በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል በርካታ የኢንተርኔት ቤቶች ተዘጉ
ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሃረርና የድሬዳዋ ወኪሎች እንደዘገቡት ከጥቅምት 17 ጀምሮ ከአዲስ አበባ የመጡ የፌደራል የጸረ ሽብር ግብረ ሃይል አባላት መሆናቸውን የገለጹ እንዲሁም የፌደራል ፖሊሶች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የኢንትርኔት ቤት ባለቤቶችን ይዘው በማሰር ወደ ማእከላዊ እስር ቤት ወስደዋቸዋል። ድርጅቶቻቸውና ቤቶቻቸው የተፈተሹባቸው ሲሆን፣ ንብረቶቻቸውም ተጭነው ተወስደዋል።
በሀረር በገሊል ህንጻ ላይ የሚገኘው የአሜን ፕሮዳክሽን ባለቤት አቶ ገብረ ሂወት ተገኝ፣ ካናል ህንጻ ላይ የሚገኘው የሃኒ ኮምፒዩተር ሲስተም ባለቤት አቶ አብዱ ማለኪ ማሃመድ፣ ራስ ሆቴል ህንጻ ላይ የሚገኘው የጀጎል ሹገል ኢንተርኔት ካፌ ባለቤት አቶ መሀመድ እንዲሁም ሞቢል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የሳሌም ፕሮዳክሽን ባለቤት ፓስተር ኤልሳቤጥ ጥቅምት 17 ቀን 2007 ዓም ከአዲስ አበባ በመጡ የፌደራል ፖሊስ አባላት ተይዘው ተወስደዋል። በአሁኑ ሰአት ማእከላዊ መወሰደቻውም ታውቋል።
በድሬዳዋ በተመሳሳይ በርካታ የኢንተርኔት ባለቤቶች መያዛቸውን ዘጋቢያችን ገልጿል።

No comments:
Post a Comment