሰራዊት የነበረበት። ይህ ግምሽ ሚሊዮን የሚገመትና ከአፍሪካ ውስጥ ከነበሩት የመከላከያ ሰራዊቶች ትልቅ ከሚባሉት ፤ እስከ አፍጢሙ በዘመናዊ መሳሪያዎች ታጥቆ የነበረው በደርግ ኢስፓ አመራር ስር የነበው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ውድቀት በዋነኝነት የሚቀርቡት ምክንያቶች ለ23 ዓመታት ወያኔዎች ህዝብን ለማንበርከክና አይበገሬዎች ነን የሚል የውሸት ታሪክ ለመጻፍ እንደሞከሩት፣ እንደሚፎክሩት አይደለም። ወያኔዎች ከሌላው ኢትዮጵያዊ የተለየ ጀግንነት የወያኔዎች የወታደራዊ ብቃትና ስትራቴጄካዊ ብስለትና እወቅት ስለነበራቸው ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብና በወቅቱ የነበረው የደርግ/ኢሰፓ መንግስት ሆድና ጀርባ ስለነበሩ ነው። የነበረው አገዛዝ ፖሊሲዎችና ብዙዎቹ ተግባራቱ የህዝብን ልብ ስላሸፈቱ፤ ቅራኒዎቹም የህዝብ ድጋፍ ስላሳጡት፤ ስራዊቱም የህዝቡ ነጸብራቅ ስለነበረ በዘርፈ ብዙ ቅራኔዎች ሰለባ ሰለተደረገ እንደነበር የዛሬው የመከላከያ ሰራዊት ከዚህ ከራሱ ታሪክና ከሌሎችም ሃገራት የወታደራዊ ውድቀት ታሪኮች ማወቅ ይገባዋል።ዘመናዊ መሳሪያ እስከአፍንጫ ቢታጠቅ ፤ ሰራዊቱን በሚሊዮን ቢያደራጅ፤ ስርዓቱ በህዝብ የተተፋ፤ በቅራኒዎች የተዋጠ–በተለይም እንደወያኔ ዘረኛና ዘራፊ አገዛዝ፤ ሀገራዊ ራእይ ባላቸው ግፍና በደል አንገሽግሾዋቸው ፍትህና ነጻነት የተራቡና የተጠሙ የህይወት መስዋትነት ለመክፈል በቆረጡ፤ የህዝብ ልጆችና በኢትዮጵያ ህዝብ ደጀንነት በአቸናፊነት እንደሚጠናቀቅ ከአገራችንም ሆነ ከሌሎች አምባገነናዊ ስርዓቶች ውድቀት መማር የግድ ነው። ከላይ እንደገለጽነው ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመጠበቅ የሚለው የሰራዊቱ ዓላማ በራሱ በወያኔ የተደፈረ፤ የተረገጠ ህገ መንግስት በመሆኑ የሞተ ሰነድ ባዶና ቀፎ በመሆኑ ህይወቱን የሚገብርበት ምክንያት የዛሬው የመከላከያ ሰራዊት ሊኖረው አይችልም። የሁሉም ብሄረሰቦች እኩልነትና የተመጣጠነ ሰራዊት በሚል የተቀመጠውም የወያኔዎች ቡዋልት ከመሆን ያላለፈ መጭበርበሪያ እንጂ ዛሬ ይህ ስራዊት በአንድ ብሄር በአንድ ቋንቋ የበላይነት በፋስሽቱ የወያኔ አርነት ትግራይ ጀነራሎችና መኮንኖች ፈላጭ ቆራጭነት ከላይ እስከ ታች ስር እንዳለ ከታች ያለው የመከላከያ ሰራዊት ያውቀዋል። በወያኔ ስር የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት ዘርፈ ብዙ ችግሮችና ቅራኔዎች እንዲሁም ደካማነት በሚመለከት በወታደራዊ ሳይንስ የላቀ እውቀት፤ ልምድና በህወአት ስር ስለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ወቅታዊ መረጃ ባላቸው የአየርና የምድር መኮንኖች የተደረጉ ጥናቶችን ንቅናቄያችን በቅርቡ ይፋ ያደርጋል።