Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, January 7, 2016

በሴቶች ዶርም ውስጥ 130 በላይ የወሲብ ማርኪያ መሳሪያዎች ተገኙ፡፡ ግብረሰዶሞች ማህበር አቋቁመዋል

በሴቶች ዶርም ውስጥ በላይ የወሲብ ማርኪያ መሳሪያዎች ተገኙ; ግብረሰዶሞች ማህበር
 አቋቁመዋል







*በግብረሰዶማውያን ዙርያ የተካሄዱ ጥናቶች አዳዲስ

መረጃዎችን ይፋ አድርገዋል
*ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች
የጥቃት ሰለባ ሆነዋል
*ኢትዮጵያውያን ከተመሳሳይ ፆታ ጋር ወሲብ ሲፈፅሙ የሚያሳዩ
ፊልሞች ለገበያ ቀርበዋል
ከወራት በፊት እዚህ አዲስ አበባ ከተማችን ውስጥ የተፈፀመ
ታሪክ ነው፡፡ ድርጊቱ የተፈፀመው በአንድ ስመ-ጥር የወንዶች
ልብስ መሸጫ ቡቲክ ውስጥ ነው፡፡ ወጣቱ በቡቲኩ ውስጥ
ተቀጥሮ መስራት ከጀመረ ቆየት ብሏል፡፡ በአለባበሱ
ሽቅርቅርና ዘመናዊ ነው፡፡ ወደ ቡቲኩ የሚመጡትን ደንበኞች
በፈገግታና በትህትና እየተቀበለ ያስተናግዳል፡፡ ደንበኞች
የፈለጉትን ልብስ አስወርደው ለመለካት ወደ መልበሻ ክፍል
ሲገቡ በዓይኑ ይከተላቸዋል፡፡ በገቡበት የመልበሻ ክፍል መጋረጃ
ላይ አይኖቹን ተክሎ ለደቂቃዎች እንደሚቆይ የቡቲኩ ባለቤት
ብዙ ጊዜ ታዝቦታል፡፡ ሆኖም ደንበኞቹ አዲሱን ልብስ ለብሰው
ሲወጡ ለማየት ከመጓጓት የተነሳ እየመሰለው በዝምታ
ያልፈዋል፡፡ “ለምን እንዲህ ታያለህ?” ብሎ ጠይቆት
አያውቅም፡፡
አብዛኛዎቹ የቡቲኩ ደንበኞች ወንዶች ናቸው፡፡ እጅግ ጥቂት
ሴቶች፤ ለፍቅረኞቻቸው፣ ለባሎቻቸውና ለወንድሞቻቸው ልብስ
ለመግዛት አሊያም ለማጋዛት ካልመጡ በቀር የሴት ዘር ወደ
ስፍራው ዝር አይልም፡፡
የቡቲኩ ባለቤት አብዛኛውን ጊዜ ከቡቲኩ አይጠፋም፡፡ አልፎ
አልፎ ከውጪ የመጡ ዕቃዎችን ለመረከብ፣ ክፍያ ለመፈፀምና
መሰል ለሆኑ ጉዳዮች ወጣ ማለቱ ግን አይቀርም፡፡ የቡቲኩ
ባለቤት ከወራት በፊት ተመሳሳይ ጉዳይ ገጥሞት ነው ቡቲኩን
ለሰራተኛው ትቶለት የሄደው፡፡ ባለቤቱ ከሄደ በኋላ ዕድሜው
በሃያዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገመት አንድ ወጣት ልብስ
ለመግዛት ወደ ቡቲኩ ገባ፡፡ የቡቲኩ ሰራተኛ አይኑን ወጣቱ ላይ
ተከለ፡፡ ወጣቱ ረዘም፣ ቀጠን ያለና ያለ ዕድሜው የተንቀዋለለ
አይነት ነው፡፡ የሚፈልገውን ጅንስ መረጠና ወደ መለኪያ ክፍሉ
ገባ፡፡ የቡቲኩ ሰራተኛ ጊዜ አላጠፋም፡፡ የቡቲኩን በር ከውስጥ
ቆልፎ ወደ መለኪያው ስፍራ ሄደና መጋረጃውን ገለጠው፡፡
ወጣቱ ከለበሰው የውስጥ ሱሪ በስተቀር ከወገቡ በታች እርቃኑን
ነበር፡፡ ሊለካው በያዘው ጅንስ ሱሪ አፉን አፈነው፡፡ ያላሰበው
ነገር የገጠመው ወጣት፤ ለመጮህ፣ ለመታገልም ሆነ
ለማምለጥና ለመከላከል አቅም አልነበረውም፡፡ እንደ ብረት
ጠንክሮ ከያዘው እጅ ለማምለጥ በሞት ሽረት ትግል
ቢፍጨረጨርም አልሆነለትም፡፡ እዛው የልብስ መለኪያ ክፍል
ውስጥ አስገድዶ ደፈረው፡፡
የቡቲኩ ባለቤት ከጉዳዩ ተመልሶ ሱቁ ሲደርስ ቡቲኩ
