Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, October 18, 2014

ሳሙኤል ዘሚካኤል ከቀረቡበት ሶስት ክሶች ሁለቱን አመነ

ሳሙኤል ዘሚካኤል ከቀረቡበት ሶስት ክሶች ሁለቱን አመነ
 ራሱን ዶክተር ኢንጂነር አድርጎ ይጠራ የነበረው ሳሙኤል ዘሚካኤል ከተመሰረተበት ሶስት ክሶች ሁለቱን በማመኑ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈበት።
ተከሳሹ ከአምባሳደር ልብስ ስፌት ድርጅት ባለቤት ወሰደ የተባለውን 58 ሺህ ብር እንዳልወሰደ ክዶ ተከራክሯል።
በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ከቀረቡት ክሶች መካከል በ12/04/06 ቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ገርጂ አምባሳደር ልብስ ስፌት ውስጥ ተጠርጣሪው ወንጀል መፈፀሙን ይጠቅሳል።
ዶክተር ኢንጂነር ነኝ በማለት አሳሳች ቃል በመናገር የድርጅቱን ባለቤት አቶ ሰኢድ መሀመድን አጭበርብሯል የሚለው በክሱ ተመልክቷል።
"ድርጅትዎን በተለያዩ መድረኮች አስተዋውቃለሁ፤ ስኬታማ የሆኑ ሰዎችንና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ 20 ታዋቂ ሰዎች የሚካተቱበትን መፅሀፍ እያዘጋጀው በመሆኑ ድርጅትዎን በዚህ መፅሀፍ አስተዋውቃለሁ" በማለት የተሳሳተ እምነታቸውን በመጠቀም ከ58 ሺህ ብር በላይ ወሰዶባቸዋል የሚልም በክሱ ተጠቅሷል።
ከእኝህ ግለሰብ ተማሪዎችን አሰልጥኜ አስመርቃለሁ በሚል ሰበብ 4 ሙሉ ልብሶችን ቼክ ሰጥቶ መውሰዱም በክሱ ተጠቅሷል።
ከቦሌ ቅርንጫፍ ወጋገን ባንክ በተዘጋ የሂሳብ ቁጥሩ በሌለው ስንቅ የአልባሳቱን ዋጋ 6 ሺህ ብር ቼክ ፈርሞ በመስጠትም ተከሷል።
በ11/07/06 በግምት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ቦሌ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ፒኬ ህንፃ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቻይና አፍሪካ ቅርንጫፍ ተፈፀመ የተባለውን ወንጀል አቃቤ ህግ 3ኛ ክስ አድርጎታል።
ግለሰቡ የካ ክፍለ ከተማ ቤቴል ሜዲካል ኮሙኒኬሽን ኤንድ ኮንሰልቲንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚል ስም የተሰጠውን የንግድ ፍቃድ አሳይቶ ብር ለመበደር ሄዷል የሚለው ክሱ፥ ይህ ንግድ ፍቃድ ከ2004 እና 2005 ዓ.ም ምንም እድሳት እንዳልተደረገለት ይገልፃል።
ተከሳሹ ግን የሁለቱንም አመታት የንግድ ፍቃድ እንደታደሰ በማድረግ በራሱ እጅ ፅሁፍ በመፃፍና በመፈረም እንዲሁም ሀሰተኛ ማህተም በመምታት ለባንኩ አቅርቧል።
በመሆኑም አቃቤ ህግ በሀሰተኛ ሰነድ በመገልገል ወንጀል ክስ መስርቶበታል።
ተከሳሹ ከቀረቡበት ክሶች አንዱን ክዶ በመከራከሩ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ምስክር ለመስማት ለጥቅምት 25 ቀን 2007 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials