ኢሳት ዜና :-ረቡዕ እለት በአዋሳ ብሉ ናይል እየተባለ የሚጠራው ሆቴል ባለቤት የሆኑት አቶ ታምራት ፣ ድርጅታቸው እንዲሸጥ በፍርድ ቤት ውሳኔ ማተላለፉን ተከትሎ፣ ውሳኔው እንዲተላለፍ አድርጓል ባሉት ወጣት ጠበቃ ዳንኤል
ላይ የግድያ ሙከራ አድርገው ተሰውረዋል። አቶ ታምራት ከአንድ ግለሰብ ጋር ባላቸው የገንዘብ ውዝግብ በመረታታቸው ሆቴላቸው እንዲሸጥ ምክንያት መሆኑን ምንጮች ሲገልጹ፣ ባለሀብቱ የመንግስት ታክስ አልከፈሉም ተብለው 12 አመት እንደተፈረደባቸውና ሌሎች
ድርጅቶቻቸው ተሽጠው ተወስኖባቸው ነበር። ራሳቸውን ከአካባቢው ሰውረው የቆዩት አቶ ታምራት ፣ ጧት ላይ ዳሻን ህንጻ ላይ በሚገኘው የጠበቃው ቢሮ በመሄድ በሸጉጥ ከገደሉት በሁዋላ፣ ከበር እንዳይወጡ ሊከላከላቸው የሞከረውን ሰውም አቁስለውት አምልጠዋል።
ቁስለኛው በኮሪያ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
ቀደም ብሎ ከባንክ እዳ ጋር በተያያዘ ሌላ ድርጅታቸው እንዲሸጥ መደረጉን ምንጮች ጠቁመዋል። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ግለሰቡ አድልኦ በሞላበት የታክስ ስርአት ንብረታቸውን እንዲያጡ ተደርጓል ሲሉ፣ ሌሎች ወገኖች ደግሞ እስካሁን ግብር ሳይከፍሉ ቆይተው አሁን
ክፈሉ ሲባሉ ድርጊቱን ፈጽመዋል ይላሉ። አቶ ታምራት እስካሁን ድረስ አልተያዙም

No comments:
Post a Comment