Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 13, 2016

የኦህዴድና የብአዴን ሃይሎች የዘር ፍጅት በመቀስቀስ የተቃውሞውን አቅጣጫ ለመቀየር እየሞከሩ ነው








በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ሁለት ወራት ባስቆጠረበት በአሁኑ ወቅት፣ የመንግስት የደህንነት ሃይሎች የዘር ፍጅት በመቀስቀስ የተቃውሞውን አቅጣጫ ለመቀየር በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን ታማኝ የውስጥ ምንጮች ለኢሳት ገለጹ።
የዘር ፍጅት እቅዱ በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ የሌላ ብሄረሰብ ተወላጆች በተለይም በአማሮች ላይ የተነጣጠረና የተቀነባበረ ጥቃት በመሰንዘር፣ የሌላ አካባቢ ተወላጆች በስጋት ከመንግስት ጎን እንዲቆሙ በማድረግ ሁኔታውን ወደ እርስ-በእርስ ግጭት በመውሰድ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን መረዳት ተችሏል።
ወደ ኢትዮጵያ የሚሰራጩት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) እና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) በኢትዮጵያ ስርጭታቸው መታወኩ የመንግስት የደህንነት ሃይሎች የታቀደውን ጥፋት በቀላሉ ለማስፈጸም ይቻላቸዋል የሚል ግንዛቤ መያዙንም ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያብራራል።
በመንግስት የደህንነት ሃይሎች የተቀነባበረው ጥቃት፣ በህዝቦች መካከል ግጭት ከመጋበዝ ባሻገር፣ በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲሁም ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች የተቀነባበሩ የቦንብ ፍንዳታዎች ጭምር ለማከናወን መታቀዱንና የቀደሙ ዕርምጃዎች የዚህ ውጤት መሆናቸው ተመልክቷል።
ድርጊቱን ለማስፈጸም የተመለመሉ የኦህዴድና የብአዴን ሰዎች ጭምር መዘጋጀታቸውንም ለመረዳት ተችሏል።
ለኢሳት መረጃውን ያደረሱት ወገኖች ህዝብን ለፍጅት ለመዳረግ በመንግስት የደህንነት ተቋም እየታቀደና እየተወሰደ ያለውን እርምጃ የሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ በትኩረት እንዲከታተሉና መረጃውን በማድረስ እንዲተባበሩም ጥሪ አቅርበዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials