Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 6, 2016

አንዳርጋቸው ጽጌ የአመቱ ምርጥ ሰው በመባል በኢትዮጵያን ዲጄ እና አጋር ድረገጾቹ መመረጡ ታወቀ::

ከኢትዮጵያ የነጻነት ትግል ስሙ የማይፋቀው ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ የአመቱ ምርጥ ሰው በመባል በኢትዮጵያን ዲጄ እና አጋር ድረገጾቹ መመረጡ ታወቀ::
ለረጅም አመታቶች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተጫነውን የጭቆና ቀንበር ለማንሳት ደፋ ቀና በማለት የነጻነት ጎህ በእትዮጵያ ምድር ላይ እንዲበራ ሲታገል ለእስር የተዳረገው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ አንዳርጋቸው ጽጌ ከኢትዮጵያ የነጻነት ትግር ውስጥ ሊፋቅ የማይችል ታሪካዊ ስሙ በየቦታው ይዘከራል ይታወሳል::
ለሕዝብ ልጆች ጀግና የሆነው ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢትዮጵያን ዲጄ እና አጋር ድረ ገጾቹ የ2015 ምርጥ ሰው ተብሎ ሲሰየም ታሪክ የማይለውጠው እና የማይሽረው ስሙን እና የትግል ድርሻው ከፍ በማድረግ ለተተኪው ትውልድ እንዲተላለፍ እና ያለውም ትውልድ በተግባር እንዲተረጉመው በማስተማር ከሃገራች እና ከወገናችን ላይ የተጫነው የጭቆና ወንበር እንዲገፈፍ በጋራ በመታገል የታጋይ አንዳርጋቸውን የትግል ስራዎች በመከተል እና በአንድነት በመታገል ቃል እየገባን የኢትዮጵያ ዲጄ እና አጋር ድረ ገጾቹ የአመቱ ምርጥ ሰው በመባሉ የተሰማንን ደስታ ለመላው የለውጥ ሃይሎች እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለመግለጽ እንወዳለን:: አንዳርጋቸው ጽጌ ከታሰረበት ይፈታ ዘንድ ትግሉን አጠናክረን በመቀጠል ጫናውን አበርትተን የነጻነት ችቦ እንድናበራ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን::... ኢትዮጵያን ዲጄ እና አጋር ድህረገጾቹ @ethiopiandj.com amharicdrama.com/ amharicplay.com / zena24online.com /clickhabesh.com / tekuret.com / tikuszena.com ...

No comments:

Post a Comment

wanted officials