የሰማያዊ አመራሮችና አባላት ክሱን እንዲከላከሉ ተወሰነባቸው
ዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም ቀበና ፍርድ ቤት የቀረቡት 14 የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ተወሰነባቸው፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ባደረገበት ወቅት ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተ በራሪ ወረቀት ሲበትኑ በቁጥጥር ስር ውለው በየካ ፖሊስ ጣቢያ በነበሩበት ወቅት ጣቢያ ውስጥ ደንብ ተላልፋችኋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው 14 የፓርቲው አመራሮችና አባላት ዛሬ በቀበና ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ በመወሰን ለህዳር 3 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተስጥቷል፡፡
አቃቢ ህግ 14ቱ የፓርቲው አባላት በፖሊስ ጣቢያ እያሉ ‹ፍትህ የለም›፣ ‹ዴሞክራሲ የለም›፣…በማለት ጮክ ብለው ድምጻቸውን በማሰማት የጣቢያውን ደንብ እንደተላለፉ በክሱ ላይ ተመልከቷል፡፡
በመሆኑም 14ቱም የፓርቲው አመራሮችና አባላት አቃቤ ህግ የመሰረተባቸውን ክስ ከአንድ ወር በኋላ ችሎት ፊት ቀርበው እንዲከላከሉ ብይን መተላለፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
No comments:
Post a Comment