Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, October 19, 2014

በየ አረብ አገራቱ ለተገደሉት ኢትዮጵያውያን ሰልፍ ያልወጣው ወያኔ አሁን ለምን? (በ ዘአብርሃም ታዬ)

እንደ አሜሪካው በሌሎች ሃገራትም  ያሉትን የኢትዮጵያን ኤምባሲ አምባሳደሮች እንጠይቃለን
ጫካው ከህወሃት ወጣ እንጂ ህወሃት ከጫካው አልወጣም

አንደኛው በዲሞክራሲም  በስልጣኔም  ቁንጮ በሆነችው አገረ አሜሪካ  ውስጥ የኖረው የህወሃት /ወያኔ ኤምባሲ ጠባቂ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በከፈተው የተኩስ እሩምታ ነው።ኢትዮጵያ በማን አለብኝነት ሰውን እንደሚገድለው ሁሉ  ከሃገር ባንዲራ በስተቀር ምንም ላልያዙት የዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪዎች አምባሳደሩን ማናገር እንፈልጋለን ብለው ሰለጠየቁ ብቻ መተኮስ በአሜሪካ ያልተለመደ ነው። ያልተለመደ በመሆኑም የአንዲት ሽጉጥ ኮሽታ የሚረብሻቸው አሜሪካውያን ሚዲያዎች የህወሃትን የጫካ ባህሪይ ተቀባብለው አስተጋቡት። 48 ሰዓት ውስጥም   የደደቢት ጫካ ከውስጡ ያልወጣለት ሰሎሞን/ ወዲ ወይኒ ወደ መጣበት ጫካ እንዲመለስ የአሜሪካ መንግስት አስገደደው።
ሌላው የዚህን አውሬ ጸባይ ከውስጡ ያልወጣለት የህወሃት የደህንነት አባል ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ተከትሎ የስርዓቱ ደጋፊ ጥቂት ሰዎች  አልሞ ተኳሻችን ለምን ተመለሰብን ሲሉ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በውጪ አገራት የሚኖሩ የህወሃት ደጋፊዎች  ተዋረድን ብለው በአደባባይ  ሰልፍ ማድረጋቸው የተለመደ ጉዳይ ግን አልነበረም።ትንግርት ነው። ኢትዮጵያውያን ሳኡዲ አረቢያ በተረፈረፉበት ወቅት ምንም ሳይሉ በቅርቡም ለምሳሌ በኢትዮጵያ ኡጋዴን እና ጋምቤላ ወገኖቻቸው ሲጨፈጨፉ ለምን ብለው ሳይጮሁ ለአንድ ባህሪው የጫካ ለነበረ ሰው ወደጫካው ለምን ተመለሰ ብለው ሰልፍ ሲጠሩ ትንሽ  ሕሊናቸው አይወቅሳቸውም።  በአንድ ሳምንት ውስጥ የታየው ይኸው ትንግርት እነዚህ የህወሃት ደጋፊዎችም ከደደቢት አምልጠው አሜሪካ ገቡ እንጂ እነሱ ከጫካ ህግ አስተሳሰባቸው እንዳልተላቀቁ በግልጽ ያሳያል።
ሰልፍ መወጣት የሚያስፈልገው ለየትኛው ነው? በየትኛውም መስፈርት 48 ሰዓት ውስጥ ሃገር ልቀቅ ለተባለ አሸባሪ ሰሎሞን/ ወዲ ወይኒ  ድጋፍ መስጠት ጤነኛ ህጋዊ አይሆንም።ይመለስና በሕግ አሸባሪ ተብሎ  በአሜሪካ ይፈረድበት ለማለት ከሆነ ሞኝነት ነው። በዕለቱ   አጸፋ ሰልፍ ያካሄዱት ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ከፍተው ያሰሙትሁሉም ዜሮ ዜሮ” የሚለው የሰሎሞን ዘፈን ከገባቸው  ወያኔዎችና ዘፋኙም ተኳሹም ሰሎሞኖች መሃይምነትን ይገልጻል።  ሌላው ቀርቶ በህወሃት በኩል ተሰልፈው የነበሩት ለአንዴም ኢትዮጵያን አልጠሩም። የሚዘፍኑት ትግርኛ ብቻ መሆኑ በእርግጥም ኤምባሲው የህወሃት እንጂ የኢትዮጵያ እንዳልሆነ በግልጽ የታየበት አጋጣሚ ነበረ።


 ህወሃቶችና በገንዘብ የተገዙት ጥቂት ሰልፈኞች ካነገቡት ጥያቄ ውስጥ የቪየና ኮንቬንሽን ይከበር የሚልም ይገኝበታል። እነዚህ ሰዎች የቪየና ኮንቬንሽንን ጥሰው አይደለም እንዴ አቶ አንዳርጋቸውን እንዲያውም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከሌላ ሃገር ድንበር ጥሰው ያፈኑት?  እንደሚጥሱት ሰብዓዊ መብት የቪየና ኮንቬንሽን አልገባንም ከሆነ ይማሩ!!!
ኤምባሲያችንንከወሮበሎች’ ለመጠበቅ ታንክና አዳፍኔ ይፈቀድልን መሰል  መፈክር ማሰማታቸውን ስናይ በእርግጥም እነዚህ ህወሃቶች በሰለጠነው አለም የሚኖሩ እንስሳት መሆናቸውን ያረጋግጣል። ኢትዮጵያውያን ከኢምባሲያቸው ያገኙት ምንም ነገር የለም። ከየ ኤምባሲው በር ላይ  በሌሎች ሲደበደቡ ፥ ሲደፈሩ ፥ ሲገደሉ ምንም ምላሽ ያልሰጠ አምባሳደር ተብዬ ነው ያለው። በአረብ ሃገር በኢትዮጵያ ኤምባሲ በር ላይ ስትማጸናቸው የነበረች እህታችን የሞተች ሰሞን አምባሳደሩ ምንም ማድረግ ባለመቻሉ ሲመጻደቅ አይተናል። እና እነዚህ አምባሳደሮችን አንገታቸውን ይዞ ስለጉዳዩ የሚጠይቃቸው ማን ነው?
በዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ቢተኮስባቸውም ኤምባሲውን የጠየቁት ፍጹም ሰላማዊ ወቅታዊ ነው፤አምባሳደሩ አቶ ግርማ ብሩን ልናናግራቸው እንፈልጋለን ጥሩልን ፥   ኦጋዴን ጋምቤላ ለተፈጠረው ጉዳይ እንደኢትዮጵያዊነታችን ማብራሪያ እንፈልጋለን” ነው ያሉት።ለዚህ ጥያቄ የሽጉጥ ተኩስ ተገቢ አይሆንም።
አሁንም ቢሆን እኛ ኢትዮጵያውያን ኤምባሲዎቻችንን መጠየቅ እንፈልጋለን። በየወቅቱ በሃገራችን ለሚፈጠሩ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የወያኔ አምባሳደሮችን ማፋጠጥ በአሜሪካ ብቻ ሳይሆን በአውሮፓ በእስያ በአውስትራሊያም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።  እንደ አሜሪካው በሌሎች ሃገራትም  ያሉትን የኢትዮጵያን ኤምባሲ አምባሳደሮች መጠየቃችን ይቀጥላል።

ዘአብርሃም  ታዬ

No comments:

Post a Comment

wanted officials