Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, January 25, 2016

ኢትዮጵያ ያወጣችው የጸረ ሽብርተኝነት ህግ እንዲሰረዝ አለማቀፍ የህግ ባለሙያዎች ጠየቁ፡፡



ኢትዮጵያ ያወጣችው የጸረ ሽብርተኝነት ህግ እንዲሰረዝ አለማቀፍ የህግ ባለሙያዎች ጠየቁ፡፡
ጥር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦክላንድ ኢንስቲቲዩት እና ኢዲኤል ሲ የተባሉት መንግስታዊ ድርጅቶች በጋራ ባስጠኑት ጥናት፣ የኢትዮጵያ የጸረ-ሽብርተኝነት ህግ አለማቀፍ መስፈርቶችን ያላሟላ በመሆኑ ለውጥ እሰከሚካሄድበት ጊዜ ድረስ ጥቅም ላይ እንዳይውል ጠይቀዋል።
ድርጅቶቹ ጥናቱን ያወጡት የአፍሪካ ህብረት 26ኛ ጉባኤ በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርጎ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ መሆኑን ምክንያት በማድረግ ነው። ጥናቱ በአለማቀፍ ህግ እውቅና ባተረፉ ባለሙያዎች የተጠና መሆኑን ተቋሞቹ ለኢሳት በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ ያለው የፀረ-ሽብር ህግ መንግስት ሽብረተኝነትን እንደፈለገ በመተርጎም በዲሞክራሲያዊ አገሮች ተቀባይነት ያላቸውን ድርጊቶች ወንጀል አድርጎ በማቅርብ እርምጃ ለመውሰድ ይጠቅመዋል የሚሉት ጥናቱን የመሩት ሊዊስ ጎርዶን፣ ህጉ ለፖሊስና ለደህንንት ሃይሎች አዲስ ስልጣን በመስጠት፣ ንጽህናን የማረጋገጡን ሚና ለተከሳሽ ይሰጣል ብሎአል።
የጸረ ሽብርተኝነት ህጉ መሬታቸውን እንዳይነጡ በጠየቁ ዜጎች ላይ ሳይቀር ተፈጻሚ መሆኑን የኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር አኑራዳሃ ሚታል ገልጸዋል። የአለማቀፉ ማህበረሰብ የፖለቲካ ንግግሮችን በወንጀልነት የሚያየውንና ና ነጻነትን የሚደፈጥጠውን ህግ በአስቸኳይ እንዲወገድ መጠየቅ እንዳለበት ሚታል አክለዋል።
ህጉ ከአለማቀፍ ህጎች ጋር በሚስማማ መልኩ እስኪቀየር ድረስ፣ የጸረ ሽብር ህጉ በስራ ላይ እንዳይውል ድርጅቶቹ በመግለጫቸው ጠይቀዋል።
ኢሳት

No comments:

Post a Comment

wanted officials