Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, October 9, 2014

የክርስትና ና እስልምና ተከታዮች ቁጥር ሲዛባ የመንግስት መልስ ከ‹‹የመለስ “ትሩፋቶች” ባለቤት አልባ ከተማ››

ስህተቱን የማያምን መንግሥት


አንድ አድርገን መስከረም 29 2007 ዓ.ም


በኢህአዴግ ውስጥ ከተራ አባልነት እስከ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታነት ድረስ ያገለገለው አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ያጸፈውን መጽሐፍ ‹‹የመለስ “ትሩፋቶች” ባለቤት አልባ ከተማ›› የሚለውን መጽሐፍ ከገጽ 367-369 ድረስ ያሰፈሯቸውን ሀሳቦች እንደወረደ እንዲህ አቅርበነዋል፡፡

ከእለታት በአንድ ቀን እንዲህ ሆነ:-በኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ከሽመልስ ከማል ጋር የጠዋት ስራችን ሀገራችንና አለም እንዴት እንዳደረች ለማወቅ ሚዲያ ሞኒተር የምናደርግበት ነበር፡፡ ይህን እየሰራን እያለ ጸሐፊዬ በኢንተርኮም ደውላ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተላ ሰዎች ሊያናግሩኝ እንደሚፈልጉ ገለጸች፡፡ እንድታስገባቸውም ነገርኳት፡፡ ሁለት ጎልማሳ እድሜ ላይ ያሉ ሰዎች ገብተውተቀመጡ፡፡ አፍታም ሳይቆዩ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጁ አቡነ ሳሙኤል ወደ ኢቲቪና ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት 
አቤቱታ እንዲያቀርቡ እንደላኳቸው ተናገሩ፡፡

ታሪኩ እንዲህ ነበር ፡-ከሁለት ቀን በፊት የእስልምና እምነት ተከታዮች በአላቸውን ለማክበር በአዲስ አበባ ስቴድዮም በዙሪያው ተገኝተው ነበር፡፡ በስፍራው የተገኝው ጋዜጠኛ ዘገባው ከ1.6 ሚሊየን በላይ ሙስሊሞች እንደተገኙ ገለጸ፡፡ በወቅቱ የስታስቲክስ ኤጀንሲ የአዲስ አበባ ህዝብ 2.7 ሚሊየን እንደደረሰ የተናገረበት ወቅት ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የክርስትና እምነት ተከታዩ ከሰማንያ ሁለት በመቶ በላይ እንደሆነ እጀንሲው አሳውቋል፡፡

በመሆኑም ሁሉም የእስልምና እምነት ተከታዮች ወደ ስቴዲዮም ወጥተዋል ቢባል እንኳ ከግማሽ ሚሊየን አይበልጥም፡፡ በዛ ላይ እንደ አቃቂ ያሉ ክፍለ ከተሞች የሚኖሩ ሙስሊሞች በአላቸውን የሚያከብሩት በአቃቂ ስታዲየም ላይ በመሰባሰብ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ያሉ የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች በተመሳሳይ በአካባቢያቸው ያከብራሉ፡፡

ሁለቱ መልዕክተኞች ይዘው የመጡት አቤቱታ ተጨምቆ ሲታይ ይህን የሚያመላክት ነበር፡፡ እርግጥም አላስፈላጊ ፉክክር በተገባበት ሁኔታ እንደዚህ አይነት ዜና መልቀቅ ተገቢ አልነበረም፡፡ በየትኛውም መንገድ ቢሆን የስህተቱ ምንጭ መንግሥት መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡ አንድም የአዲስ አበባ ሕዝብ ተብሎ የተገለጸው ልክ አይደለም ፤ አልያም በስታዲየም ተገኝ የተባለው ተጋኖ ቀርቧል፡፡ቅሬታ አቅራቢዎቹ ያነሱት ጥያቄ ተገቢነት ያለው መሆኑን ገለጽን፡፡ አጣርተን ምላሽ እንደምንሰጥ ቃል ገብተን አሰናበትናቸው፡፡ እያለ ደራሲው ይቀጥላል….ቀጥሎም
‹‹ በዜና መልኩ ወደ እርምት መስጠት ብንገባ የፖለቲካ ስራችን ይበላሻል፡፡ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በአሉ ያለምንም ችግር በመቶ ሺዎች ወጥተው ማክበራቸውን ፤ ይህም በእንከን የለሹ ህገ መንግስት የተገለጸው የሃይማኖት ነጻነት እውን መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ የሚያመላክት ጽሑፍ እንላክላቸው፡፡ የቅዳሜ የኢቲቪ ህትመት ዳሰሳ በዚህ ላይ ሰፊ ትንታኔ እንዲሰጥ አቅራቢዎችን ጠርተን ኦሬንቴሽን እንስጣቸው  ፡፡ ደጋግመው በመቶ ሺዎች በተገበት እያሉ ይናገሩ›› አልን፡
እነሆ የስምኦን ልጅ በረከት ያዘዘንን አደረግን፡፡ አዲስ ዘመን መቶ ሺዎች በተገኙበት በድምቀት እንደተከበረ የጻፍንላትን ለህትመት አበቃች፡፡ የህትመት ዳሰሳ ቋሚ ተሰላፊው ሚዛን ከአሸብር ጋር ሆነው መቶ ሺዎች ሲሉ ዋሉ፡፡ ይህም ሆኖ በሚዲያና ማህበራዊ ድረ ገጾች መብጠልጠሉ ግን አሁንም አላባራም፣፣…… ይለናል  አቶ ኤርሚያስ ለገሰ