ያለወትሮው ተዘግቷል፡፡ ሁኔታው ያልተለመደ በመሆኑ ቡቲኩን
በራሱ ቁልፍ ከመክፈቱ በፊት ጉዳዩን ለፖሊስ አመለከተ፡፡
ፖሊሶች በስፍራው ደርሰው በሩ ሲከፈት ተገድዶ የተደፈረው
ወጣት፤ እዛችው የልብስ መለኪያ ክፍል ውስጥ በትውከትና
በሰገራ ተጨማልቆ ወድቋል፡፡ ሌላ በቡቲኩ ውስጥ የተገኘ
ሰው ግን አልነበረም፡፡ ባለቤቱ በሁኔታው እጅግ ደነገጠ፡፡
ፖሊሶች እሱን በቀጥጥር ስር አዋሉና ወጣቱን ወደ ህክምና
ሥፍራ ላኩ፡፡ የቡቲኩ ባለቤት የሠራተኛውን ባህሪና ለደንበኞቹ
የነበረውን አቀባበልና ስሜት ቀስ እያለ ማስታወስ ጀመረ፡፡
እንዴት ይህንን ነገር ሳልጠረጥር ቀረሁ ሲልም ተቆጨ፡፡ ግን
ሁሉም ነገር ጅብ ከሄደ—- ሆኖበታል፡፡ ለቀናት በፖሊስ ጣቢያ
ቆይቶ፣ በዋስ ተለቀቀ፡፡ ወንጀል ፈፃሚው ግለሰብ ግን ዛሬም
ድረስ ዱካው አልተገኘም፡፡
እንዲህ ያሉ ታሪኮች ዛሬ በአገራችን በተለይም በመዲናችን
የተለመዱ ተግባራት ሆነዋል፡፡ ድርጊቱ ከዕለት ወደ እለት እጅግ
በሚዘገንንና በሚያስደነግጥ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው፡፡ ህፃናት
ልጆች በትምህርት ቤታቸው ውስጥ በሚያስተምሯቸው
መምህራን እየተደፈሩ ነው፡፡
ለዚህ ደግሞ በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ሰባተኛ ወንጀል
ችሎት እየታየ ያለውና በ“ካራክተር ሆልማርክ አካዳሚ”
መምህራን ተፈፀመ የተባለው የግብረሰዶም አስገድዶ የመድፈር
ወንጀል የቅርብ ጊዜ አብነት ነው፡፡ ስድስት መምህራን የአስርና
የአስራ አንድ አመት ዕድሜ ባላቸው ሁለት ህፃናት ላይ
በተደጋጋሚ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ክስ
ቀርቦባቸው፣ ጉዳዩ በክስ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት ድርጊቱ እጅግ እየተስፋፋ ሲሆን በማህበረሰቡም
ላይ የስነ ልቦናና የማህበራዊ ግንኙነት እንዲሁም፣ የትምህርት
ማቋረጥና የጤና ችግር እያስከተለ እንደሆነ በአዲስ አበባ ከተማ
ሴቶችና ወጣቶች ቢሮ በቅርቡ የተደረገ ጥናት ይጠቁማል፡፡
ጥናቱ በአሁኑ ወቅት ተመሳሳይ ፆታን ለወሲብ ማሰብ እጅግ
እየተለመደ መምጣቱንና ከተመሳሳይ ፆታ ጋር ወሲብ በመፈፀም
ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች መበራከታቸውን ይፋ አድርጓል፡፡ የዚህ
ችግር ሰለባዎች በአብዛኛው ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች
የሆኑ ህፃናት፣ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እንዲሁም
የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች፣ በወሲብ ንግድ ሥራ ላይ
የተሰማሩ ሰዎችና በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የህግ
ታራሚዎች መሆናቸውንም ጥናቱ አረጋግጧል፡፡
የግብረሰዶማዊነት ችግር የምዕራባውያንና የሰለጠኑት አገራት
