በጎንደር 14 ሰዎች ተገደሉ፣ የመንግስት ሃይሎች የዘር ግጭት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ ነው ተባለ
የህወሃት አመራር በጎንደር በአማራና በቅማት ብሄረሰቦች መካከል በድጋሚ የዘር ግጭት ለመፍጠር እየሞከረ እንደሆነ ከአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመለከተ።
ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ተገድለው የተገኙ 6 የአማራ ብሄር ተወላጆች በህወሃት የደህንነት ሃይላት የተገደሉ ቢሆንም ገዳዮቹ ቅማንቶች ናቸው በሚል ቅስቀሳ የአማራ ህዝብ በቅማንት ላይ እንዲነሳ ሆን ተብሎ ታስቦ የተሰራበት እንደነበር ኢሳት ከስፍራው ያነጋገራቸው እማኞች አስረድተዋል።
አብዛኞቹ ሟቾች ወጣቶች ሲሆኑ ተገድለው ከተጣሉ ከ 1 ቀን በኋል ሬሳቸው እንደተገኘ ለማወቅ ተችሏል።
ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የአማራ ብሄር ተወላጆች ለበቀል ባለመነሳሳታቸው የተበሳጩት የህወሃት/ኢህአዴግ የደህንነት ካድሬዎች፣ ከቅማንት ወገን ሌሎች 8 ሰዎችን የገደሏቸው ሲሆን፣ ለቅማንቶች ደግሞ “አማራ ገደላቸው” የሚል ወሬ በመንዛት የቅማንትን ህዝብ ለበቀል እንዲነሳ ሲቀሰቅሱ እንደነበር ታውቋል።
ሆኖም የአካባቢው ነዋሪዎች ስሜታዊ ሳይሆኑ ወንጀለኞቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም፣ የህወሃት/ኢህአዴግ የደህንነት ሃላፊዎች ግን ገዳዮቹ ለመያዝ ወይም ለፍርድ ለማቅረብ አለመፈለጋቸው ተመልክቷል።
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ በአካባቢው የሚኖሩ አንድ ሰው ለኢሳት እንደገለጹት፣ በአሁኑ ሰዓት ንጹሃንን እየገደለ የዘር ግጭት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ያለው የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት እንደሆነ ህዝቡ በሚገባ ተረድቷል ብለዋል። የአካባቢው ህብረሰብ በግድያው የህወሃት እጅ እንዳለበት እንደተገነዘበ ለማወቅ ተችሏል።
ህወሃት ኢህአዴግ ከዚህ በፊት በሁለቱ ህዝቦች መካከል በተደጋጋሚ ግጭት ለመፍጠር ሞክሮ የነበረ ቢሆንም፣ በሁለቱ ህዝብ ውይይት ለአጭር ጊዜም ቢሆን እርቅ እርቅ ተፈጥሮ በአካባቢው ሰላም ሰፍኖ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ህወሃት አሁን የቀሰቀሰው የዘር ግጭት በአካባቢው ሰላም በማደፍረስ የእራሱን አላማ ለማሳካት እንደሆነ ታውቋል።

No comments:
Post a Comment