Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, January 17, 2016

በየአልቃይዳ ክንፍ ቡርኪናፋሱ የሆቴል ጥቃት 27 ንፁሃን ተገደሉ

በቡርኪናፋሱ የሆቴል ጥቃት 27 ንፁሃን ተገደሉ 
======
የአልቃይዳ ክንፍ እንደሆነ የተነገረለት አል ሞራቢቱን በኦጋድጉ የሚገኝን ትልቅና ዘመናዊ ሆቴል በመውረር የጅምላ ግድያ መፈፀሙ ታውቋል ።
ትናንት ምሽት ሆቴሉን የወረሩት ሽብርተኞቹ ከ18 የተለያዩ አገራት ለስብሰባ የመጡ 27 ሰዎችን መግደላቸውንና 33ቱን ማቁሰላቸውን ኤኤፍ ፒ ዘግቧል ።ከቆሰሉት ሰዎች መካከልም ፈረንሳዊው የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ ላይላ አላዊ ትጠቀሳለች ።
ሆቴሉን ከተቆጣጠሩ ሰዓታት በኋላ የደረሱት በፈረንሣይ ወታደሮች የሚመሩት የአገሪቱ የመከላከያ አባላት ለረዥም ሰዓታት የተኩስ ልውውጥ በማድረግ በሆቴሉ ታግተው የነበሩትን 126 ሰዎች ለማስለቀቅ መቻሉም ተሰምቷል።
አራት ታጣቂዎች ከወታደሮች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ መገደላቸውን ያወሳው የዜና ምንጩ ሁለቱ ሴቶች ነበሩ ብሏል ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials