(ዘ-ሐበሻ) የአርበኞች ግንቦት 7 የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ቻፕተር እሁድ ጃንዋሪ 30, 2016 ዓ.ም የድርጅቱን መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ይዞ ሕዝባዊ ስብሰባ መጥራቱን አስታወቀ::
እሁድ ጃንዋሪ 30, 2016 በሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ ደብል ትሪ ሆቴል የተጠራው ይህ ሕዝባዊ ስብሰባ ከቀኑ 2:00 እንደሚጀምር አዘጋጆቹ ለዘ-ሐበሻ የላኩት በራሪ ወረቀት ያስረዳል:
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተለይ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥና በአጠቃላይ የምስራቅ አፍሪካ አሳሳቢ በሆነው በረሃቡ; በየከተማው በተነሱ ሕዝባዊ ቁጣዎችና ሌሎች የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮችን ከሕዝብ ጋር አንስተው እንደሚወያዩ ያስታወቀው አዘጋጁ ስብሰባው ለሁሉም ሰው ክፍት በመሆኑ በስፍራው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን ወዳጆች እንዲገኙ ጥሪውን አቅርቧል::
No comments:
Post a Comment