Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, September 6, 2014

አገር አቀፉ የኪነጥበብ ሽልማት ፕሮግራም ተሰረዘ

አገር አቀፉ የኪነጥበብ ሽልማት ፕሮግራም ተሰረዘ
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጳጉሜ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊያካሂደው የነበረው የኪነጥበብ ሽልማት አርቲስቶች ከፍተኛ ቅሬታ ከማቅረባቸው ጋር ተያይዞ እንዲሰረዝ መወሰኑ ተሰማ፡፡
ሚኒስቴሩ ኪነጥበብን ለማበረታታት በሚል በሥነጹሁፍ፣ በሥዕል፣በሙዚቃ እና በፊልም ዘርፎች ብቻ የየዘርፎቹ ማህበራት መርጠው የላኩዋቸውን 10፣ በድምሩ 40 ዕጩዎች በማወዳደር ከየዘርፉ የተሻለ ውጤት ያገኘውን ለመሸለም አቅዶ እየተንቀሳቀሰ የነበረ ቢሆንም ምርጫው ኢ-ፍትሐዊ ነው በሚል ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው አርቲስቶች ከፍተኛ ተቃውሞ ማንሳታቸውን ተከትሎ ውድድሩ እንዲሰረዝ መደረጉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ተናግረዋል፡፡
ማህበራቱ ያካሄዱት የዕጩዎች ምርጫ የማህበር አባል በመሆንና ባለመሆን እንዲሁም በመቀራረብ ላይ የተመሰረተና የየዘርፉን ብቁ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ያገለለ መሆኑም ጭምር ተጨማሪ ቅሬታ አስነስቶም እንደነበር ታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ማህበራቱ ያቀረቡለትን ዕጩዎች በመቀበል በተንቀሳቃሽ ስልክ አጭር መልዕክት፣ ሚኒስቴሩ በመረጣቸው 20 ያህል የመገናኛ ብዙሃን እና በየዘርፉ በተመረጡ ባለሙያዎች የመጨረሻ ዳኝነት በመስጠት አሸናፊዎችን ለመለየት በማቀድ ማስታወቂያዎችን ማስነገር ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በድንገት ሒደቱ እንዲቆም በመወሰኑ እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡
ሽልማቱ ለወደፊቱ እንደገና ስለመቀጠልና አለመቀጠሉ የታወቀ ነገር የለም።

No comments:

Post a Comment

wanted officials