እስማኤል አሊስሮ 11 ወጣት ምሁሮችን ከስልጣናቸው ሊያነሱ ነው (ሾልኮ የወጣውን የተባራሪዎቹን ስም ይዘናል) – ጸጋዬ በርሄ 12 ሚሊዮን ብር እንደሚያገኙ ተጋለጠ
አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፡
የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ እስማኤል አሊስሮ በመጪው የ2007 ምርጫ የክልሉ ፕሬዝደንት ሆነው ለመቀጠልና በተጨማሪም የአብዴፓ ፓርቲ ሊቀመንበር ለመሆን በከፍተኛ ተስፋ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ታውቋል።
አቶ እስማኤል አሊስሮ ከምርጫው በፊት ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ያሰቡ ሲሆን። ሃሣባቸውንም ለማሳካት በአሰራራቸው የማይስማሙ 11 ምሁር ወጣቶች ከመሀል ኮሚቴ አባልነትና ከየኃለፊነት ቦታዎቻቸው ለማንሳት ተዘጋጅቷል። እነዚህ ወጣቶች በብዛት የህወሓት መንግስት በክልሉ እጁን እንዳያስገባ የሚል አመለካከት ያላቸው ሲሆን አቶ እስማኤል አሊስሮ ደግሞ በዚህ አይስማሙም።
የፓርቲው ሊቀመንበር (የአብዴፓ) የክልሉ የትምሀርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጠሃ አህመድን ጨምሮ አስራ አንድ ወጣቶች ምናልባት ከምርጫው በፊት በተለያየ ምክንያት ከስልጣናቸው ይነሳሉ የሚል ግምት በስፋት እየተነሳ ነው።
1/ አቶ ጠሃ አህመድ
2/ አምባሳደር ሀሳን
3/ አቶ ሱልጣን አህመድ
4/ ወ/ሮ ዛህራ ሁማድ
5/ መ/ድ አሊ ጋርቦኢስ
6/ አቶ ኢሊያስ ሀሳን
7/ አቶ ኡስማን አይኒሳ
8/ አቶ ሀላቶ መሀመድ
9/ አቶ አሊ አብደላ
10/ አቶ ደረሳ አሊ
11/ አቶ ኢብራሂም ሁማድ… ሲሆኑ እነዚህ ወጣቶች ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሊነሱ መሆናቸው ከአቶ እስሚኤል ቢሮ የተገኘ የውስጥ መረጃ ይጠቁማል።
1/ አቶ ጠሃ አህመድ
2/ አምባሳደር ሀሳን
3/ አቶ ሱልጣን አህመድ
4/ ወ/ሮ ዛህራ ሁማድ
5/ መ/ድ አሊ ጋርቦኢስ
6/ አቶ ኢሊያስ ሀሳን
7/ አቶ ኡስማን አይኒሳ
8/ አቶ ሀላቶ መሀመድ
9/ አቶ አሊ አብደላ
10/ አቶ ደረሳ አሊ
11/ አቶ ኢብራሂም ሁማድ… ሲሆኑ እነዚህ ወጣቶች ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሊነሱ መሆናቸው ከአቶ እስሚኤል ቢሮ የተገኘ የውስጥ መረጃ ይጠቁማል።
ከዛ በኋላም በቦታዎቻቸው ለአቶ እስማኤል እና ለህወሀት ተማኝ ሆነው ሊያገልግሉ የሚችሉ ናቸው ተብለው የታሰቡትን ለመተካት ታስቧል። ይሄ ሳይሳከላቸው ቢቀር አቶ እስማኤል አሊስሮ በፈቃዳቸው ስልጣን እለቃለሁ ብለው ህወሃትን መስፋራራት አንድ አማራጫቸው ነው ሲሉም ምንጮቹ ያስረዳሉ።
በተመሳሳይ ዜና በአፋር ወጣቶች ሊመሰረት የታሰበው «ከዳባ አፋር አክሲዮን ባንክ» እንዳይመሰረት ተደረገ። ከሁለት ሳምንታት በፊት በሰመራ ከተማ በአሊ ግደይ ሆቴል በተደረገው ሰብሰባ የቀድሞ የትግራይ ከልል መሪ የነበሩትና አሁን የፈደራል የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ፀጋዬ በርሄ ተገኝተው የነበረ ሲሆን የአፋር አክሲዮን ማህበር አላማው ከአፍዴራ ጨው የሚገኘው ገቢ ለአፋር ክልል እንዲገባና ወጣቶችም በማህበር ተደራጅተው ራሳቸውን ከመለወጥ ባሻገር የአፋር ኢንተርናሽናል ባንክ ለመመስረት ነበር። ግን አቶ ፀጋዬ በርሄ ጣልቃ በመግባት መሆን የለበትም ብለዋል። ምንም እንኳ ከወጣቶች ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠማቸው ቢሆንም አሁን ያለው የወሎ አክሲዮን ማህበር የሚባለው ማህበር ያቋቋሙት አቶ እስማኤል አሊስሮ ሲሆኑ የማህበሩ ኃላፊ የሆነው አቶ ሲዒድ ያሲን ለአቶ እስማኢል አሊ ስሮ፣ ወ/ሮ ፈጡማ አብደላ (የእስማኤል ሚስትና) ለአቶ ፀጋዬ በርሄ በየአመት 12 ሚለዮን ብር ይሰጣቸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፋር ክልል የፀጥታ አካሎች የፍርድ ቤት ዳኞችና የፍትህ ቢሮ ኃላፊዎች በአይሳዒታ ከተማ ስልጠና ላይ ይገኛሉ።
ባለፈው ረቡዕ 28/1/2007 ጀምሮ ለ10 ቀናት ለሚቀጥለው የዚህ ስልጠና አላማ በመጪው ምርጫ ከህዝብ ሊነሳባቸው የሚችለው አመፃን ማዕከል ያደረገ ነው። በአፋር ክልል የሚገኙ 32 ወረዳዎች የተሳተፉበት በዚህ ስልጠና የሚደረገው በአማርኛ ቋንቋ ሲሆን «ለምን በራሳችን (በአፋርኛ) ቋንቋ አታደርጉልንም» የሚሉም አሉ ነገር ግን የአፋር ክልል እሰካሁን በራሳቸው ቋንቋ ሊሰሩ ያልቻሉበት ዋናው ምክንያት በክልሉ ለሚገኙ የወያኔ ድህንነቶች እንዲመች መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ለምንጮቻችን ነግረዋል።
በሌላ ዜና ዛሬ እሁድ2/2 /2007 ጀምሮ ለ10 ቀናት የሚቆይ የጋዜጠኞች፣ የማስታዋቂያ ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም በየወረዳው የሚገኙ ሪፖርተሮች ክልል አቀፍ የሚዲያ ስራተኞች ስልጠና በዛው በአይሳኢታ ከተማ ተጀምሯል።
ከኢቢሲ፣ ከሬዲዮ ፋና እና ከድምፅ ወያነ የአፋርኛ ክፍል ሰራተኞች በስልጠናው የሚካፈሉ ሲሆን ከየጣቢያው ሶስት ጋዜጠኞች በዚህ ስልጠና እንዲካፈሉ ተደርገዋል። ስልጠናው በመጪው ምርጫ ቀስቀሳው በሚዲያ ጉልበት እንዲኖረው ለማድረግ ቢሆንም በአሁን ወቅት በአፋር ክልል እነዚህ የመንግስት ሚዲያዎች የሚከታተል በጣም አነስተኛ ነው።
በአፋር ክልል እስካሁን የሬዲዮ ጣቢያ የሌለ ሲሆን ከመቀሌ በየቀኑ ለ1ሰዓት የሚሰራጨው የአፋርኛ ፕሮግራም ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው ራሱ ህወሃት ነው። ሁለቱም ስልጠናዎች እየመሩ ያሉት ከመቀለ የመጡ ባለሥልጣናት እንደሆኑ ታውቋል።
– Ze-Habesha
No comments:
Post a Comment