የበሰበሰውን የወያኔ ስርአት እንዲወድቅ እያንዳንዱ ዜጋ ትግሉ እንዲፋጠን ሚና መጫወት አለበት።
በዚህ የመጨረሻው ወሳኝ ምእራፍ ላይ ወጣቱ ትውልድ ዘመናዊ ባርነትን እሺ ብሎ የማይቀበል ተፈጥሮ የሰጠችውን ነጻነት በአምባገነኖች ሲነጠቅ ዝም የማይል በመሆኑ ለወያኔ አገዛዝ የማያመች ሆኖበታል ። Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በነጻ አስተሳሰቦች መኖር በማይቻልባት ኢትዮጵያ ወያኔ ዜጎች ካልደገፉት ዘርፈ ብዙ እርምጃዎችን በተከታታይ ይፈጽማል። ወያኔ ከጽንሰቱ ጀንሮ ፣ ውለደቱና እድግቱ የሆነው አሸባሪነት ፣ ጽንፈኝነትና ዘረኝነት ሆኖ ከሚታወቅበት ተነስተን ባሁኑ ወቅት አሸባሪነትን ሲቃወም እና ሌሎችን ሲወነጅል መስማቱ <ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ> ያስብላል ። ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔን መቃወም ብቻ ሳየሆን አለመደገፍ በራሱ ከተቃዋሚነት ጎራ ይፈርጃል ።ነጋዴው ለሃገሪቱ የሚያስመዘግበው የንግድ ዕድገትና ለዜጎች የሚከፍተው የስራ ዕድል እና ተያያዥ አስተዋጾኦች ባሻገር ወያኔን መደገፉን በተለያየ መልኩ ካላስመሰከረና በተጨማሪም ለወያኔ ያለውን አምልኮ ካላረጋገጠ ያገልግሎቱ ጠቀሜታ በዜሮ ተባዝቶ ከንግዱ አለም ጨዋታ ውጪ ይደረጋል። ገበሬው ማዳበሪያ ለማግኘትና ዘርቶ ለማጨድ ወያኔ ባዘጋጀለት መንገድ ብቻ መግዋዝ ይኖርበታል። ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ከፍተኛ ተጽእኖ የሚደርስበት ሲሆን ከዚያም አልፎ በቀጥታ የሚያረሰው መሬት ተነጠቆ ለልመና ለስደት ሊዳረግ ይችላል። የሀይማኖት አባቶች በልማት ስም ወያኔያዊነትን ካልሰበኩ በተቃዋሚ ፓለቲከኞች ጎራ ይመድባሉ።የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ ለመቀጠር ቢጫው የወያነ የአባልነት ካርድ ከትምህርት ማሰረጃና ከስራ ልምድ በላይ ዋንኛ የቅጥር መስፈረት ነው ።ተማሪውም ከከፍተኛ የት/ም ተቐማት ተመርቆ ለመውጣት (የትምህርር ጥራት ችግሩ እነዳለ ሆኖ) የወያኔ አባልነት ፎርም እንዲሞላ ይገደዳል። ፍርድ ቤቶች በህግ የበላይንት ሳይሆን ለወያኔዎች በሚመች መልኩ በንጹሀን ዜጎች ላይ በግፍ ይፈርዳሉ። ዜጎች መኖሪያቸው ተነጥቆ ለወያኔ አባላትና ለደጋፊዎቻቸው ተሰጥቶ ለጎዳና ህይወት ይዳረጋሉ ።ሰላማዊ ታጋዮች፣ ጋዜጠኞች ግለሰቦች የሀይማኖት መሪዎች ለወያኔ ያልተመቸ ማንኛውም ዓየነት እንቅስቃሴ የሚያደርግ አካል በአሸባሪነትና በአክራሪት ተፈርዶበት እስር ቤት ይወርወራል። ወያኔ አገራችንን ከተቆጣጠረበት ጀምሮ እስካሁን ድርስ ጽንፈኝነትንና እና ሸብርተኝቱን በተቀነባበረ መልኩ ሬት ሬት እያለን ሲግተን የቆየና ዘረኝነትን በየቦታው ሲሰብክና ህዝቡን ሲያወክ የኖረና በተግባር ያሳየን መሰሪ ቡድን አሁን ደሞ ባዲስ መልኩ በቲዮሪ ላስተምራችሁ ብሎ የዩነቨረሲቲ ተማሪዎችን እና የየከተማ ነዋሪዎችን እያስገደደ ይገኛል። ይህ ባዲስ መልኩ የሚንቀሳቀሱበት አካሄድ ጤናማ ያልሆነና ሰርአቱ የህብረተሰቡን ያመለካከት አቅጣጫ በማስቀየር የፈለጉት ኢሰብአዊ የሆነወን ያገዛዝ እድሜያቸውን ለማራዘም ያቀዱት ነገር እነዳለ ያሰታውቃል። ወያኔን የሚያሰጋው እና እንዲህ እንቀልፍ የሚነሳው የወጣቱ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ እያደረገ ያለውን አመጽ እንድሆነ ይታወቃል። ወጣቱ ትውልድ ዘመናዊ ባርነትን እሺ ብሎ የማይቀበል ተፈጥሮ ሰጠችውን ነጻነት በአምባገነኖች ሲነጠቅ ዝም የማይል በመሆኑ ለወያኔ አገዛዝ የማያመች ሆኖበታል ። ሀገር ውስጥ እየታየ ያለው በተለይ ወያኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ያጸደቀው የጸረሽብር ህግ ሳይገታው ህዝቡ ለነጻነቱ ለመታገል ተቃውሞውን እየገለጸ ባለበት እና ባሳየው ወኔና ቁጣ ወያኔን ማሸበሩ ከድሬዎችና ፈደራል ፖሊስ እያደረጉ ካሉት ህገወጥ እንቅስቃሴ ማረጋገጥ ይቻላል። ወያኔን እንቅልፍ መነሳት እና መቆሚያ መቀመጫ መንሳት የእያንዳንዳችን ዜጎች ግዴታ ሲሆን ይህ ለኛ የነጻነት ቀናችን መቅረቡን ከበስበስ የቆየው ለወያኔ አገዛዝ ደግሞ መውደቂያው መቅረቡ የሚያሳይ ነው

No comments:
Post a Comment