Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, January 28, 2016

(የአቡነ መልኬጼዲቅና የኦርጋኑ ጉዳይ) ባልበላውም ጭሬ ደፋዋለሁ አለች ዶሮ !! | ጥቂት ጥያቄ መልስኛ ስለ ኦርጋን

(የአቡነ መልኬጼዲቅና የኦርጋኑ ጉዳይ) ባልበላውም ጭሬ ደፋዋለሁ አለች ዶሮ !! | ጥቂት ጥያቄ መልስኛ ስለ ኦርጋን


Abune Melekestedik Organ
ከመኳንንት ታዬ
ሰው ማንነቱን በራሱ ማስተዋል ሲቆጥበው ያለነጋሪ እንደሚያተርፍ አውን ነው።ማትረፉ በራሱ የንግዱ መልካም መሆንን አያመላክትም።አንዳንዴ ተፈላጊው ነገር ገበያ ላይ እንብዛም ባለመኖሩ ረባም አረባም የሚፈለገው ነገር እስካለ ብቻ ገዢም የሚገዛበት ሻጭም አንዲሸጥ እድል ይሰጠዋል።

ይህ የማትረፉ አለም ውጣ ውረድ ነው።ሰውም በማንነቱ እንዲሁ የሚሆንበት አጋጣሚ አለ።ትልቅ የሚባል ፤መልካም የሚባል ሃይማኖቱን አክባሪ የሚባል ፤ ብቻ እንደሁነቱ አሳሳቢነት ለስፍር የሚሞላ ማንነት አለው የምንለው ሰው ሲጠፋ ፤ይሻላል የሚባል ከማይሻሉት የተሻለ ይመረጣል።
ይህ ሁሉ ምርጫ ለሚሰጥ ወይም ላለው ነገር ነው ።ሃይማኖት ማለት ግን አንድ እና አንድ ነው። መሆን አለመሆን።ከዚህ ያለፈ ስሌትም ባለቤትነትም አይኖረውም።ብዙዎች ለስህተታቸው ማስታገሻ የሚያደርጉት የነሱን አላዋቂነት ሳይሆን ድሮ እያወቁ ቆይተው ዛሬ መርሳታቸውን ባለማስታውስ ነው ።
ይህቺን ደረሰኝ የምታክል ፅሁፍ እንድከትባት ያስቻለኝ በቅርቡ የተለየ የመዝሙር መሳሪያን በተመለከተ በስደት እገኛለሁ ከሚሉ አንድ አባት የተሰነዘረው ሃሰብ ነው።በርግጥ ከላይ ለማለት እንደሞከርኩት ሰው ችግር የሚገጥመው ከሃገሩ ሲሰደድ ሳይሆን ከማንነቱ ሲሰደድ ነው። ለዚህም እንደማስረጃ ከምንይዛቸው ነገሮች እንዲህ እንደ አሁኔው አይነት ነገሮችን ስናይ ለግምትም ለማለትም እንቸገራለን።አውነት ነው። ላያስደነግጠንም ላያሳስበንም ይችላል ። እንቅስቃሴውም አሁን አደለም ።አሁን ንግግር የሆነበት ምክንያት ሲደመር ስለሆነ ነው።ግን እኮ ኦርጋን ሌሎች ይጠቀማሉ ።ስለዚህ እኛም መጠቀም አለበን ነው የሚሉን አቡነ መልከፀዲቅ።
ደግ እሳቸው ተቀብለውታል ።ለማስረጃውም ሌሎችን ጠቅሰዋል።እንግዲህ ልፋ ያለው ….. ከሆነ ምን ይደረጋል። ግን እኮ ሌሎች እኛ ልንበላ ጨርሶ የማንችለውን አህያ እና ፈረስ እየበሉ ክርስቶስን የሚያመልኩ አሉ።ለዚህም ደግሞ እንደማስረጃ ሮሜ ም14 ከቁጥር፩-፬ ድረስ እንዲህ ተብሎአል።በእምነት የደከመውን ተቀበሉት በአሳቡም ላይ አትፍረዱ።
ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈቀደለት የሚያምን አለ፤ ደካማው ግን አትክልት ይበላል ይላል…”ይህ እንግዲህ በመፅሃፍ የተፈቀደ እና ያልተፈቀደ ፤የሚያፅይፍ የሚበላ እና የማያፀይፍ የሚበላ አለ።በመፅሃፍ እንደተናገረ። በዚህ አውነት ሌሎች ሃገር የሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን ከላይ የተጠቀሱትን ፈረስ ወይም ውሻ ወይም ለእኛ ለኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሃዶ አማኞች ለመብልም ለባህሪያችንም ያልተፈቀደ ነገር የሌላ ሃገር ኦርቶዶክሶች ስለ በሉ ይበላሉ ወይ ?አሁን ባሉበት ሁኔታ አብነት መሆን ከሆነ እንግዲህ ይብሉና ይኸው እኔ በላሁ ብለው ያሳዩንና ስላኦርጋኑ እናስብበት ።አለዚያ ብዙ የሚሰራ ስራ እያለ በኑፋቄ ስራ ላይ ተሰማርቶ”ባልበላውም ጭሬ ደፋዋለሁ እንዳለችው ዶሮ “የሚሆንበዎ ይመስለኛል ።
ለዚህም ነው ከሃገር ብቻ ሳይሆን ከማንነታችንም እየተሰደድን ይመስላል ለማለት ያስደፈረኝ ።ወደ መፅሃፍ ቅዱሳዊው መልስ ስንጓዝ በስህተትም በኦርጋን አመስግኑ የሚል አላየንም። ስለዚህ ከተሰበከልን ወንጌል ውጭ የሚሰብከንን መላአክትም ቢሆነ እንዳንቀበል መፅሃፍ ያዛልና አንቀበልም።
ይቆየን

No comments:

Post a Comment

wanted officials