የፋሽስቱ የወያኔ አርነት ትግራይ ጀነራሎችና ወታደራዊ መኮንኖች እንደ ሲቪል የወያኔ ዘመዶቻቸው፤ በጎሬጥ የሚተያዩ፣ የሚናናቁ፣ በጥቅምና በስልጣን የሚሻኮቱ፤ የተቋሰሉ እንደሆነ ከታች ያለው ሰራዊት ያውቀዋል። አንዳንዶቹ ልባቸው የሸፈተና አጋጣሚና ጊዜ ቢያገኙ እርምጃ ለመውሰድ የሚያደቡ እንዳሉ በልዩ ልዩ ጊዜዎች ንቅናቄችን መረጃዎች ደርሰውታል። በ3ኛ ሀገሮች ከንቅናቄው ተወካዮች ጋር ለመገናኘት መልዕክት የላኩም አሉባቸው። አላማቸው፣ ራዕይያቸውና ግባቸው ህዝባዊ ስላልሆነ በንቅናቄው በኩል የእነዚህ የህወሀት መኮንንኖች ጥያቄ ተቀባይነት አላገኘም።በዘራፊ፣ ሙሰኛና ዘረኛ የወያኔ ወታደራዊ አዛዦች ለሚመራው ከህዝብ አባራክ ለወጣው ሰራዊት የምናቀርብለት ጥሬ መሣሪያውን በግፈኞችና በፋሽስቶች ላይ እንዲያዞር ነው። የነፃነት ታጋዮችን እንዲቀላቀል ጥሪ እናደርጋለን። ነገ ጥለውትና አጋልጠውት ለሚፈረጥጡ የዚህ የዘረኛና ዘራፊ ስርዓት ግፈኛ መሪዎች መሳሪያ ሳይሆን የህዝብ ወገን መሆን መርጦ ራሱን ኢትዮጵያንም፤ ከአብራኩ የወጣበትን የኢትዮጵያ ህዝብ ከውርደት እንዲያወጣ ንቅናቄያችን ጥሪ ያቀርብለታል!የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ፦ይህን ትግል ዳር ለማድረስና በድል ለማጠናቀቅ ዋና መሰረቱ ጠንካራ ድርጅት ነው።
- ግንቦት 7፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ አስተባብሮ ወደ ድል ለመምራት ዝግጁ ነው፤ ድርጅታዊ አቅሙን እንድናጠናክር ለሁሉም አትዮጵያዊ ጥሪ እናደርጋለን፤
- ግንቦት 7 ሁለገብ ትግልን – ሕዝባዊ ተቃውሞን፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነትን እና ሕዝባዊ አመጽን – አስተባብሮ መምራት ወደሚችልበት ደረጃ ለማድረስ በጋራ ቆርጠን እንድነሳ ጥሪ እናደርጋለን፤
- ትግሉ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ በአጎራባች አገሮችና ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩባቸው ሌሎች አገራት ውስጥ በመሆኑ በሁሉም ቦታዎች ድርጅቱን በማስፋት እንድናጠናክር ጥሪያችንን እናቅርባለን፤
- ትግሉ በከተማም በገጠርም፤ በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም በመሆኑ እነዚህን አስተባብሮ የሚመራ ድርጅት ያስፈልጋል።
በፀረ-ወያኔ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ የፓለቲካ ድርጅቶች የሚዋሃዱበትና የሚቀናጁበት ወቅት አሁን ነው። ከሁሉም በላይ ከወያኔ በኋላ የተዋሃደችና የጠነከረች ኢትዮጵያ እንድትኖረን ካሁኑ አገር አድን ኃይል ማደራጀት አስፈላጊነቱን ንቅናቄያችን ከምንም በላይ ይገነዘባል። በዚህም መሠረት ግንቦት 7 በተግባራዊ ትግል ውስጥ ካሉ ድርጅቶች ጋር በየጊዜው እየዳበረ መጥቶ የአገር አድን ኃይል ምሥረታን ያለሙ ኅብረቶችን ለመፍጠር ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህም መሠረት:በዓላማ፣ በአደረጃጀትና በስልት ከሚመስሉን ለመዋሃድ ጥረት እናደርጋለን። በአሁኑ ሰዓት ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እና ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ጋርለመዋሀድ ተስማምተን እየሰራን እንገኛለን። በዓላማ የምንስማማ ሆኖ አደረጃጀታችንን የማቀራረብ ሥራ የሚጠይቅ በሚሆንበት ጊዜ በጥምረት ለመሥራት ጥረት እናደርጋለን። በዚህ ረገድ የሚጠቀሱት ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትሕዴን)፣ በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ እና ከአፋር ሕዝብ ፓርቲ ጋር የመሠረትናቸው ጥምረቶች አብይ ምሳሌ ናቸው። በተለይ ከትሕዴን (ደሚት) ጋር የምንሠራቸው የጋራ ሥራዎች እየጎለበቱ መጥተዋል። ከሌሎች የኢትዮጵያ ድርጅቶች ጋር ለጋራ ሥራ የምናደርጋቸው ትብብሮች፣ በዚህ ረገድ የሚጠቀሱት የቤኒንሻጉል ሕዝቦች ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ንቅናቄ፣ ኦነግ፣ አብነግ በአርአያነት ይጠቀሳሉ።ዛሬ ለሁሉም ለነፃነቱ፣ ለሰብዓዊ ክብሩና መብቶች ለሚቆረቆሩ ኢትዮጵያዊያን የቀረቡትአማራጮች ሁለት ብቻ ናቸው።- በዜጎች ላይ ጭካኔዎች የሚፈጸሙባት፤ የሰው ልጆች ሰብዓዊ ፍጡራን ለአርመኔያዊ ግፍና ስቆቃ በሚዳረጉባት ሀገር፤ በውርደትና በደል የሚማቅቁባት፤ ዘራፊና ዘረኛጥቂት ፋሽስቶች እንዳሻቸው የሚፈነጩባት፣ ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ባይተዋርና የበይ ተመልካች፣ መብትና ሀገር አልባ የሆነ በሶስተኛ ዜግነት፤ እንዲያውም በባርነት አንድ ጊዜ ብቻ የሚኖርበት፣ የምትኖርበት በዚህ አለም ውድ ህይወቱን በሲኦል የሚገፋበት አንዱ አማራጭ ነው፡፡
- በሌላና በተጻጻሪው የሚገኘው አማራጭ ደግሞ የሰው ልጅ፤ ሰብዓዊ ፍጡር፣ ማንም ኢትዮጵዊ ዜጋ ምንም ያድርግ ወይም ታድርግ ወንጀል ቢፈጽም እንኳን በህግ የበላይነት — በግፍ ሰቆቃና ቅስም ሳይሰብር፣ ውርደት ጭካኔያዊ ተግባራት ሳይፈጸምበት– ቅጣቱን የሚቀበልበት የህግ የበላይነትና ነጻ ዳኝነት የነገሠባት ኢትዮጵያ ናት። እያንዳንዱ ዜጋ፣ እያንዳንዱ ብሄር ብሄረሰብ አሮሞው፣ አማራው፣ የደቡብ ህዝቦች፣አፋሩ፣ ኦጋዴኑ፣ ጋምቤላው፣ ህይወታቸው፤ እድላቸው በእንደአሁኑ በጥቂት ዘረኞችና በእነሱ ሎሌዎች ሞግዜትነት፤ ፈላጭ ቆራጭነት የሚወሰንበት፣ በላያቸው ላይ የሚሾሙበት፣ በግድ የሚጫኑበት ሳይሆን ብሄር፤ ብሄረሰቦች ፤ እያንዳንዱ ህዝብ በየአካባቢው ነጻና ርዕታዊ በሆነ ዲሞክራሲያዊ መንገድ ራሱ በሚመርጧቸው መሪዎች/ተወካዮች ብቻ የሚተዳደርበት ስርዓት በትግላችን እወን ማድረግ ብቸኛው አማራጭ ነው፡፡
