ኬንያ ባለ ሔብት ኢትዮጵያ ከነ አሜሪካ ማለትም ከምእራባዊያን ጋር ያላትን ትስስር ለማጠናከር አልሸባብን ትረዳለች ማለታቸዉ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነዉ አለም ይህንን ለማመን ይቸገራል ነገር ግን ይህንን እዉነታዎች ቁልጭ እያሉ በመዉጣት ላይ ይገኛሉ።
የአሜሪካ ጦር ከኢትዮጵያ በተለይም የጦር መሰረት አድርጎት ከነበረዉ አርባ ምንጭ ወጣ፡ የሁለቱ አገራት ዉስጣዊ ስምምነት መሻከር ምክንያት ተብሎ በፖለቲካ ተንታኞች የተቀመጠዉ የአሜሪካ ፍላጎት ወደ አሰብ በማዘንበሉ እንደሆነ ግልጽ እየሆነ ይገኛል፡ ያለ እኔ ሶማሌያ ከንቱ ናት እያለ! የሚኮፈሰዉ የኢትዮጵያ አምባገነን ህወሃት ከምእራባዊያኑ ገሸሽ ማለት ወዲህ ጦሩን ከሶማሌያ ማንቀሳቀስ ጀመረ።
የጦር ሄሊኮፍተሮች ወደ ኢትዮጵያና ሱዳን አረፉ ከባድ ተሽከርካሪዎች ለሶማሌያ ፌደራል መንግስት በዉሰት ተሰጡ የተመረጡ ልዩ ኮማንዶዎች አዛዦችና እግረኞች ከተመረዉ ዘር ተለቅመዉ ወደ ድሬዳዋ ተሸጋገሩ፡ በሶማሌያ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ እንዲሁም ሌሎች ኢትዮጵያዊያኖች ለናሙና ተቀመጡ፡
አልሸባብ በምርኮና በዉጊያ ያጣዉን ከባድና ቀላል መሳሪዎች በሙሉ በምስራቁ በኩል በገፍ ገባለት፡ ሐይሉን በአጭር ግዜ ዉስጥ አደራጀና ወታደራዊ መረጃ እየተሰጠዉ ወደ ወደ አፍሪካ ህብረቱ ካምፕ አሚሶም ገሰገሰ በዚያ ባደረሰዉ ጥቃት ብዙ ወገኖቻን አለቁ አዎ ወያኔ ጆሮም አይንም የለዉም በዉስጡ ያሉት ተቆርቋሪዎች ግን እንዲህ መረጃ ያወጣሉ 321 የሚጠገ ወገኖቻችንን ሙትና ምርኮ ሆነዋል ከ75 በላይ ቁስለኖች ወደ ኬንያ ተወስደዉ የት ሆስፒታል እንደሚገኙም ለጊዜዉ አልታወቀም 37 የሚጠጉ በምርኮ አልሸባብ እጅ ገብተዋል የወያኔ ኢቢሲ ከስፍራዉ የለም! ኮረኔል የማነ ገ/ማ ሶማሌያ ላይ ያደረሱትን ጥቃት ብቻ በኢቢሲ ይነግሩናል! የደረሰባቸዉንም ከዉጭ መረጃዎች እንኳን እንዳንሰማ በእጅ አዙር ገንዘብ ክፍያ ሚዲያዎች ይታለላሉ ኢትዮጵያዊ እናት ልጇን ከሶማሌ ትጠብቃለች የትግራዩ ነጻ አዉጭ ግን የበረሐ ግብሩን ለአምልኮዉ ይገብራል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
ጉድሽ ወያኔ
No comments:
Post a Comment