አንድነት ፓርቲ በእስር ላይ የሚገኙት አመራሮቹ ኢሰብአዊ ድርጊት እንደተፈጸመባቸው አስታወቀ
ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ለአንድ ሳምንት ያክል በታሰረበት ክፍል ውስጥ እንዲጸዳዳ መደረጉን፣ ለ3 ቀናት በጨላ ክፍል ውስጥ ታስሮ የበቀል እርምጃ እንደተወሰደበት ፓርቲው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆነው አቶ ዳንኤል ሽበሺ ደግሞ በታፈነ ክፍል ውስጥ እንዲቀመጥ መደረጉን፣ በተቅማጥና በሌሎች በሽታዎች እየተሰቃየ ቢሆንም መጸዳጃ ቤት እንዳይሄድ መከለክሉን የገለጹት የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ በላይ ፍቃዱ፣ ይህን የበደል ዘመን ህዝቡ በቁጭት ለለውጥ መነሳት አለበት ብለዋል።
በአንድነት ፓርቲ አመራሮች ላይ የሚደርሰውን ስቃይ በተመለከተ የማእከላዊ እስርቤት ሃላፊዎችን ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። ከአቶ ሃብታሙና አቶ ዳንኤል ሽበሺ ሌላ ፣ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት አቶ አንዱአለም አራጌና ናትናኤል መኮንን አሁንም በእስር ላይ ናቸው።
No comments:
Post a Comment