ችግር ብቻ እንደሆነ መቁጠር፣ ህብረተሰቡን ለአስከፊ ጉዳት
እንደዳረገው የጥናት ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡ ይሄ ዓይነቱ
አዝማሚያ መዘነጋት በመፍጠር ወላጆች ስለ ልጆቻቸው
አዋዋል፣ የባህርይ ለውጥና አለባበስ እንዳያስተውሉና ወቅታዊ
እርምጃዎች እንዳይወስዱ ያደረገ ሲሆን ልጆችንም እጅግ ለከፋ
ጉዳት እያጋለጠ ነው፡፡ ትናንት በሩቁ ስንሰማው የነበረው
ግብረሰዶማዊነት፤ ዛሬ የእያንዳንዳችንን ቤት የሚያንኳኳ
የሁላችንም ሥጋት ሆኗል፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት በ“ሴቭ ዘ
ቺልድረን ካናዳ” እና በ“ብራይት ፎር ቺልድረንስ ቮለንተር
አሶሴሽን” ትብብር የተካሄደ ጥናት እንዳመለከተው፤
በከተማችን አዲስ አበባ ከሚፈፀሙ የአስገድዶ መድፈር
ወንጀሎች መካከል 22 በመቶ የሚደርሱት የተፈፀሙት
በወንዶች ላይ ነው፡፡ እነዚህ ወንዶች የተደፈሩትም ተመሳሳይ
ፆታ ባላቸው ሰዎች ነው፡፡ ጥቃቱ ከተፈፀመባቸው አብዛኛዎቹም
ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ናቸው፡፡ ከጥቃቱ
ፈፃሚዎቹ መካከል 43.7 በመቶ ያህሉ የጥቃቱ ሰለባዎች
የቅርብ ሰዎች እንደሆኑ ጥናቱ አመልክቷል፡፡
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ማህበር ከክፍለ ከተማው
ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የግብረ ሰዶማዊነት
መስፋፋትን ለማውገዝ ሰሞኑን አንድ ትልቅ ጉባዔ አዘጋጅቶ
ነበር፡፡ በገነት ሆቴል በተዘጋጀውና በሺዎች የሚቆጠሩ
የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ
የኪነጥበብ ባለሙያዎችና የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በተገኙበት
በዚህ ጉባዔ ላይ “ዩናይትድ ፎር ላይፍ ኢትዮጵያ” በተባለ አገር
በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የተዘጋጀ ጥናታዊ ፅሁፍ
ቀርቧል፡፡ የድርጅቱ መሥራችና ዳይሬክተር ዶ/ር ሥዩም
አንቶኒዮስ በዚሁ ጥናታቸው ላይ እንደገለፁት፣ ግብረሰዶማዊነት
በአገሪቱ እጅግ በጣም በሚያስደነግጥ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው፡፡
የመጀመሪያና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
የግብረሰዶማውያን መፈልፈያ ቦታዎች እየሆኑ ነው፡፡ በአንድ
መንግስታዊ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ውስጥ በተደረገ
ድንገተኛ ፍተሻ፣ በሴቶች የመኝታ ክፍሎች (ዶርም) ውስጥ
ከ130 በላይ የተለያዩ አርቴፊሻል የወሲብ መሣሪያዎች
ተገኝተዋል፡፡ እዚሁ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ
የኮንዶሚኒየም ህንፃ ውስጥ አንድ የአስራ ሰባት አመት ወጣት
በርካታ ወንድ ህፃናትን እያባባለና እያስገደደ ደፍሯል፡፡
በከተማውም ሆነ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የግብረሰዶም
ተግባር እጅግ በሚያስደነግጥ ፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑን
የጠቆሙት ዶ/ር ሥዩም፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ በተለያዩ
ጊዜያት በወንዶች ፊንጢጣ ውስጥ ገብተው የቀሩ የለስላሳ
ጠርሙስና ሌሎች ባዕድ ነገሮች በቀዶ ጥገና ወጥተዋል
ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ወንዶች ከወንድ ጋር፣ ሴቶች ደግሞ
ከሴቶች ጋር ወሲብ ሲፈፅሙ የሚያሳዩ ፊልሞች ተሠርተው
ገበያ ላይ መዋላቸውንም ጠቁመዋል፡፡
በአገሪቱ የግብረሰዶማዊነት ተግባር እጅግ መስፋፋቱን
አመላካች ከሆኑት ተግባራት መካከል ግብረሰዶማውያኑ
“ሬይንቦ” የተባለ ማህበር በግልፅ አቋቁመው፣ አባላት
ለመመልመልና ድርጊቱን ለማስፋፋት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን
ዶ/ር ሥዩም ተናግረዋል፡፡ ድርጊቱ በአገሪቱ እንዲበራከትና
እንዲስፋፋ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል በSex tourism
አማካኝነት ወደ አገራችን የሚገቡ የውጪ ዜጐች፣ ከኢትዮጵያ
ውጪ ኖረው የሚመጡ ኢትዮጵያውያን፣ ወደተለያዩ አገራት
ለንግድና ለሌሎች ሥራዎች የሚንቀሳቀሱ ሰዎች እና የልቅ
ወሲብ ፊልሞች መበራከት እንደሆኑ ተጠቁሟል፡፡
አሁን በአገሪቱ ውስጥ ባለው ሁኔታ የሴት ግብረሰዶማዊያን
(ሴት ለሴት ግንኙነት የሚፈፅሙ) በቁጥር አነስተኛ
መሆናቸውን የገለፁት ዶ/ር ሥዩም፣ የወንድ ግብረሰዶማውያን
ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ነው ብለዋል፡፡ በሆነ አጋጣሚ
ወይም በመደፈር ወደ ግብረሰዶማዊነት ህይወት የሚገቡ
ወጣቶች ወይም ህፃናት ድርጊቱን እንዳያቆሙና ከችግራቸው
እንዳይላቀቁ ግብረሰዶማውያኑ ያስፈራሯቸዋል – “አንድ ጊዜ
በፊንጢጣ ግንኙነት ማድረግ ከጀመርክ ፊንጢጣ ውስጥ
የሚፈጠር እጭ ይኖራል፡፡ እጩ ደግሞ በየጊዜው ስፐርም
ማግኘት ይኖርበታል፣ ያለዚያ ግን አንጀትህን ይቦድሰውና ለከባድ
የጤና ችግር ትጋለጣለህ” እያሉ፡፡ በዚህ ምክንያትም አንድ ጊዜ
የችግሩ ሰለባ የሆኑ ሰዎች ከድርጊቱ ለመላቀቅና ወደ
ትክክለኛው ህይወት ለመመለስ አይፈልጉም፡፡ ይህ አባባል ግን
ፈፅሞ ከእውነት የራቀና ግብረሰዶማውያኑ የአባላት
ቁጥራቸውን ለማበራከት የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡ ይህንን እጅግ አደገኛ በሆነ ፍጥነት እየተስፋፋ
ያለውን የግብረሰዶማዊነት ተግባር ለመግታት ከፍተኛ ንቅናቄ
ማድረግ እንደሚገባውና እያንዳንዱ ሰው በቤቱ ውስጥ በልጆቹ
ላይ የሚታዩ ለውጦችን ትኩረት ሰጥቶ በመከታተል፣ ልጆቹ
ወደማይመለሱበት ጥፋት ውስጥ ከመግባታቸው በፊት