በየጊዜው በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የሚወጡ ጽሑፎች መልስ ይኑራቸውም አይኑራቸው ፤ ለበላይ አካል እንደሚደርሱ ከዚህ ጽሁፍ ለመረዳት ችለናል፡፡(የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር በማዕተብ ዙሪያ ለተነሳው ሃሳብ ማስተባበያ እንደሰጡት)፡፡  አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ካነሷቸው ሃሳቦች ጋር በተመለከተ አንድ አድርገን ይዛ ከወጣችው ጽሁፎች ውስጥ አንዱን ለማንበብ ይህን ይጫኑ፡፡





ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበብ

(አንድ አድርገን ሰኔ 19 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በርካታ ጊዜያት መንግስት እና አለማቀፋዊ ተቋማት የቁጥር ነገር አያስማማቸውም ፤ IMF ወይንም World Bank የሀገሪቱ እድገት በዚህኛው ዓመት 6 ከመቶ አይበልጥም ብሎ ሲተነብይ መንግስት ደግሞ “አይሆንም እኛ ለተከታታይ 6 ዓመታት 11.2 በመቶ ነው ያደግነው” በማለት ዓመታዊ ያልተሰላ ሂሳብ ያቀርባል እና በየዓመቱ ሰኔ አልፎ ሀምሌ ሲመጣ የቁጥር ነገር ዋናው የመከራከሪያ ያለመስማሚያ ነጥብ ሆኖ መመልከት የዘወትር ተግባራችን ከሆነ ሰንበትበት ብሏል፡፡ አሁን እኛ አነሳሳችን ስለ እንደዚህ ዓይነት ነገር ለመናገር አይደለም  ፤ ባይሆን ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ ይህ “የቁጥር ነገር” በሙስሊም ወንድሞቻን ዘንድ እንዴት እየቀረበ መሆኑን ለማስገንዘብ እና ለማሳየት በማሰብ ነው “የቁጥር ነገር” በማለት የተነሳነው፡፡


ከጥቂት ቀናት በፊት የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ላይ “እስልምና በኢትዮጵያ” የሚል የእስልምና በኢትዮጵያ አመሰራረት ከስነ መሰረቱ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ያለውን አመለካከት በምሁራን አንደበት ሰፊ ትንታኔ በመስጠት ሰዎች እንዲያውቁ የማድረግ ፕሮግራም በመስራት ላይ ይገኛል ፤ ተጋባዥ እንግዶች በእምነቱ ውስጥ የተለያየ የስልጣን ተዋረድ ላይ ከሚገኙ የሃይማኖት ሰዎች በተጨማሪ በእስልምና እምነት ላይ የዶክትሬት ወረቀታቸውን የሰሩ ሰዎች ይገኙበታል፤ በዚህ ወቅት በእውቀት ደረጃ ያወቅናቸውንና የታዘብናቸውን ነገሮች አሁን ካለንበት ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማመሳጠር ለማቅረብ አንወዳለን ፤ የመጀመሪያው ሙስሊም ወንድሞቻችን “ኢትዮጵያ ውስጥ የነገሠ የእስልምና ሃይማኖትን የሚከተል ንጉስ” እንደነበር ዘወትር በመገናኛ ብዙሃን ፊት በመቅረብ ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነገር ሆኗል ፤ ነገር ግን በዚህ የውይይት መድረክ ላይ እንደተገነዘብኩትኝ ኢትዮጵያ ውስጥ የእስልምናን እምነት ተከታይ የነበረ ንጉስ እንዳልነበረ  ፤ ይህን ንጉስ አለ ብለው የሚሉ ሰዎች ካሉ መሰረታቸው አፈ-ታሪክ እንጂ የሚጨበጥ ማስረጃ እንዳልተገኝለት ጭምር ነው ፤ ነገሠ የተባለበት ዘመን ትንሽ ራቅ ስለሚል በዚያን ጊዜ የነበረ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ጸሀፊዎች የተጻፉ መዛግብት ማግኝት አልተቻለም ፤ ይህ ንጉስ ነገሰ በተባለበት ዘመን አነጋገሡን ፤ ማንን እንዳገባ ፤ ምን ያህል ልጆች እንደወለደ ፤ ልጆቹ የእርሱን ንግስና ለምን እንዳልተቀበሉ እና ለትውልድ ለምን እንዳላስተላለፉ የሚገልጥ ይህ ነው የሚባል ማስረጃ ማግኝት አዳጋች መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ አሁን የማንንም ታሪክ ለመደምሰስ ወይም እንዳልተደረገ ሆኖ ለማቅረብ ሳይሆን ያልተደረገን እና በዘመኑ ያልተከናወነን ነገር ከ15 ክፍለ ዘመን በኋላ በመነሳት እኛም ነገስታት ነበሩን ማለት በታሪክም ተጠያቂ ስለሚያደርግ ይህ ነገር እንደዚህው በቀላሉ መታየት የለበትም የሚል አቋም አለን፡፡

