በጉራፈርዳ ወረዳ 25 አማሮች መገደላቸው ተሰማ
በደቡብ ክልል በቤንች ማጅዞን በጉራፈርዳ ወረዳ በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ የመዠንግር እና የሸኮ ተወላጆች አንድላይ በማበር የአርኛረኛ ተናጋሪዎችን እየጨፈጨፉ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካታ ሰዎች መሞታቸው ተሰማ።
(ከዚህ ቀደም ከጉራ ፈረዳ የተፈናቀሉ አማሮች፡ ፎቶ ፋይል)
ከአካባቢው የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በስፍራው ይኖሩ የነበሩት እነዚሁ አማሮች ቤት ንብረታቸውን ለቀው ወደ አካባቢው ከተሞች እየተሰደዱ ሲሆን እስካሁንም እየተፈጸሙ ባሉ ጭፍጨፋዎች 25 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል።
በቤንች ማጂ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ እነዚህን ዜጎች የጨፈጨፉት የመዠንገርና የሸኮ ተወላጆች አዳዲስ የጦር መሳሪያዎችን መያዛቸውን የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ የዜና ዘጋቢዎች ይህ መሳሪያ ለደቡብ ሱዳን ተብሎ የመጣ እንደሆነና ከጭፍጨፋው በስተጀርባ የመንግስት እጅ ሳይኖርበት እንደማይቀር የሚያሳይ ነው ሲሉ በአካባቢው ጥቃት የደረሰባቸውን አማሮች አስተያየት በመጥቀስ ዘግበዋል።
በጉራፈርዳ በተፈጠረው ጭፍጨፋ በአካባቢው ያሉ የመንግስት ወታደሮች ከመዠንገር እና ከሸኮ ተወላጆች ጋር መተባበራቸውን የሚገልጹት እነዚሁ የጥቃት ሰለባዎች ሆን ተብሎ የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት እየተደረገ ያለ ሴራ ነው ይሉታል። በጉራፈርዳ መሬታችንን ለቃችሁ ውጡ በሚል እንዲህ ያለው ጭፍጨፋ ሲፈጸም የመጀመሪያው አለመሆኑ ይታወሳል።

No comments:
Post a Comment