Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, October 7, 2014

ሰበር ዜና የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የፕሬዝዳንትነት ስልጣናቸውን አስረከቡ

ሰበር ዜና
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የፕሬዝዳንትነት ስልጣናቸውን በጊዜያዊነት ለምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ አስረከቡ፡፡ ኡሁሪ ኬንያታ ስልጣናቸውን የለቀቁት በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የቀረበባቸውን ክስ እንደ ተራ ግለሰብ ለማድመጥ ሲሉ ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ኬንያታ ዛሬ ይህን ውሳኔ ያስተላለፉት በአገሪቱ ፓርላማ ፊት በመገኘት ነው፡፡ ኬንያታ ወደ ፓርላማው ሲገቡ የአገሪቱ የክብር ዘብ ለአንድ የአገር ፕሬዝዳንት የሚደረገውን አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡ ሃላፊነታቸውን ለቀው ከፓርላማው ሲወጡ ግን ፕሬዝዳንታዊ አጀብ አልተደረገላቸውም፡፡
ኬንያታ ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር “የአገሬ ዜጎች ዴሞክራሲያዊ ውሳኔ ለሌሎች ፍርድ የሚቀርብ ስላልሆነ የ40ሚሊዮን ህዝብ ባለቤት የሆነችውን ሉዓላዊት አገሬን በፍርድ ቤት ፊት አላቆማትም” በማለት ለምን በግለሰብ ደረጃ ፍርድ ቤት ለመቅረብ እንደፈለጉ አብራርተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ኬንያታ ለፍርድ የሚቀርቡት በ2008 በአገሪቱ በተካሄደው ምርጫ ወቅት በተነሳው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመሞታቸውና ይህንንም እርሳቸው አስተባብረዋል የሚል ክስ ስለተመሰረተባቸው ነው፡፡
ኬንያታ በፍርድ ቤቱ ነፃ ከወጡ ስልጣናቸውን መልሰው ሊረከቡ እንደሚችሉ ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials