Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, October 29, 2014

ወዳጃችን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (በአቤ ቶኪቻው)

ወዳጃችን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (በአቤ ቶኪቻው)

teme
ወዳጃችን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ከተከሰሰባቸው ክሶች በአንደኛው ሶስት አመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት።
በሌሎቹ ክሶች ምን እንደሚፈረድበት ቀጥሎ የምናየው ቢሆንም ተሜ እና ሌሎች ወንጀለኛ ያልሆኑ ሰዎችን… (ይሄን ግዜ አንዳድ አብዝተው የዋህ የሆኑ ሰዎች እና አብዝተው የኢህአዴግ ዝምድናን የተጋመዱ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ወንጀለኛ ያላቸውን ሰዎች ከወንጀል ነጻ ናቸው ማለት ተገቢ ነውን… እያሉ ሊሞግቱን ጣታቸውን ሲያሞጠሙጡ ይታየኛል… ነገር ግን አሁን አሁን በሀገራችን ሰርቆ እና ደብድቦ ከሚታሰረው ”መልካም ሁኑ ጥሩ ሁኑ ተዉ ኋላ ይቆጫችኋል” ብሎ መክሮ እና ገስጾ የሚታሰረው እየበዛ መሆኑን ለማረጋገጥ ቃሊቲ ቂሊጦ እና ዝዋይን አየት አየት ማድረግ በቂ ነው….) እና ተሜ እና ሌሎች ወንጀለኛ ያልሆኑ ሰዎች እስር ቤቱን መሙላታቸው የአሳሪያቸውን አሳር ያበዛ እንደሆነ እንጂ ለእነርሱማ ብርቃቸው አይደለም፤
ለምሳሌ ተሜን እንውሰድ… ገና ፍትህ ጋዜጣ ስትጀምር ጀምሮ ከሀገር እንዲወጣ ወይም ደግሞ ከአንደበቱ መንግስትን የሚያስከፋ እንዳያወጣ በተለያዩ ሰዎች ሲያስመክሩት ነበር። እርሱ ግን ”ሌላ ሀገር የለኝም” መንግስትን መምከርም ሀላፊነቴ ነው፤ ብሎ ፍንክች የአባ ቢላው ልጅ ሆነ! ከዛም አልፎ ተርፎ በአንዱ ሲዘጉበት በሌላው እየከፈተ ለሁላችንም መተናፈሻ መድረክ ፈጠረልን… መተንፈሳችን የሚያመው መንግስታችን… በመጨረሻም ተሜን ”ለምን ጻፍክ” ብሎ ከሰሰው
እስከ አሁን ባለው ልምድ መንግስታችን ጸሀፊያንን ወይም ፖለቲከኞችን አልያም አሳቢ ግለሰቦችን የሚያስረው ለምን ጻፋችሁ ለምን ፖለቲከኛ ሆናችሁ ወይም ለምን አሳቢ ሆናችሁ ብሎ አልነበረም፤ ይልቅስ ወይ ከኦነግ ወይ ከኦብነግ ወይ ከግንቦት ሰባት ወይ ከአርበኛ ወይ ደግሞ ”ከአንዳንድ የወጪ ሀይሎች” (እነዚ የውጪ ሀይሎች እንማን እንደሆኑ ግን እስከዛሬ ግልጽልጽ ብሎ አልተከሰተልንም…!) ተገናኝተዋል ዶልተዋል እያለ ነበር የሚያስረው። ተሜን ግን በግልጹ በዚህ ግዜ እንዲህ ብለህ ጽፈሃል በዚህ ግዜ ይሄንን ብለሀናል በሚል በሌላ አባባል ለምን ይናገረናል በሚል ክስ ነው ለእስር የዳረጉት።
የሆነው ሆኖ አሳሪዎቻችን ራሳቸው ሞቅታው ጋብ ቢልላቸው የማይክዱት ሀቅ እስር ቤቱን የምንግስት ብልግና ተቃዋሚዎች እየሞሉት መሆኑን ነው። ለሁሉም ነገር ልክ አለውና እስር ቤቱ ልኩ ደርሷል ያኔ ይሞላል፤ ሲሞላ መፍሰሱ አይቀርም። እስር ቤት ሞልቶ ሲፈስ ደግሞ ቦንድም ቦንብም የማይገድበው ጎርፍ ይፈጠራል።
ልባም መንግስት ቢኖር ከሚመጣው ጎርፍ ራሱን ይጠብቅ…!
EMF

No comments:

Post a Comment

wanted officials