ኢህአዴግን በማይደግፉት ዘንድ ስጋት ፈጥሯል
በምስራቅ ጎጃም ዞን የአርሶ አደሮች የመሬት ይዞታ ደብተር እየተሰበሰበና መሬት እየተቆጠረ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ የመሬት ይዞታ ደብተሩ የሚሰበሰበው ‹‹ምርጫው እየተቃረበ በመሆኑ አርሶ አደሮችን ለማፈንና ለማንገራገር ያመች ዘንድ›› ነው ያሉት ምንጮቹ ኢህአዴግን የማይመርጥ አርሶ አደር መሬቱን ሊነጠቅ ይችላል ተብሎ በስፋት እንደሚወራ ጠቁመዋል፡፡ ይህም ኢህአዴግን በማይደግፈው አርሶ አደር ዘንድ ስጋት እንደፈጠረ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁሉም ወረዳዎች በወል መሬት ይዞታ ያላቸውና ቤት የሰሩ አርሶ አደሮች ከይዞታቸው ውጭ መሬት የያዙ በማስመሰል በፍ/ቤት በፍታብሔርና በወንጀል በፈጠራ ክስ እንደሚጠየቁ የብአዴን ካድሬዎች እያስፈራሩ መሆናቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