ባለን መረጃ መሰረት በትግራይ አካባቢ የሚገኝው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው መስጂድ እንደሆነ የሚነገርለት አል-ነጃሺ መስኪድን ከላይ ካልነው የፈጠራ ታሪክ ጋር በማመሳጠር የሀገሪቱ እና የዓለም ቅርስ ሆኖ እንደ ላሊበላ አክሱም እና መሰል አድባራት የማስመዝገብ ስራ መጀመሩን ነው፡፡ እኛ ይህ መስጂድ በታሪክነት መመዝገብ የለበትም የሚል ጭፍን አመለካከት የለንም ፤ ነገር ግን መመዝገብ ያለበት በጊዜው የነበረው ታሪክ መነሻ በማድረግ ሳይጨመርና ሳይቀነስ መሆን መቻል አለበት የሚል የጠራ አቋም አለን ፤ ክርስትትያኑ ታሪክ እንዳለው ሁላ ሙስሊሙም የራሱ ታሪክ አለው ፤ ነገር ግን ያልተደረገን ታሪክ ለፉክክር መጨመር ታሪክን ከማጉደፍ በተጨማሪ ወደፊት የሚያመጣው የታሪክ መፋለስ ስለሚኖር መታሰብ ያለበት ጉዳይ መሆን መቻል አለበት፡፡

በመቀጠልም በዚህ “እስልምና በኢትዮጵያ” የሚል ተከታታይ ፕሮግራም ላይ አንድ በአሁኑ ሰዓት የሙስሊሙን ጥያቄ መንግስት ዘንድ እንዲያቀርብ ከተመረጡት ሰዎች ውስጥ ስለ አንዋር መስኪድ ስለተሰበሰበው የአማኝ ብዛት ሲናገር እንዲህ በማለት ነበር “በዛሬው እለት ከግማሽ ሚሊየን በላይ ኢስላም በመርካቶ አንዋር መስኪድ በመሰብሰብ ከስግደት በኋላ ተቃውሞውን ማሰማት ችሏል”በማለት ሲናገር በመስማታችን በጣም ተገርመናል ፤ ሲጀመር አዲስ አበባ ውስጥ በባለፈው ሀገራዊ የህዝብ ቆጠራ ስሌት ከ2.8 ሚሊየን በላይ ሰዎች በከተማይቱ ይኖራሉ ብሎ ያስቀምጣል ፤ ታዲያ ከዚህ ቁጥር ውስጥ74 በመቶ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አማኝ ሲሆን ፤ 16 በመቶ ደግሞ የእስልምና ሃይማኖት አማኞች መሆናቸውን ያስቀምጣል ፤ እኛ ለሂሳብ እንዲያመቸን የከተማዋ ነዋሪ 3.5 ሚሊየን ብናደርሰው እንኳን ሁሉም ሙስሊም ከቤቱ ወጥቶ አንዋር መስኪድ ቢሰበሰብ 560 ሺህ ህዝብ ነው የሚሆነው ፤ ይህ ደግሞ የማይታሰብ ነው ፤ እንዲው የውስጥን መሻት ከመግለጽ አኳያ ካልሆነ በቀር ያልሆነ እና ያልተደረገን ነገር በመገናኛ ብዙሃን ብዙሀንነትን ለመግለጽ መናገር ራስን ትዝብት ላይ ስለሚጥል ጠንቀቅ ማለቱ የተሻለ ይመስለናል ፡፡


