ዓለም በኤቦላ ስጋት መታመስ ሲጀምር በቀድሞዋ ዛየር በዛሬዋ ዴሞክራቲክ ሬፐብሊክ ኮንጎ ተኅዋሲውን ያገኙት የቤልጅየም ተወላጁ ፕሮፌሰር ፒተር ፒዮ መታወስ ጀመሩ።ፕሮፌሰሩ በአሁኑ ወቅት የለንደን የግል ንጽህናና የምድር ወገብ አካባቢ በሽታዎች ትምህርት ቤትን በሃላፊነት ይመራሉ።
በቅርቡ የተከሰተውን አስከፊ የኤቦላ ወረርሽኝ ለመግታት እየሰሩ እንደሆነ ይታመናል። በጌንት የህክምና ትምህርት ቤት የመጨረሻ ዓመት ተማሪ ሳሉ የተወሰኑ የፒዮ መምህራን በተኅዋሲ እና በባክቴሪያ የሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎችበመድሃኒቶችና ክትባቶች መበራከት ምክንያት ስለሚቀንሱ ዘርፉ የወደፊት ተስፋው የተመናመነ እንደሆነ ነግረዋቸው ነበር።
ነገር ግን ፒዮ እነዚህ ደቃቅ ተኅዋሲያን በሰው ልጅ ላይ ባላቸው ከፍተኛ ተፅዕኖ ይገረሙ ነበር።እናም የመምህራኑንምክር ሳይሰሙ በተኅዋሲ እና በባክቴሪያ በሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎች ላይ ትኩረታቸውን ለማድረግ ወሰኑ።
”ከህክምና ትምህርት ቤት ከተመረኩ የተወሰኑ ዓመታት በኋላ በአንትወርፕ የምድር ወገብ አካባቢ በሽታዎች ትምህርት ቤት በስልጠና ላይ ነበርኩ።አንድ ቀን ከቀድሞዋ ዛየር ለምርመራ የተዘጋጀ የደም ናሙና መጣልን።የደሙ ናሙና የአንዲት ሟች መነኩሲት ሲሆንየሞታቸው ምክንያት ቢጫ ወባ ተብሎ የሚጠራውህመም ነው ተብሎ ይታሰብ ነበር።ከዛ የደም ናሙናውስጥ ዛሬ ኤቦላ ተብሎ የሚጠራውን አደገኛ ተኅዋሲአገኘን።እናም ወደ ዛየር አመራሁ። የዓለም ጤና መድረክን በድንገት የተቀላቀልኩት በዚህ መንገድ ነበር።”
ፒተር ፒዮ የኤቦላ ተኅዋሲን ካገኙ አርባ አመታት ተቆጠሩ።በምዕራብ አፍሪካ የተከሰተው ኤቦላ መስፋፋት በአለምሰላምና ደህንነት ላይ የተጋረጠ አደጋ መሆኑን የተባበሩት መንግስታ ድርጅት አስታውቋል።ከዚህ ገዳይ ተኅዋሲ ጋርበሚደረገው ትንቅንቅ ከፊት ከተሰለፉት ባለሙያዎች መካከል አንዱ የሆኑት ፒዮ አሁን የተከሰተው መስፋፋትእንዳስደነገጣቸው ይናገራሉ።
”ይህ የኤቦላ መስፋፋት በይፋ ከሚታወቁት ሃያ አምስተኛው ነው።መስፋፋቱ በምዕራብ አፍሪካ የመጀመሪያውከእስካሁኖቹም ትልቁ ነው።በዚህ መስፋፋት የሞቱት ሰዎች ቁጥር በቀድሞዎቹ በአንድነት ከገደሉት መብለጡአስገርሞኛል።ምክንያቱም የቀድሞዎቹ በቦታና ጊዜ የተወሰኑ ነበሩ።ካሁን ቀደም የኤቦላ ህሙማኑን በመለየትናእንቅስቃሴያቸውን በመገደብ በትናንሽ መንደሮችና ከተሞች የተከሰቱትን ወረርሽኞች መግታት ተችሏል።”
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በምክትል ዋና ጸሃፊነት በሙያው ያገለገለገሉት ፒዮ የተባበሩት መንግስታትድርጅት ሰላም አስከባሪ ጓድ የኤቦላ መስፋፋትን ለማስቆምለሚደረገው ጥረት እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ ሲያቀርቡቆይቷል።
”ይህ ከፍተኛ የተኅዋሲዎች ስርጭት በደኖች አልያም በሌሊት ወፎች ውስጥ የተደበቀ ነዉ። የህዝብ ቁጥር ብዛት መጨመር የሚታይባቸዉ ፤ ደናማና ደን የተጨፈጨፋባቸዉ፤ ለዓመታት የርስ በርስ ጦርነት የሚታይባቸዉ አካባቢዎች እንዲሁም በሙስና የተጨማለቁ መንግሥታት ምን ያህል ለዚህ ተኅዋሲ መስፋፋት ተጋላጭ መሆናቸዉን አናቅም። ይህም ማለት በባለስልጣናት እና ብልሹ የጤና ተቋማት እምነት ጠፍቶአል።”
በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በምህጻሩ ዩ.ኤን.ኤም.ኢ.ኢ.አር. ተብሎ የሚጠራ የኤቦላን የምዕራብ አፍሪቃስርጭት ለመግታት የአስቸኳይ ጊዜ ግብረ-ሃይል አቋቁሟል።ፒዮ ግን ይህን ስርጭት ለመግታት የሚደረገው ጥረትዘገምተኛ ነው በማለት በተደጋጋሚ ይተቻሉ።ስርጭቱ ከቁጥጥር ውጪ የሆነበትም አንዱ ምክንያት ይህው ዘገምተኛምላሽ መሆኑን ይናገራሉ።
”በላይቤሪያ ለ100,000 ሰዎች ያለው አንድ ዶክተር ብቻ ነው።ከእነዚህም መካከል ብዙዎቹ በቅርቡ በኢቦላ ሞተዋል።”
የኢቦላ ህመምተኞቹን በመለየትና እንቅስቃሴያቸውን በመገደብ በቅርቡ የተከሰተው ወረርሽኝ የመጨረሻው መሆን እንዳለበት ፒዮ ያምናሉ።ለዚህም ወረርሽኙ ሊዛመት በሚችልባቸው አካባቢዎች በቂ የመድሃኒት ክምችትእንደሚያስፈልግ ይናገራሉ።
ትሬቨር ግሩንዲ
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ
No comments:
Post a Comment