ኢሳት ዜና :- በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ስራ በሚገኘው ደጀና አቬሺን ውስጥ የሚሰራ ስሙ በውል ያልታወቀ አንድ ወታደር በግቢው ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች በተከፈተው ሻሂ ቤት ውስጥ
በአስተናጋጅነት የምትሰራዋን በደብረዘይት ነዋሪ የሆነች ወጣት በስድስት ጥይቶች ተኩሶ መግደሉን የአይን እማኞች ገለጹ።
ትናንት 11 ሰአት ላይ ሰራተኞች ሰርቪስ አውቶቡስ ለመያዝ በተሰለፉበት ወቅት፣ ወታደሩ በአስራዎች እድሜ ውስጥ የምተገኘዋን ሙሉ የምትባለዋን ወጣት በጥይት ደብድቦ ገድሏታል። በድርጊቱ የተበሳጩት ሌሎች ሰራተኞች ወታደሩ ባለመያዙ
ተቃውሞአቸውን መግለጻቸውን ተከትሎ፣ ከግማሽ ሰአት በሁዋላ የግቢው ባለስልጣናት ” ግለሰቡ መያዙን” በመግለጻቸው ሰራተኞች ወደ ቤታቸው መሄዳቸው ታውቋል።
በግቢው ውስጥ የሚታየው ሰብአዊ መብት ጥሰት ከፍተኛ መሆኑን የሚናገሩት ሰራተኞች ማንም ድርጅት ትኩረት እንዳልሰጠው ገልጸዋል።
No comments:
Post a Comment