ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በፌዴራልፖሊስ ተከበበ
ኢህአዴግ ከተለያዩ የሃገራኅችን ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ተማሪዎች በግዳጅ “የመለስ ራዕይ” እያሰለጠናቸው ይገኛል።
የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲም ከትግራይ ምስራቃዊ ዞንና ዓዲ ኣሕፈሮም ወረዳ የተውጣጡ ተማሪዎች ተሰብስቦውበታል። ተማሪዎቹ በስልጠና ወቅት ከህወሓት ከድሬዎች ኣቅም በላይ ጥያቄዎች በመጠየቅ ህወሓትን እያበሳጩ ከሰነበቱ በኋላ ከሓሙስ 28 / 12 / 2006 ዓ /ም ጀምረው በኣበል ክፍያ በተፈጠረ ኣለመግባባት “ከግቢው ኣንወጣም” ብለው ኣድመዋል።
በዚህ ኣድማቸው የኣቋም ለውጥ ባለማምጣታቸው ግቢው በፌዴራል ፖሊስ ተከቦ እየተጠበቀ ይገኛል። ከተማዋም ከዞኑ የተውጣጡ ፖሊሶች ተሞልታለች። የኣዲሱ ትውልድ ጀግኖች በህወሓት ፕሮፖጋንዳ በፍፁም ሊታለሉ ኣልቻሉም።
በሌላ ዜና…!
————
————
እሮብ 27 / 12 / 2006 ዓ/ ም ደግሞ በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ኢህኣዴግ ባዘጋጃቸው ተማሪዎችና የተቀረው ስልጣኝ ተማሪ በተጀመረ ግጭት የፈዴራል ፖሊስ ገብቶ ተማሪዎችን በመደብደብ ከፍተኛ ጉዳት ኣድርሷል።
ስብሰባው እየመሩ የነበሩ ካድሬዎች ካዳራሹ ሮጠው ከግቢው ያመለጡ ሲሆኑ፤ ተማሪዎች እርስበርስና የፌዴራል ፖሊስ ደርሶ ባደረሰው ድብደባ ክፉኛ የተጎዱ ተማሪዎች መኖራቸው የዓይን እማኞች ከቦታው ገልፀዋል።
No comments:
Post a Comment