ሊታደጋቸው ይገባል ሲሉ ዶ/ር ሥዩም ተናግረዋል፡፡
ግብረሰዶማውያን በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች የራሳቸው
መገናኛ ሆቴሎች፣ መቀጣጠሪያ ካፌዎች፣ የተመሳሳይ ፆታ
ወሲብ መፈፀሚያዎች፣ መዝናኛና ማሣጅ ቤቶች እንዳሏቸው
ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከተመሳሳይ ፆታ ጋር ወሲብ በመፈፀም
ሥራ የሚተዳደሩ ግብረሰዶማውያን (ቆሚታዎች ነው
የሚባሉት) በአብዛኛው በቦሌ አካባቢ የሚገኙ ሲሆን በተለይ
ደግሞ ፍሬንድሺፕ ህንፃ፣ ቦሌ ድልድዩ አጠገብና፣ ቦሌ ሸዋ ዳቦ
አካባቢዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ፒያሣ የሚገኙ ጥንታዊ ሆቴሎችና
ረዘም ያለ ዕድሜን ያስቆጠረ አንድ ካፌም የግብረሰዶማውያን
መገናኛ፣ መቀጣጠሪያና መተዋወቂያ ሥፍራዎች ናቸው፡፡
ከጥናቱ ለመረዳት እንደተቻለው፣ ግብረሰዶማውያኑ አብዛኛውን
ጊዜ ከተለመዱት የወንዶች አለባበስና ስታይል ለየት ያሉና
በቀላሉ አይን የሚስቡ ነገሮችን ማድረግ የሚያዘወትሩ ሲሆኑ
አብዛኛዎቹ በግራ ጆሮአቸው ላይ ሎቲ ያደርጋሉ፡፡ ጠበብ ያሉ
(ታይት) ሱሪዎችን፣ ሰውነትን በተለይም ደረትና ክንድን
የሚያጋልጡ ልብሶችን መልበስና ሱሪያቸውን ዝቅ በማድረግ
ፓንታቸውን እያሣዩ መሄድንም ያዘወትራሉ፡፡ ቅንድባቸውን
ለመቀንደብ፣ ጥፍራቸውን ለመሞረድና የእግር ተረከዞቻቸውን
ለመሠራት አብዛኛዎቹ ግብረሰዶማውያን የሴቶች የውበት
ሳሎኖችን ያጣብባሉ፡፡ ብዙውን ጊዜም ነጣ ያሉ (ድፍን ነጭ)
ካልሲዎችን በክፍት ጫማ ማድረግን ያዘወትራሉ፡፡ ሁልጊዜም
ንፁህና መልካም ጠረን እንዲኖራቸው ይተጋሉ፡፡ በአዲስ አበባ
የሚገኙ በርካታ ፔኒሲዮኖች ለግብረሰዶማውያን አገልግሎት
በመስጠት ተግባር ላይ እንደሚሳተፉም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለግብረሰዶማውያንነት በአብዛኛው ተጋላጭ የሚሆኑት
በወላጆቻቸው የተረሱ ህፃናት፣ ከአንድ ወላጅ ጋር ብቻ የሚኖሩ፣
የጐዳና ተዳዳሪዎች፣ ስደተኞች፣ የአዕምሮ ውሱንነት ችግር
ያለባቸው ሰዎች፣ የአካል ጉዳተኞችና በህፃናት ማሳደጊያ ውስጥና
በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ያሉ ሰዎች መሆናቸው በጥናቱ
ተጠቁሟል፡፡ የግብረሰዶማዊነት ችግር ለኤችአይቪ፣ ለወሲባዊ
ግንኙነት ፍላጐት ለማጣት፣ ራስን ለመጥላት፣ ከሰዎች
ለመገለልና ለብቸኝነት፣ ለጭንቀትና ፍርሃት እንዲሁም ከአስራ
አራት በላይ ለሚሆኑ የጤና ችግሮች እንደሚያጋልጥ ተገልጿል፡፡
ይህ ወቅታዊ ጥሪ ለወላጆች፣ ለመንግስትና ለህብረተሰቡ
እንዲሁም ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የቀረበ ሲሆን
ጉዳዩ አፋጣኝ የመፍትሔ እርምጃ ካላገኘ እጅግ አደገኛ ለሆነ
የማህበረሰባዊ ቀውስ ይዳርጋል፡፡
ከዲር ሻፊ

source : fast mereja facebook page

No comments:

Post a Comment

wanted officials