Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, October 18, 2014

በዳርፉር ሶስት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ተገደሉ

በዳርፉር ሶስት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ተገደሉ

በሰሜን ዳርፉር ኮርማ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የውሃ ጉድጓድ ሲጠብቁ ከነበሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 2ቱ ወዲያውኑ ሲገደሉ አንደኛው በጽኑ ቆስሎ የነበረ ቢሆንም፣ ትንሽ ቆይቶ ህይወቱ አልፎአል።
በሱዳን ዳርፉር ግዛት በሰላም ማስከበር ላይ የነበሩት በተባበሩት መንግስታት ድርጅትና በአፍሪካ ህብረት የጋራ የሰላም ማስከበር ተልዕኦ ውስጥ የሚገኙት ሶስቱ የኢትዮጵያ ወታራደሮች ኮርማ በተባለ አከባቢ ለአንድ የውሃ ተቋም ጥበቃ እያደረጉ ነበር።
የመንግስታቱ ድርጅት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በአከባቢው ተኩስ በመክፈት ወታደሮቹን መግደላቸውን አስታውቋል።
የፀጥታው ምክርቤት ግድያውን ባወጣው መግለጫ አውግዟል።
ምክር ቤቱ በመግለጫው በወታደሮቹ ሞት የተሰማውን ሀዘን ለሟች ቤተሰቦችና ለኢትዮጵያ መንግስት ገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ባንኪሙን በሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ ላይ የተፈፀመውን ድርጊት ተቀባይነት የሌለውና ዓለም አቀፍ ህግጋትን የተላለፈ ብለውታል።
በሱዳን ዳርፉር ግዛት ተቀስቅሶ የነበረውን ግጭት ለማስቆም ለተሰማራው የመንግስታቱ ድርጅትና የአፍሪካ ሀብረት የጋራ ሰላም አስከባሪ ተለዕኮ ኢትዮጵያ በአጠቃላይ 2 ሺህ 500የሚሆኑ ወታደሮችን አውጥታለች።

No comments:

Post a Comment

wanted officials