Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, September 22, 2014

በጀርመን ሃገር ለምትገኙ ገር ለምትገኙ ለእኔም አንዳርጋቸው ነኞች በሙሉ !

እኔም አንዳርጋቸው ነኝ

Andargachew Tsige.jpg2
አቶ አንዳርጋቸውን በሕይወት ያገኘሗቸው አንድ ቀን ብቻ ነው። ይኸውም የቅንጅት አመራሮች ታስረው በነበረበት  ጊዜ ይፈቱ እያልን በዓለም ዙሪያ ሰላማዊ ሰልፍ በምናደርግበት ጊዜ ባንዱ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ነበር። ከዚያ በተረፈ  የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ እሳቸውንም አካትቶ ከተቋቋመ በዃላ፤ በተለያዩ መድረኮች እየተገኙ  የሚያደርጓቸውን የውይይት ቪዲዎዎች፤ በተለያዩ ሚዲያዎች በሚሰጣቸው ቃለ ምልልሶችና እንዲሁም ካንዳንድ ሰዎች  ጋር የሚያደርጉትን ክርክር በማዳመጥና በመሳሰሉት ሲሆን፤ ለመጨረሻ ጊዜም ድምጻቸውን በዚህ መልክ የሰማሁት   መስከረም ወር 2006 ዓ.ም. ገደማ በዲያስፖራው አካባቢ ባጠቃላይና እንዲሁም ባንዳንድ ለየት ባሉ አቀራረቦች  ወያኔን ለቀቅ፤ ግንቦት 7ትን ጠበቅ የሚያስብል ዓይነት ጠረን ያለው ተቃውሞን ያስከተለ ከኢሳት ቴሌቪን ጋር  ባደረጉት ቃለ ምልለሳቸው ነው። ከዚህ የተለየ ስለሳቸው የማውቀው ነገር የለኝም።
ከላይ የአቶ አንዳርጋቸውን ስም ማዕከል አድርገው የተቋጠሩትና ለዚህ ጽሁፌ ርዕስ አድርጌ ያስቀመጥኳቸውን ሶስት  ቅኝቶች ስንሰማቸው ወራቶችን መሸኘታችን አከራካሪ እንዳልሆነ በሁላችን በኩል ግንዛቤ እንዳለ እምነት አለኝ። በበኩሌ  ግን ከስማ በለው ባለፈ አቶ አንዳርጋቸውንና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችንም አያይዘው በተዘጋጁ አጋጣሚዎች ላይ  ተገኝቼ ደጋግሜ አዳምጫቸዋለሁ።
http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2014/09/Enem-Andargachew-negn.II-XY-1.pdf

No comments:

Post a Comment

wanted officials