ኣቶ ልጃለም ካልኣዩ በኣዲስ ኣበባ በዘብኝነት ተቀጥሮ እየሰራ በነበረበት መስርያ ቤት 21/ 01 / 2007 ዓ/ም እሮብ ማታ 05:30 ሰዓት በመስርያ ቤቱ በመኪና ተግጭቶ እንዲሞት ተደርጓል።
ኣቶ ሊጃለም በደቡባዊ ዞን፣ እንዳመኾኒ ወረዳ፣ ነቕሰገ ቀበሌ፣ ወዲ ሰብሮ በምትባል ሰፈር ተወልዶ ያደገ ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓቱም በዚቹ ሰፈር ተከናውነዋል።
ኣቶ ልጃለም ካልኣዩ በኣውቶሞቲቭ ዲፕሎማ የተመረቀና በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ከኢትዮዽያ ሰራዊት ጎን ተሰልፎ ኣገራዊ ግዴታው በጀግንነት በመወጣት በእጁ የተወሰነ ጉዳት ደርሶት ነበር።
በ2002 ዓ/ ም ዓረና-መድረክ በመወከል ለክልል ምክር ቤት በእንዳመኾኒ ወረዳ እጩ ተወዳዳሪ እንደነበር ይታወቃል።
ከምርጫ ብሗላ ዓረና በመሆኑ በሞያው ስራ ሊቀጠር ባለ መቻሉ ኣዲስ ኣበባ ሂዶ በዘበኝነት ተቀጥሮ እየሰራ ባለበት ሁኔታ ነው በመኪና ተግጭቶ ለህልፈት የበቃው።
በ2002 ዓ/ም የህወሓት/ኢህኣዴግ መንግስት ዓረና-መድረክ ለፈዴራል ምክርቤት እጩ ተወዳዳሪ የነበረው ኣቶ ኣረጋዊ ገብረዮውሃንስ በቢላ ታርዶ እንዲ ገደል ማድረጉ የሚታወስ ነው።
ባሳለፍነው ሳምንት የዓረና ስራ ኣስፈፃሚ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን ሃላፊ የሆኑት ኣቶ መሰለ ገብረሚካኤልም የግድያ ዛቻ እየደረሳቸው ነው።
ኣቶ ልጃለም ካልኣዩ በ2005 ዓ /ም የዓረና 3 መደበኛ ጉባኤ ማእከላይ ኮሚቴ ኣድርጎ መርጦት ነበረ።
ኣቶ ልጃለም ሂወቱ እስክታልፍ ድረስ ጠንካራ የዓረና ኣመራር ሁኖ ዘልቋል።
ጓዳችን እንዲህ በኢትዮዽያ ኣገርህ ለፍትህ፣ ዲሞክራሲ፣ ነፃነት፣ለህግ የበላይነትና ሉኣላዊ ክብርዋ ለማጎናፀፍ እየታገልክ በማለፍህና የጀግና ሞት በሞመትህ ሃዘንም ኩራትም ይሰማናል። መላ የዓረና ኣባላት ከኢትዮዽያ ህዝብ ጎን ተሰልፈው ኣንተ የሞትክለት ዓላማዎች ሁሉ እውን ለማድረግ ቆርጠው ትግላቸው ይቀጥሉታል።
እግዝኣብሄር ነፍስህ መንግስተ ሰማያት ያዋርሳት።
ድል ለኢትዮዽያ ህዝብ...!
ንውፃነታችን በእጃችን ነው...!
No comments:
Post a Comment