Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, January 19, 2016

መምህር ግርማ ወንድሙ ከ76 ቀናት እስር በኋላ ተፈቱ – በ4 ክሶች 240 ሺህ ብር ዋስ አስይዘዋል

girma wendimu












(ዘ-ሐበሻ) በተለያዩ ክሶች ተከሰው ላለፉት 76 ቀናት በ እስር ላይ የነበሩት ታዋቂው አጥማቂና መምህር ግርማ ወንድሙ ከእስር መፈታታቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታወቁ::
መምህር ግርማ በማታለል ወንጀል; ካለፈቃድ የቤተክርስቲያንን ስም ተጠቅመው አጥምቀዋል እንዲሁም ከሰው ሕይወት መጥፋት ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ክሶች ተመስርተውባቸው ፍርድ ቤት ሲመላለሱ መቆየታቸውን ጉዳዩን እየተከታተለች ስትዘግብ የነበረችው ዘ-ሐበሻ ማስታወቋ ይታወሳል::
መምህር ግርማ በተከሰሱበት ክሶች ሁሉ በተደጋጋሚ በዋስ ሲለቀቁ እንደገና ፖሊስ አዳዲስ ክሶችን እያመጣ እስከዛሬዋ ድረስ መቆየታቸው ይታወሳል::
ዛሬ ጃንዋሪ 13, 2015 (ጥር 4) በዋለው ችሎት መል አከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ላይ ፖሊስ ለአራተኛ ጊዜ አቅርቦት ከነበረው አንደኛ በጸበል አፍነው ሰው ገድለዋል በሚለው ክስ ፍርድ ቤቱ በ100 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፈቅዷል::
መምህር ግርማ በ800 ሺህ ብር የማጭበርበር ክስ – በ40 ሺህ ብር ዋስ ተለቀው ነበር:: እንዲሁም በቤተክህነት ክስ 50 ሺህ ብር; እንዲሁም አዲስ በተከሰሱበት ክስ 50 ሺህ ብር ዋስ ያስያዙ ሲሆን በ76 ቀናት እስር ቆይታቸው መምህሩ ለዋስ 240 ሺህ የኢትዮጵያ ብር በድምሩ አውጥተዋል::

No comments:

Post a Comment

wanted officials