አበበም በዕለቱ ባስተላለፈው መልዕክት ያገኘነውን አጋጣሚ ሁሉ ሰፊውን ህዝብ እና የተከበረችውን ሃገራችን ኢትዮጵያን ድምፅ ማሰማት አለብን ብሏል፡፡ የምዕራባዊያን ሃገራት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ አምባገነን መንግስታትን እንደሚረዱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ እና ፖሊሲና ስትራቴጅዎቻቸውን እንዲከልሱ እንዲሁም ከሰብአዊ መብቶች መጠበቅ አለመጠበቅ ጋር በቀጥታ ማያያዝ እንደሚገባቸው በሁሉም አጋጣሚዎች ማሳወቅ ይገባልም ተብሏል፡፡