ዘገባዎች አሊ አብዱላህ ሳላህ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ በሚደርስባቸው ተጽእኖ ምከንያት በየመን ያላቸውን የፖለቲካ ህይወት እርም ለማለት ወስነዋል ብለዋል፡፡
የየመን የዜና ምንጭ የሆነው የመን ኢትሀዲ እንዳለው የኢትዮጵያ መንግስት የፕሬዝደንቱን ጥያቄ ‹‹በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እስካሉ ድረስ በምንም አይነት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እንዳይሳተፉ ›› በሚል ቅድመ ሁኔታ መቀበሉን አትቷል፡፡
የቀድሞው ፕሬዝደንት ከታጣቂዎች የተለያዩ ማስፈራሪያዎች እና ዛቻዎች እየደረሰባቸው ነውም ተብሏል፡፡