Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, January 17, 2016

በመንፈስ ቅዱስ ይመሩናል ስንል በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሊመሩን ነው እንዴ?


(ቃልኪዳን ኃይሉ)
ፍሬንዶች ሰሞኑን ብዙ ነገሮች ተከሰቱ ልበል (ማነው የሆነ ሰው በል አለኝ እሺ ብያለሁ) ፕሪዝን ብሬክ ከስንት ጊዜው በኋላ ቀጣዩ ሲዝን ሊወጣ መሆኑ፤ የሀናና በሆነ ልጅ መወደድ(ይቺ እንኳጥገራ ነገር ይመስለኛል)፤ የገነት ጤንነት መመለስ፤ የበውቀቱ መጻሕፍ መውጣት፤ የአዲስ አበባ ኦሮሚያ ማስተር ፕላን መቆም፤ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ለመመለስ ግንባተው መፋጠኑ፤ የሰለሞን መኪና በድጋሚ ጨረታ መቅረብ…
ለማንኛውም የመጨረሻዋ ግን ከብዳኛለች፡፡ የጳጳሱ ቁጣና ማስፈራራት፤ ጳጳሱ በጣም ነው ያስደነገጡኝ፡፡ እሳቸው እኮ በመንፈስ ቅዱስ ይመሩናል ያልናቸው የሁላችንም የመንፈስ አባት ናቸው፡፡ ግን በጠበቅናቸው ሙድ ሳይሆን ኢቢሲ ላይ በባለስልጣኖቻችን ላይ የምናያት አብዮታዊ ትእቢትና መንፈስ ይዘው ከችእእእእ… ደነገጥኩ መቀደስ ማስቀደስ ትተው የጠ/ሚ ኃይለማርያም ልጅ ሰርግ ሔደው እስከ ቅልቅል የከረሙ ነው የመሰለኝ፡፡ ኧረ አባታችን ደስ አይልም፡፡
ጳጳሱ በማሕበረ ቅዱሳን ላይ እንደዛ ሲዝቱ አባይ ፀሀዬ ትዝ አለኝ፡፡ “ተወደደም ተጠላ የአዲስ አበባ-ኦሮሚያ ማስተር ፕላን ይተገበራል” የሚሉ ነው የመሰለኝ፡፡ እኛ አቡነ ሽኖዳን በኢትዮጵያ ይተካሉ ብለን ስንጠብቅ “አቡነ አባይ ፀሀዬ” ሆነው ቁጭ ኧረ አባታችን!፡፡
ይልቁንስ የዳንኤል ክብረት መልስ እንዴት መሠጠችኝ፡፡ “ማሕበረ ቅዱሳንን ማንንም አያፈርሰውም እግዚአብሔር ካልፈቀደ በስተቀር” ብሏል፡፡ ዋው ፓምም…. ፓፓምም… መሳጭ ብለናል፡፡ ጳጳሱ ይጠቀሙበታል የምለውን ስክነትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ አካሄድ ትንሹ ዳንኤል (እዚህ ጋር የእድሜ ንፅፅሩ ከጳጳሱ አንፃር እንጂ ከእኔ ጋር እንዳልሆነ ይታሰብበት) ሲጠቀምበት ሳይ ተመቸኝ፡፡
እውነቱን ነው ቤቴልሔም በናቡከደነጾር ፈርሷል፤ የሰለሞን ቤተመቅደስ ፈርሷል፤ ክርስቶስም በጠላቶቹ ተይዞ ተተፍቶበታል፣ ተዘብቶበታል፣ ተገርፏል፣ ተሰቅሏል… ይህ ሁሉ ግን በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ እንጂ በሌሎች ጉልበትና ድንፋታ አልነበረም፡፡ ዳንኤልም ያለው ይሄንን ነው፡፡
እኔ እምለው ለምንድነው ማሕበረቅዱሳንን ማፍረስ የፈለጉት፤ ምክንያታቸው በቂና አሳማኝ ይሆን ይሆን፤ ካፈረሱት በኋላ የሚመጣውን ችግር ለመቀበል ዝግጁ ናቸው (ከመጻሕፍ ቅዱስ ካልተማሩ ከኦሮሚያ ማስተር ፕላንና የሕዝብ ቁጣ መማር ደግ ነው)፤ የቤተክርስቲያኗን ወጣቶች እንደሚከፉና እንደሚከፋፈሉ አልተረዱት ይሆን?
አባት ልጁ ምን ቢያጠፋ እንዲህ እስከማፍረስ ድረስ ይሄድ ይሆን፤ ከመንፈሳዊ አንድምታው ይልቅ ፖለቲካዊ ይዞታ ይኖረው ይሆን? ቀኖና ቤተክርስቲያንን ብዙዎች እየጣሱ ይመከሩ ይከለሱ ተብሎ እንዳልታለፈ ስለምን ማሕበረ ቅዱሳን ላይ ደመ መራራ መሆን አስፈለገ?
ጳጳሱ ግን የማሕበረ ቅዱሳንን በሕልውና ያለመቀጠል ጉዳይ እንደኢህአዴግ የመሬት ፖሊሲ የማይቀርና በመቃብሬ ላይ የሚሆን ነው ምናምን ማለታቸው በመንፈስ አባታችን ለምንላቸው ለእኛ ትንሽ አስከፍቶናል፡፡ ቢያስቡበት ደስ ይለናል፡፡
እኔእምለው ግን ባለፈው ቅዱስ ሲኖዶሱ “ማሕበረ ቅዱሳን ምንም አላደረገም ይልቁንስ እርሶ እያስቸገሩ ነው ካልሆነ እናወግዞታለን” ተባሉ ምናምን አልተባለም፡፡ ታዲያ በቆረጣ ጳጳሱ ምን እያደረጉ ነው፡፡ ሌላ ችግር ሊፈጥሩ ደግሞ እኛም በተራችን ሲኖዶሱ ይውረድ ብለን አባቶቻችንን እንድንሰድብና እንድንቀየም ሊገፉን ነው?
ሲኖዶሱ፣ በሳል አባቶች፣ ቤተክርስቲያኔ የምትሉ አንዴ ብቻ ሳይሆን ደግማችሁ ደጋግማችሁ አስቡበት፡፡ በድጋሚ ከልሱት፡፡ ዋጋ የሚያስከፍል መሰለኝ፡፡ አባቶችን ለመምከር አይደለም ግን እኛ እንዲህ ስለተሰማን ነው፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials