Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, January 31, 2016

የሐዋሳውን የመሬት መንቀጥቀጥ ሽሽት ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ በመኪና አደጋ የሞቱት ተማሪዎች ቀብር ዛሬ ይፈጸማል

hawasa
ከዳዊት ሰለሞን
በሐዋሳ በተደጋጋሚ የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ በመሸሽ ወደ አዲስ አበባ በማምራት ላይ የነበሩ የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መቂ አዋሽ ወንዝ ድልድይ ጋር እንደደረሱ የተሳፈሩባት ሚኒባስ ከከባድ መኪና ጋር በመላተሟ ህይወታቸው ማለፉ አይዘነጋም ።
በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት የአላማጣ ልጆችና ከ25-18 ባለ የእድሜ ክልል ውስጥ ይገኙ የነበሩ የሁለተኛ ዓመት የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ናቸው ።አገራችን አራት ኢንጅነሮችን በአንድ ቅፅበት አጥታለች ማለት ነው ።
1- አሸናፊ ተካ – እድሜ 25 – የሃይድሮሊክ ኢንጂነሪንግ ተማሪ
2 – አበበ ሞረሳ – እድሜ 23 የኬሚካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ
3 – ኢዮብ ህሉፍ – እድሜ 20 የኬሚካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ
4 – ሀየሎም በርሄ እድሜ 18 የመካኒካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ።
ዛሬ በአለማጣ ከተማ ስርዓተ ቀብራቸው የሚፈፀምላቸውን ተማሪዎች ነፍስ አምላክ ያሳርፍ፣ ለቤተሰቦቻቸው ፣ለወዳጆቻቸውና ለሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ መፅናናትን ይስጥልን ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials