Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, October 5, 2014

/አስደንጋጭ ዜና/ ማዕተብ ማሰር ሊከለከል ነው!

ሚኒስትር ሺፈራው: በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የክርስቲያንነት መታወቂያችንን ማዕተብ ከማሰር እንደምንከለከል አስታወቁ፤ ማዕተባችንን እናጥብቅ!

  • ከሥልጠናው ተሳታፊዎች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሟቸዋል፤ ከሥራ ባልደረቦቻቸውም ጠንካራ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል፡፡
  • ‹‹በሴኩላሪዝም ሰበብ ማዕተብኽን በጥስ ማለት ሃይማኖትን ከማስካድና እንደ ሰቃልያነ አምላክ አይሁድ መስቀሉን ለመቅበር ከመሞከር ተለይቶ አይታይም፡፡ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እና ታሪካዊ ትውፊት እንዳይፋለስ የመጠበቅና የማስጠበቅ ሓላፊነት ያለበት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥንቃቄ ሊከታተለው ይገባል፡፡›› /የሥልጠናው ተሳታፊዎች/
  • ‹‹ፈትል አንድነት እየሸረቡ ለክርስትና ሕይወት መግለጫ በክርስትና ጥምቀት ጊዜ አንገት ላይ ማሰር በቤተ ክርስቲያናችን የጸና ኾኖ ሲሠራበት ይኖራል፡፡›› /የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ/
*              *             *
  • ‹‹ሚኒስትሩ የመንግሥትን ሴኩላርነት ለማረጋገጥ በሚል የሰጧቸው አስረጅዎች የግልጽነትም የአግባብነትም ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ የሚበዛው ኢትዮጵያዊ አማኝ ከመኾኑ አንፃር ትርጉም እንዳለውና በሕገ መንግሥቱ እምነት ነክ ድንጋጌዎች እንደተንጸባረቀ ከሚታመነው የሴኩላሪዝም ፈርጅ (positive secularism) ይልቅ በርእዮትና አሠራር የተደገፈ ሃይማኖትንና ሃይማኖተኝነትን የማዳከም (negative secularism) አዝማሚያዎች ያይልባቸዋል፡፡ ከእምነት ተቋማት ጀርባ የግንባሩን አባላት ጨምሮ ሰፊው አማኝ ሕዝብ መኖሩን ታሳቢ ያደረገ ‘በነፃነት ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ መስተጋብር’ እንደሚኖር በመንግሥት የኢንዶክትሪኔሽን ጽሑፎች ከተቀመጡት አቅጣጫዎች ጋራም የሚጣጣሙ አይደሉም፡፡ በተለይ ከቤተ ክርስቲያናችን አንፃር ለተነሡ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ፣ በፓወር ፖይንት ካቀረቡት ዶኩመንት ያለፈና ‘more of personal’ የሚመስል ‘issue’ ያላቸው ነው የሚመስለው፡፡ በዚኽ አኳኋን እንዴት ነው ዜጎች ‘ሚዛናዊ አስተሳሰብ’ እንዲያዳብሩ የሚጠበቀው? ከመንግሥት ጋራ አብሮ መሥራትስ እንዴት ይቻላል?››
  • ‹‹ክርስትናችን ‘የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጥ’ የሚል ሴኩላሪዝምን በአዎንታዊነትና በቀላሉ የሚገልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ያለው ነው፡፡ በሚኒስትሩ የተብራራው የሴኩላሪዝም መርሖ ግን ምእመኑን ለእምነቱ ለዘብተኛ በማድረግ በሒደት ወደ ሃይማኖት አልባነት የመምራት ተንኰል የተሸሸገበት ያስመስላል፡፡››
  • ‹‹ክርስቲያንነታችንን በየራሳችን የምንመሰክርበት መለዮአችን ማዕተብ ለመንግሥት ሴኩላርነት ተፃራሪ እንደኾነና ሊከለከል እንደሚችል መናገር ስለ መንግሥት የሴኩላሪዝም መርሖ የተሳሳተ መልእክት በማስተላለፍ ሰፊውን አማኝ ፀረ – ሴኩላር የሚያደርግ፣ ሕዝቡንና መንግሥትንም ፊት ለፊት የሚያፋጥጥ እንዳይኾን ያሰጋል፡፡››
/የመንግሥት መካከለኛ አመራሮች የኾኑ ኦርቶዶክሳውያን የሥልጠናው ተሳታፊዎች/
*              *             *
Dr shiferaw Teklemariam

No comments:

Post a Comment

wanted officials