አንጋፋው ኢትዮጵያዊ ፎቶግራፈር ኢቲቪን ሊከስ ነው
ንጉሴ ተሸመ ደጀኔ ይባላል፡፡ዕድሜውን ለፎቶግራፍ ጥበብ የሰጠ እና የኢትዮጵያን ፎቶግራፍ ታሪክ በግሉ ያጠና እና (ኢትዮጵያዊ) የራስተፈሪያን ታሪክን ፅፎ ያዘጋጀ ያልተዘመረለት የፎቶ ጥበብ ባለሙ ነው፡፡በሻሸመኔና በናዝሬት ኑሮና ስራውን ያደረገው ጋሽ ንጉሴ በቅርቡ በኢቲቪ 1 በጌቱ ተመስገን የቀረበውን ዘጋቢ ፊልም የሚወቅስበት ብዙ ጉዳዮችን ያነሳል፡፡ጌቱ አቶ ንጉሴ ከዓመታት በፊት አግኝቶ ከህዝብ ያስተዋወቃትን ፎቶዋ በወጣትነቷ በቱሪዝም ኮምሽን ተባዝቶ ሲቸበቸብ የኖረውን ተበዳይዋን ለህዝብ ራሱ ፈልጎ እንዳገኘ አድርጎ አቅርቧል፡፡እንደውም ዛሬ በራሱ ፌስቡክ ገፅ በጻፈው መሰረት ወደ ህግ ለወስደው እንደሚችል ጠቁሟል፡፡
ሃቀኛ ጋዜጠኞች በሚታሰሩበት በሚሰደዱበትና በሚጋዙበት በዚህ ወቅት ጥቂት የመንግስት ጋዜጠኞች የብዙሃኑን ድምፅ አፍነውና ባለሙያዎችን እያበሳጩ የሚሰሯቸው ስራዎች አንድ ሊባል ይገባዋል፡፡ለሙሉው መረጃ ከዚህ በታች ያለውን ፅሁፍ ያንብቡ፡፡ጋሽ ንጉሴ ምኒሊክ ና ዮሃንስ የተባሉ ወንዶች ልጆች እና የሞዴሊስት ትዝታ ንጉሴ እና የህጻን ኢትዮጵያ አባት ነው፡፡በአሁኑ ወቅት በኣዳማ/ናዝሬት ነዋሪ ነው፡፡ሁላችንም ከጋሽንጉሴ ጋር በመቆም ለሐቅ ኣጋርነታችንን እናሳይ፡

No comments:
Post a Comment