Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 6, 2016

በምዕራብ ሀረርጌ ውስጥ የምትገኘው ሂርና ከተማ ዛሬም ተቃውሞ ቀጥሎዋል/ መንገዱን ዘግተውታል።

በምዕራብ ሀረርጌ ውስጥ የምትገኘው ሂርና ከተማ ዛሬም ተቃውሞ ቀጥሎዋል።
የምዕራብ ሀረርጌ ከተማ የሆነችው የሂርና ጀግኖች ወጣቶቹ ለሁለተኛ ጊዜ ሊገል ሊጨፈጭፋቸው ታጥቆ የመጣውን ጠላት የህወሀት ወታደሮችን በቆመጥና በድንጋይ አሳደው ከከተማዋ አስወጥተው መንገዱን ዘጉት።
 ሂርና ከአዲስ አበባ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ሲጓዙ ከጭሮ( አሰበ ተፈሪ) ቀጥላ የምትገኝ ከተማ ስትሆን ነዋሪዎቿም ቀን ከለሊት ወደ ድሬደዋ ሀረር ጅግጅጋ የሚጓዙ እንግዶችን በታታሪ ሰራተኝነት የሚያገለግሉ ተወዳጅ ስነ ምግባር ያላቸው ጨዋ ጠንካራ ሰራተኞች አገር ሰዎች ሲሆኑ ዛሬም ያለ ምንም እረፍት በተከታታይ ተቃውሞ ማሰማት የቀጠሉ ሲሆን ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ የሚወስደውን መንገድ ከላይም ከታችም ዘግተውታል።
እንደ ሰሞኑን ሁሉ የታጠቁ የህወሀት ወታደሮች ወደ ከተማዋ በእግር በመግባት ነዋሪዎቹ ላይ የጥይት ዶፍ ማውረድ የጀመሩ ሲሆን እስካሁንም ሶስት ሰዎች ተመተው የህክምና እርዳታ በመውሰድ ላይ ናቸው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials