በህዳሴ ግድብ ላይ የሚያተኩረው የሶስትዮሽ ምክክር በካይሮ ተጀመረ
በግብፅ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ መካከል የሚካሄደው የሶሰትዮሽ ውይይት ዛሬ ጠዋት ላይ በካይሮ ተጀምሯል።
በዚህ ውይይት ሶስቱ ሀገራት በውሃ ሚኒስትሮቻቸው በሚመራ ቡድን ተወክለዋል።
በግብፅ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙሃሙድ ድሪል በሶስትዮሽ ውይይት ዙሪያ ከሀገሪቱ የውሃ ሃብትና መስኖ ሚኒስትር ጋር ተነጋግረዋል።
ዛሬ ጠዋት ላይ በካይሮ በተጀመረው የሶስቱ ሀገራት የቴክኒክ ኮሚቴ ውይይትም በታላቁ የህዳሴ ግድብ የውሃ ፍሰትና የማህበራዊ ኢኮኖሚ ጥናቶችን የሚያካሂድ አለም አቀፍ ቡድን ይመርጣል ተብሎ ነው የሚጠበቀው ።
የሚቀጠረው አማካሪ ደርጅት የ20 አመታት የተመሳሳይ ስራዎችና ጥናት ልምድ እንዲሁም እንዲህ አይነት ስራዎችን በሰራባቸው ጊዜያት የነበሩት የስነ ምግባር ሁኔታም በመመዘኛዎች ይፈተናል።
የግብፅ የውሃ ሃብትና መስኖ ሚኒሰትር ሆሳም ሞግሀዚ አጥኚ ድርጅቱ በሁለት ቀናት ስብሰባ ካልተመረጠ፥ የቴክኒክ ኮሚቴው ሌሎች የመምረጫ ሁለት ሳምንታትን ተጠቅሞ ምርጫውን ያሳውቃል ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግደብ በአሁኑ ወቅት ግንባታው 40 በመቶ መድረሱን በማንሳት የዘገበው ደይሊ ኒውስ ኢጅብት ነው።
No comments:
Post a Comment