Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, January 5, 2016

የድሬደዋ ሲሚንቶ ፋብሪካ በሰራተኞች እና አስተዳደሩ ዘንድ ውጥረት እንዳየለ ሰራተኞች ገለጹ፡፡

የድሬደዋ ሲሚንቶ ፋብሪካ በሰራተኞች እና አስተዳደሩ ዘንድ ውጥረት እንዳየለ ሰራተኞች ገለጹ፡፡
--------
የእረጅም ጊዜ አገልግሎት የነበራቸው ስምንት ነባር ሰራተኞች በማባረር ከሞሶቦ ፋብሪካ በመጡ የአንድ አካባቢ ሰዎች በምትካቸው እንዲቀጠሩ መደረጉ በሰራተኞች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡ በተደጋጋሚ ጊዜ አጠቃላይ የሰራተኞች ስብሰባ በሚደረግበት ወቅት በትግርኛ ቋንቋ ስብሰባው መደረጉ ያልተቀበሉት ሰራተኞች ሁሉም በሚሰማው ጥያቄ ለመጠየቅ በአማረኛ ቋንቋ ቢሆን የተሻለ ነው፡፡ በማለት ለተነሳው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ የሚሉት ሰረተኞች ከመድረኩ የተሰጠው መልስ ካልፈለጋችሁ ስበሰባውን ለቃችሁ መውጣት ይቻላል፡፡ በማለት ያስፈራሩናል፡፡ ሲሉ ይገልጻሉ፡፡ ጥያቄውን የጠየቁት ሰዎች ከስራ የመባረር እድላችን ከፍተኛ እንደሆነም፡ ስጋታቸውን የገለጹ ሲሆን በድርጅቱ ያለው ኢ ፍትሀዊ አሰራር ዘረኝነት አድሎ በሰራተኛው በኩል ቁጭት እንደፈጠረባቸው ያስረዳሉ፡፡
~~በሌላ በኩል ድርጅቱ ስራ ካቆመ ሁለት ወር ቢሆነውም አዲስ የስራ ድልድል በማለት በርካታ ሰራተኞችን በድልድል ሽፋን በቅርቡ ሊባረሩ መሆኑ እየተሰማ ነው በማለት ይገልጻሉ፡፡ ድሬደዋሲሚንቶ ፋብሪካ በአንድ አካባቢ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንደተቆጣጠሩት በመግለጽ ለማን አቤት እንደምንል ግራ ተጋብተናል ሲሉ ሰራተኞቹ ቅሬታቸውን ያሰማሉ፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials