በቅርቡ የብሄር ብሄረሰብ ቀን የተከበረባትና የብሄሮች መቻቻል ኣንድነት እና ፍቅር ተምሳሌት ተደርጋ በወያኔ ኣገዛዝ የተንቆለጳጰሰችው ጋምቤላ በጎሳ ጦርነት እየተናጠች ነው ። አዲስ ስታንዳርድ የተባለው እንግሊዘኛ ድህረገጽ ባወጣው ሰበር ዜና መሰረት በጋምቤላ ክልል በተነሳው ግጭት ቀጥሎ በጋምቤላ ከተማ እስር ቤት ላይ በደረሰ ኣደጋ ቢያንስ ሰባት ሰዎች መሞታቸውን ዘግቧል።አስር ቤቱን ሰብረው ለመግባት የኑኤር ተወላጆች ባደረጉት ግጭት ሰባቱ ሰዎች መገደላቸው ታውቋል።
በቦታው የነበረውን የኣይን ምስክር ያነጋገረው ኣዲስ ስታንዳርድ እንደዘገበው የኑኤር አና ኣኝዋክ ጎሳን ግጭት ተከትሎ በጋምቤላ ከተማ ኣራት ኪሎ ተብሎ በሚጠሯው የጋምቤላ ማረሚያ ቤት ላይ የታጠቁ የኑኤር ተወላጆች ከባድ ጥቃት ኣድርሰዋል።በግጭቱ ተጎድቶ ለሕክምና የመጣ ሰው ዋቢ ያደረገ ዘገባው ጋምቤላ መንግስት ኣልባ ሆናለች ብሏል፥ኣከባቢው ላይ የሰፈሩ የወያኔ ፖሊሶች አና ወታደሮች የጋምቤላ ከተማ ፖሊሶችን ትጥቅ ኣስፈትተዋቸዋል።
በኣከባቢው ግጭት የተነሳው በሁለቱ ኦሳዎች ኣባላት ግለሰቦች መካከል በመሬት ቁርሾ ኣለመግባባት ተከትሎ የተነሳውን ተኩስ እና ከቁትትር ውጪ የወጣውን ግጭት ኣስታኮ የክልሉ ታጣቂዎች የኑኤር ተወላጆችን ኣፍሰው ማሰር ከጀመሩ በኋላ መሆኑ ታውቋል። በክልሉ ኣሁንም ግጭቱ የቀጠለ ሲሆን በከተማው ከፍተኛ ውጥረት ኣይሏል።
No comments:
Post a Comment