Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, January 31, 2016

“ዕድሜዬም ኃይማኖቴም አይፈቅድም ስንቅ መቀበሉ ይቀራል እንጅ አትነኩኝም” እስክንድር ነጋ!!

Eskinder Nega 23በትላንትናው ዕለት እስክንድርን ለመጠየቅና ስንቅ ለማቀበል የሄዱ ቤተሰቦቻችን እስክንድርን ማግኘት ሳይችሉ የቋጠሩትን ምግብ ይዘው መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ምክንያቱ ደግሞ፣ እስክንድር ቤተሰብ ለማግኘት ከክፍሉ ሲወጣ የደረሰበት መብቱን የጣሰ ፍተሻ ነበር።
የትላንትናው ፍተሻ ባልተለመደ መልኩ ብልት አካባቢ ከፍተኛ መነካካትን ያካተተ እንደነበር ከውስጥ አዋቂዎች ለማወቅ ችያለሁ። እስክንድር ይህንን ብልት ላይ የሚደረግን ፍተሻ ” ዕድሜዬም፣ኃይማኖቴም ስለማይፈቅድ ስንቅ መቀበሉ ይቀራል እንጅ ( ብልቴን መንካት) አትችሉም” በሚል ከቤተሰብ ሳይገናኝና የገባለትን ምግብም ሳይቀበል መቅረቱን ለማወቅ ችያለሁ። ህምምምም!!
በእነሱው እስር ቤት፣በእነሱው ጥበቃ ሥር ያለን ግለሰብ ስንቅ ለመቀበል ሲወጣ በእንትኑ ቦንብ ያንጠለጠለ ይመስል እንደዚህ ማዋከቡ የሰዎቹን ፍርሃት ልክ ከጣራ በላይ መዋሉን ያሳያል።
“ጉድጓዱን አርቀህ አትቆፍር የሚገባበት አይታወቅምና!”
እኛም እንላለን እስክንድር ሆይ መብትህን አሳልፈህ አትስጥ፣በመብትህ አትደራደር…ሰባት ሞት የለምና!!

No comments:

Post a Comment

wanted officials