በጋምቤላ ጉዳይ የጠቅላይ ሚ/ር ኃይለማርያም ንግግር አንድምታ
ተስፋሁን አለምነህ
“በጉዳዩ እጃቸው አለበት ያላቸውን የመንግሥት ባለስልጣናት ላይ እርምጃ እንወስዳለን፡፡ ጠባብ እና ትምክተኛ የሆኑ ኃይሎች ናቸው ጉዳዩን የሚያራግቡት በቀጣይም እርምጃ እንወስዳለን!!”
ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ በጋምቤላ በአማራ ብሄር ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደተፈፀመ ከዘር ማጥፋቱ የተረፉ ወገሄቻችንም መኢአድ አቅሙ የቻለውን ሁሉ ከሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጋር ቁስለኞችን አሳክሟቸዋል ከሠውነታቸው ጥይት እንዲወጣላቸው አድርጓል፡፡
ቦታው ድረስ በመሄድ ለዓለም አስታውቋል፡፡ በተደጋጋሚ የአቋም መግለጫዎችን አውጥቷል፡፡ የተቃውሞ ሠልፍም ጠርቷል፡፡ መኢአድ ሌሎች ሃቀኛ ተቃዋሚዎች እስከአሁን ምንም አላሉም፡፡
ታዲያ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር በቀጥታ መኢአድ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ጠባብ የምትለዋ ከየት እንደተጨመረች ባይገባንም ትምክተኛ የምትለው ቃል ግን በወያኔ አጠራር ለመኢአድ እና ለአማራ የተለመደች ናት፡፡ ይሁን እንጂ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር እርስ በርሱ ይጋጫል፡፡ እጃቸው ያለበት የመንግሥት ባለስልጣናት እርምጃ እንወስዳለን፡፡ ይህ ማለት መንግሥት በጉዳዩ ላይ እጁ አለበት ማለት ነው፡፡ ታዲያ መኢአድ ጉዳዩን መንግሥት ነው የሚፈፅመው ቢል ምን ላይ ነው ስተቱ?
ለምንስ እርምጃ ይወሰድበታል? ታዲያ ይህን የመሠለ አይን ያወጣ እና አሳፋሪ እና አሳዛኝ የሆነ ድርጊት ካልተቃወምን ምኑን ልንቃወም ነው?
ሌላው ጠቅላይ ሚኒስትር የብሄር ግጭት ለማስነሳት የሚጥሩ ብለው የገለፁት መኢአድ በኢትዮጵያ ምድር አማራ እንዳይኖር እና ዘር ለማጥፋት እየተሠራ ያለው ድርጊት ይቁም ማለት ምኑ ላይ ነው ብሄር ከብሄር ማጋጨት የሚሆነው?
የመዥንገር ጐሳ ጡረታ በወጡ የወያኔ ካድሬዎች መሬታቸውን እየተነጠቁ ነው ማለት ምኑ ላይ ነው ብሄርን ከብሄር ማጋጨት የሚሆነው?
ምስጋና ይግባቸውና ኢሳት ቴሌቪዥን፣ ጀርመን ሬዲዮ ለህብር ሬዲዮ ሶሻል ሚዲያው ጉዳዩን በትክክል መኢአድን ምንጭ አደርገው በትክክል ዘግበውታል፡፡
ታዲያ ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ የተፃፈላቸውን እያነበቡ ሃቁን ገደል ከተው ፉጨትና ማቅራራት ምን አመጣው?
ሰበብ ፈልጐ እንደለመዱት ሠላማዊ ተቃዋሚዎችን ጨርሶ ለማጥፋት ካልሆነ፡፡ እንደቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር መረጃ ማስረጃ እያልን አንራቀቅም፡፡
በቂ ማስጃ አለን፡፡ በጋምቤላ ከ540 በላይ ንፁሀን አማሮች ተገድለዋል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቆስለዋል፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሃብት ንብረታቸው በግፍ ተቃጥሎባቸዋል፣ ተፈናቅለዋል፡፡ ብዙ ቁጥር ያላቸው መዥንገሮች መሬታቸውን በወያኔ ካድሬዎች ተቀምተዋል፡፡
ታዲያ ሃቁን ተቀብሎ ስህተትን አምኖ ስህተትን ለማረም መጣር ሲገባ የሃገርን የቁልቁል ጉዞ ማፋጠን ምን ይሉታል?
እንዴት ሃገርን ያህል ነገር አስሮ ሃገርን መምራት ይቻላል፡፡ በርግጥ እንደወያኔ ያለ ፍፁመ የለየለት አባገነን ቡድን (መንግስት) ሁሉንም ነገር በመደፍጠጥ መፍትሄ የሚያመጣ እና ስልጣን የሙጥኝ ብሎ የሚይዝ ይመስላቸዋል፡፡
የሆነው ሆኖ የጠቅላይ ሚ/ር ንግግር ከጀርባው በመኢአድ ላይ እንዲት የተሸረበ ተንኮል እንዳለ በግልፅ ያሳያል፡፡
ያሉትን ይበሉ ተቃውሞአችን እንቀጥላለን በቅርቡ ለሚደረገው ሰልፉም አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረግን ነው፡፡ ፀረ-ኢትዮጵያኖች በትግላችን ድል እንደምናደርጋቸው ለአንድም ሰከንድም ቢሆን አንጠራጠርም፡፡
አንዲት ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
No comments:
Post a Comment