Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, October 11, 2014

በኢኮኖሚ ነጻነት ከ152 ሃገራት ኢትዮጵያ የ139ኛ፣ በግለሰቦች ነጻነት ከአምናው በከፋ ሁኔታ ላይ ትገኛለች(Fraser Institute Canada)

መቀመጫውን ካናዳ ያደረገው ፍሬዘር ተቋም(FRASER INSTITUTE) ማክሰኞ ኦክቶበር 7 ቀን 2014ዓ/ም የዓለም የኢኮኖሚ ነጻነትን የሚዳስስ ሪፖርቱን ይፋ ያደረገ ሲሆን ሪፖርቱ ካካተታቸው 152 ሃገራት ኢትዮጵያ የ139ኛ ደረጃን ማግኘቷ ታውቋል። በሪፖርቱ ሆንግ ኮንግ ፣ሲንጋፖር፣ኒው ዚላንድ እና ስዊዘርላንድ በተከታታይ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ደረጃን ይዘዋል። በቅርቡ በብድር ቀውስ የገጠማትአርጀንቲና፣ ዚምባቡዌ፣ኮንጎ(ሪፐብሊክ)፣ እና ቬንዙዌላ ደግሞ በተከታታይ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘዋል።
ከአፍሪካ ሞሪሽየስ፣ ከአውሮፓ ስዊዘርላንድ፣ከሰሜን አሜሪካ ካናዳ፣ከኤዥያ-ፓስፊክ ሆንግ ኮንግ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ ዱባይ የመሪነቱን ቦታ ይዘዋል።
ኢትዮጵያ የገንዘብ ግሽበትን ለመቀነስ ጥቂት ጥረት በማድረጓ እንዲሁም የሰው ሃይል ዝውውር እና የውጭ ገንዘብ ምንዛሬ አስመልክቶ ቀለል ያለ ቁጥጥር ማድረጓ አምና ከነበረችበት የ142ኛ ደረጃ ወደ 139ኛ ደረጃ ከፍ ማለት አስችሏታል። ሆኖም በሪፖርቱ የተቀሩት መመዘኛዎች ግን ኢትዮጵያ ከአምናው በከፋ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ለምሳሌ የመንግስትን ልክ እና ባህሪ በሚተነትነው የሪፖርቱ ክፍል የኢትዮጵያ መንግስት የግለሰቦችን ነጻነት እና ጥቅም እየነጠቀ ለፖለቲካ ፍጆታ በቡድን ስም ለተደራጁ እንደሚሰጥ፣ የመንግስት ገንዘብ ለፖለቲካ ፍጆታ እንደሚውል እና ያላግባብ እንደሚባክን፣ለፖለቲካው የማይወግኑ ነጋዴዎችንና ጥሮ አዳሪዎችን በከፍተኛ የግብር ጫና ገፍቶ ከስራ እንደሚያፈናቅል ይገልጻል። በዚህ ረገድ አምና ከነበረበት የ6.2 ደረጃ ወደ 7.3 ማደጉ መግስት ድርጊቱን አጠናክሮ መቀጠሉን ያሳያል።
የንብረት መብት እና የህግ ስርዓትን አስመልክቶ ሪፖርቱ ባስቀመጠው መመዘኛ ኢትዮጵያ ከአምናው በ0.2 ዝቅ ብላለች። ይህም የሆነበት ምክንያት በሃገሪቱ ነጻ እና ገለልተኛ የሆነ የፍትህ ስርዓት ባለመኖሩ፣መከላከያ ሰራዊት በፖለቲካው እና በህግ ሂደቶች ላይ እንደፈለገ ጣልቃ መግባቱ፣የህግ ስርዓቱ በህዝቡ ዘንድ ተዓማኒነት ማጣቱ፣ ፖሊሶች በህዝብ ያላቸው አመኔታ ዝቅተኛ መሆን እና ዜጎች በንብረታቸው ላይ እንዳያዙ ከፍተኛ ቁጥጥር መደረጉ ወዘተ እንደሆነ ተጠቅሷል።
በመጨረሻም ሪፖርቱ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከገበያ ይልቅ በመንግስት በሚወጡ የቁጥጥር አዋጆች እና የዋጋ ተመኖች ምክንያት ወደፊት መሄድ እንዳልቻለ ፣በርካታ ነጋዴዎች በዚህ ምክንያት ከንግድ እንደወጡ እና ይህንንም ተከትሎ በበርካታ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እንደተፈጠረ ያስረዳል። በመንግስት የሚወጡት የቁጥጥር ደምቦች እና አዋጆች በሁሉም ነጋዴዎች ላይ እኩል ተፈጻሚ ያለመሆናቸው ሁኔታውን የከፋ አድርጎታል።
About the Economic Freedom Index
Economic Freedom of the World measures the degree to which the policies and institutions of countries support economic freedom. The 2014 report was prepared by James Gwartney, Florida State University; Robert A. Lawson, Southern Methodist University; and Joshua Hall, West Virginia University. This year’s publication ranks 151 countries and Hong Kong. The report also updates data in earlier reports in instances where data has been revised.
For more information on the Economic Freedom Network, datasets, and previous Economic Freedom of the World reports, visit http://www.freetheworld.com.
***
TEAM is the official partner and co-publisher of the Economic Freedom Index of the World Report in Ethiopia. The Amharic edition of this report will be published by the end of October 2014. For more information contact us: info@teaminitiatives.org

http://teaminitiatives.org/

No comments:

Post a Comment

wanted officials