- ምርጫችን ሙስሊም ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን፣ ሁሉም የእምነትቶች፣ መብቶቻቸው የሚረጋገጥበት፤ ስብዕናቸው፣ ድምጻቸው የሚከበርበት፣ እምነቶቻቸው በሚፈቅዱት መስረት የራሳቸውን ጉዳዮች በራሳቸው መንገድ በነጻ የሚወስኑበት፣ በመንግስት ጣልቃ ገብነት ሳይሆን በህግ የበላይነት ብቻ የሚወስኑበት፣ በምንም መልኩ የማይደፈሩበት፣ የማይዋረዱባት፣ የማይረገጡባት፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ለስደት ባርነት ተዳርገው ለስቃይ ለበደል፣ ለወርደትና ጥቃት በየአረብ አገሩ የማይሸጡባት ኢትዮጵያ በትግላችን እውን ማድረገ ብቸኛው አማራጭ ነው።
- ምርጫችን ስልጣን የተገደበባት፣ አንዱ ስልጣን ሌላውን ስልጣን የሚቆጣጠርባት፣ ስልጣን ህዝብን ማገልገያ እንጂ ለመንግስታዊ ዘረፋ የማይውልበት፣ ህዝብን ለማገልገል እንዲ ህዝብን መገልገያ የማይደረግበት፣ ስልጣንና ባለስልጣናት ለህዝብ ተጠያቂ የሚሆኑባት፣ ትክክለኛ የህዝብ ወሳኝነት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚረጋገጥበት ፤ ሰብዓዊት የሰፈነባት ፤ የዜጎችዋ ሰቆቃና ስቃይ፣ ወርደትና ስደት፣ ድቀት የሚያከትምባት፣የነጻነት አየርን ሁሉም ዜጎች የሚተነፍሱባት፣ ትክክለኛ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ስርዓት የነገስባት ኢትዩጵያን በትግላችንና በሁለንተናዊ በመስዋእትነት እውን ማድረግ የቀረበልን ብቸኛ አማራጭ ነው።
- ምርጫዎችን የመወስን ወስኖም ለተግባራዊ የትግል እንቅስቃሴዎች ዝግጁ መሆን ጊዜው አሁን ነው!! ንቅናቂያችን ለኢትዮጵያ ወጣቶች፤ የዩኒቨርሲቲና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ ለሁሉም ብሄር ብሔረሰቦች፣ የልዩ ልዩ እምነት ተክታዮች፣ ለኢትዮጵያ ሴቶች አልገዛም ባይነት፣ የህዝብ እምቢተነት፣እንዲሁም አመጽ እንዲያቀጣጥሉ ንቅናቂያችን ጥሪውን ያቀርባል!! የመንግስት ሰራተኞች ስራ በመጎተት ስራ በማቀዝቅ ስርዓቱን የበለጠ እንዲያዳክሙት ጥሪያችንን እናቀባለን።
የተዋበች፣ ሰብዓዊትነት የሰፈንባት፣ የገዢዎ ሳይሆን፣ የዘረኞች ሳይሆን የህግ የበላይነት ብቻ የነገሱባት የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ፍትሃዊ የሆነ የሃብት፣ የስልጣን፣ የጥቅም ክፍፍል የሚረጋገጥባት ፤ የእያንዳዱ ዜጋ ነጻነት የተረጋገጠባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በትግላችን በመስዋዕትነት እውን ለማድረግ ሁላችንም ቆርጠን እንነሳ! የምንችለውን አይነት መስዋዕትነት በእጥፍ ድርብ ለመክፈል በጋራ ተነስተናል!! ሁሉም የሚችለውን የትግል ዘርፍ መርጠን ያለውን ጠጠር ሁሉ እንወረውራለን!! ለዚህም ቃል ኪዳን እንገባለን።አትላንታ ፤ ኦገስት 31፡ 2014-- Ze-Habesha
No comments:
Post a Comment