Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, January 25, 2016

የተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብት ኮምሽን በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እሚወሰደው የሀይል እርምጃ እንዲቆም አሳሰበ፡፡




የተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብት ኮምሽን በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እሚወሰደው የሀይል እርምጃ እንዲቆም አሳሰበ፡፡

ኢሳት፤- (ጥር 13 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ጋር በተገናኘ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እየወሰደ ያለውን የሃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆም የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አርብ አሳሰበ።


በተቋሙ ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰሩ ከፍተኛ ባለሙያዎች መንግስት እየወሰደ ያለውን ድርጊት በመቃወም የጋራ መግለጫን ያወጡ ሲሆን የጸጥታ ሃይሎች እርምጃም በአፋጣኝ እልባትን እንዲያገኝ ጠይቀዋል።

በፀጥታ ሃይሎች የተገደሉ ሰዎች ድርጊትም መንግስት ዜጎቹን በአጋርነት ከመመልከት ይልቅ እንደ ሁከት ፈጣሪ (እንቅፋት) አድርጎ መመልከቱን የሚያሳይ አካሄድ ነው ሲሉ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የማስተር ፕላኑ እቅድ ተግባራዊ እንደማይደረግ ቢገልጹም የጸጥታ ሃይሎች እየወሰደ ያለው እርምጃ እጅግ አሳሳቢ መሆኑንም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ ገልጿል።

ከዚሁ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ ለእስር የተዳረጉ ሰዎች በአስቸኳይ እንዲፋቱ ጥሪውን ያቀረበው ድርጅቱ ከ140 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውም እርምጃ በገለልተኛ አካላት ማጣራት እንዲካሄድበት አስቧል።

ሃሙስ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ የመከሩት የአውሮፓ ፓርላማ አባላት የጸጥታ ሃይሎች የወሰዱት ድርጊት ማጣራት እንደሚካሄድበት ተመሳሳይ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። ይኸው አለም አቀፍ ትኩረትን ስቦ የሚገኘው የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ሁለተኛ ወሩን ያገባደደ ሲሆን፣ በእስካሁኑ ሂደትም በትንሹ 150 ሰዎች መገደላቸውን የፓርቲ አመራሮችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ይገልጻሉ።

የጋራ መግለጫን ያወጡት የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን በአለም ዙሪያ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመመርመር ለተቋሙ እንደሚያቀርቡ ለመረዳት ተችሏል።

ይኸው ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን መንግስት ሰላማዊ ሰልፈኞችን በሽብረትኝነት መፈረጁን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከመሆኑም በተጨማሪ ሃገሪቱ በሽብርተኛ ላይ በምታካሄደው ዘመቻ ላይ አለመተማመንን ሊያጎለብት እንደሚችል አመልክቷል።

ሃሳባቸውን በነጻነት ለመግለጽ አደባባይ የወጡ ዜጎችም መብታቸው ተጠብቆ ጥያቄያቸው ሊደመጥ እንደሚገባ የባለምያዎቹ ቡድን አክሎ ገልጿል።

ኢሳት

No comments:

Post a Comment

wanted officials