የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች የ8 ቀን ስልጠና ቅጣት ተጣለባቸው
የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን ለ11 ቀናት የወሰዱት የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች ስልጠናውን በደንብ አልተከታተላችሁም በሚል ተጨማሪ 8 ቀን እንዲሰለጥኑ ቅጣት እንደተጣለባቸው ሰልጣኝ ሰራተኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡
መስከረም 19/2007 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2007 ዓ.ም በተሰጠው ስልጠና 4100 የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች እንዲሰለጥኑ የተደረገ ሲሆን ሰራተኞቹ ግማሹን ቀን ሰልጥነው ግማሹን ቀን እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡ ሰራተኞቹ ‹‹ስልጠናው የዕረፍት ጊዜያችን የሚሻማ ነው›› በሚል ስልጠናውን የተቃወሙ ሲሆን ስልጠናውን አቋርጠው በመውጣትና በመቅረት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡
ይህንን ተከትሎም ስልጠናው ባለቀበት በዛሬው ቀን ‹‹እያቋረጣችሁና እየቀራችሁ ስልጠናውን በሚገባ ባለመከታተላችሁ ተጨማሪ 8 ቀን እንድትሰለጥኑ ቅጣት ተጥሎባችኋል፡፡›› እንደተባሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ሰራተኞቹ ከነገ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 8/2007 ዓ.ም በቅጣት የተጣለባቸውን ተጨማሪ ስልጠና ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ባለፉት 11 የስልጠና ቀናት ለአበል 50 ብር እንዲሁም ለባነርና ለሌሎች ቁሳቁሶች 90 ሺህ ብር በአጠቃላይ 2,345,000 (ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ አምስት ሽህ) ብር እንደወጣ የታወቀ ሲሆን በቀጣይ 8 ቀናትም ተጨማሪ የቅጣት ስልጠናም ተጨማሪ እስከ 2 ሚሊዮን የሚደርስ ገንዘብና ጊዜያቸው ሊጠፋ መሆኑ እንዳሳዘናቸው ሰራተኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

No comments:
Post a Comment