Based on the 2007 Census conducted by the Central Statistical Agency of Ethiopia (CSA), Addis Ababa has a total population of 2,739,551, of whom 1,305,387 are men and 1,434,164 women; ......The religion with the most believers in Addis Ababa is Ethiopian Orthodox with 74.7% of the population, while 16.2% are Muslim, 7.77% Protestant, and 0.48% Catholic.[17]   

የዛሬ ሁለት ዓመት ‹‹አረፋ›› በዓላቸውን ሲያከብሩ እንደተለመደው በጠዋት አዲስ አበባ ስታዲየም በመሄድ የስግደት ስርአታቸውን እያከናወኑ ነበር ፤ በጊዜውም በቀጥታ በሚደረግ ስርጭት ላይ የኢቲቪ ሙስሊም ዘጋቢ እንዲህ ብሎ ነበር “ በዛሬው እለት ከ1.5 ሚሊየን የሚበልጡ ሙስሊሞች በስታዲየም እና በዙሪያው በሚገኙ ቦታዎች ላይ በመገኝት በአሉን በደማቅ ሁኔታ እያከበሩ ነው” በማለት ሲናገር ፊቱ ላይ የማፈር ወይም የመሸማቀቅ ሁኔታ በፍጹም አይታይበትም ፤ በመሰረቱ ስታዲየሙ ሰዎች የሚቀመጡበት ቦታ ቢሞላ መቀመጫው ብቻ 40 ሺህ ሰው መያዝ አይችልም ፤ ሜዳው ከ10 ሺህ ሰው በላይም መስተናገድ አይችልም ፤ በስታዲየሙ ዙሪያ አስር የስታዲየምን ቦታ የሚያክል ህዝብ መስገድ ቢችል እንኳን ከግማሽ ሚሊየን የማይበልጥ ቁጥር እናገኛለን፤ ይህ ማለት እኛ እጅጉን አጋነነው ነው እንጂ የዚህን ግማሽ ሰው ከወጣ ራሱ ብዙ የሚባል ቁጥር ነው ፤ እየሆነ ያለው ነገር ግን የራስን ቁጥር ከክርስትያኑ ጋር በማስተያየት ለራስ የተሻለ እይታን ለመፍጠር የሚደረግ ነገር መሆኑን ለማወቅ ያችላል ፤

መንግስትም ይህን ለምን ? ብላችሁ ብትጠይቁ “የሃይማኖት እኩልነት” የምትለውን አንቀጽ ከህገ መንግስቱ ላይ በመምዘዝ መልስ ይሰጣል  እንጂ ስለ ተባለው ቁጥር ትክክለኝነት ዘጋቢውን የሚጠይቅበት አግባብ የለውም ፤ ይህ ማለት ከአዲስ አበባ ነዋሪ 50 በመቶ ሙስሊም ነው እያሉን ነው ፤ እርስዎ ይህን ነገር እንዴት ያዩታል ? በመሰረቱ በአዲስ አበባ ውስጥ በመስኪድ ቁጥር ከ100 ካሬ እስከ ከ5ሺህ ካሬ በላይ ስፋት ያላቸው ከ150 በላይ መስኪዶች እንዳሉ እሙን ነው ፤ ከእነዚህ ውስጥም 70 በመቶ የተሰሩት ባሳለፍነው 10ት አመታት ውስጥ ነው ፤ የኦርቶዶክስት ቤተክርስትያን በ1826 ዓ.ም በመጀመሪያ ከተመሰረተው የቀራንዮ መድሃኒአለም ቤተክርስትያን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያሉት ከ132 አይዘሉም ፤ ይህ አሁን መሬት ላይ ያለ እውነታ ነው ፤ ይህ የአማኝ ቁጥር ግን ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው ፤ የኤፍ ኤም ጣቢያዎቻችን እና ብቸኛው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና መሰል የመገናኛ ጣቢያዎች  በቁጥር ጉዳይ ላይ መጠንቀቅ ይገባቸዋል የሚል እምነት አለን፡፡

ይህ እይታ የ“አንድ አድርገን” ብሎግ አዘጋጆችን ብቻ የሚወክል ነው፡፡ 
http://andadirgen.blogspot.de/2012/06/blog-post_26.html

No comments:

Post a Comment

wanted officials