በአዋሽ ወንዝ ሙላት ጉዳት የደረሰባቸው የአፋር ተወላጆች የድረሱልን ጥሪ እያቀረቡ ነው
በአስር ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ በውሃ ሙላት ህይወቱ ለአደጋ ተጋልጦ በሚገኝበት ወቅት ከመንግስት የሚቀርብላቸው ድጋፍ አነሳ መሆኑን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
ከውሃ ሙላቱ የተረፍነዎች በምግብ እጦት እየተሰቃየን በመሆኑ መንግስት በአፋጣኝ ይደረስልን ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል። አፋጣኝ መልስ ካልተሰጠም እስካሁን ከታየው በላይ አስከፊ የሆነ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ተፈናቃዮች አስጠንቅቀዋል።
ከአፋር ህዝብ እንደተወከሉ የሚገልጹ የአገር ሽማግሌዎች በጎርፉ ከ87 ያላነሱ ሰዎች መሞታቸውንና ከ500 ያላነሱ የደረሱበት አለመታወቁን ለቀይመስቀል ሪፖርት ቢያደርጉም፣ መንግስት ግን የሞተ ሰው የለም በማለት እያስተባበለ ነው። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ችግሩ ከአቅሙ
በላይ መሆኑን ለፌደራል መንግስቱ ማመልከቱ ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment